በቤት ውስጥ ግርዛት የአምስት ወር ልጅ ሞተ

ግርዛት

በጣልያን ሰሜናዊ ሪጊዮ ኢሚሊያ ግዛት ወላጆች የአምስት ወር ሕፃን ልጃቸውን በቤት ውስጥ ለመግረዝ ሲሞክሩ ሕፃኑ ለድንገተኛ የልብ ህመም በመጋለጡ ወደ ቦሎኛ ሆስፒታል ቢወሰድም ወዲያው ሕይወቱ ሊያልፍ ችሏል።

ሕፃኑ ወደ ሆስፒታል ተወስዶ ሕይወቱ በዚያው ያለፈው ባለፈው አርብ ዕለት ነበር። የግዛቲቱ ባለሥልጣናት ትውልደ ጋናዊያን ናቸው የተባሉት የሕፃኑ ወላጆች ላይ ምርመራ መጀመራቸውን አስታውቀዋል።

ባለፈው የአውሮፓውያኑ ዓመት መጨረሻ ላይም በጣልያን መዲና ሮም በሚገኝ የስደተኞች መጠለያ የሁለት ዓመት ሕፃን በተመሳሳይ የግርዛት ሙከራ ሕይወቱ አልፏል።

"አደጋውን ስሰማ ክው ነበር ያልኩት..." አቶ ተወልደ ገ/ማርያም

በጣልያን በዓመት በአማካይ አምስት ሺህ ግርዛቶች የሚካሄዱ ሲሆን ከአንድ ሦስተኛ በላይ የሚሆነው በህገወጥ መንገድ የሚካሄድ እንደሆነ መረጃዎች ያሳያሉ።

በካቶሊካዊቷ ጣልያን የግርዛት አገልግሎት በሕዝብ የጤና ተቋማት አይሰጥም። በአገሪቱ የሚገኙ በርካታ ስደተኞች ደግሞ ግርዛት በተለምዶ ከሚካሄድባቸው እስልምናን ከሚከተሉ አገራት የሄዱ ናቸው።

ምንም እንኳ ግርዛት ቀላል የሚባል ህክምና ቢሆንም ሙሉ በሙሉ ግን አደጋን የማያስከትል አደለም።

የገጠር አስተማሪው አንድ ሚሊዮን ዶላር አሸነፉ

ተያያዥ ርዕሶች