ዓለም ለሴቶች እንዳልተሰራች የሚያሳዩ ነገሮች

ሴት ወታደር በግዳጅ ላይ Image copyright David Turnley via Getty Images

ካሮላይን ክሪያዶ ፔሬዝ ነገሮች ሁሌም ከወንዶች አንፃር ብቻ መቃኘታቸውንና ይህች ዓለም እንዴት ለወንድ ብቻ እንድትሆን ተደርጋ እየተቀረፀች እንዳለ ጥናት መስራት የጀመረችው በአንድ ወቅት የልብ ህመምን በሚመለከት የተሰበሰቡ መረጃዎች ሁሉ በወንዶች የህመሙ ምልክት ላይ ብቻ የተመሰረቱ መሆናቸውን ካስተዋለች በኋላ ነው።

ጡትን ከግንዛቤ ካልከተቱት የፖሊስ ጥይት መከላከያ ልብሶችና ጫማዎች ጀምሮ በርካታ ነገሮች ወንድን ብቻ ታሳቢ በማድረግ የተሰሩ እንደሆኑ ትናገራለች።

የህዋ ልብሶች

በአንድ ወቅት ናሳ ሴቶች ብቻ ወደ ህዋ የሚያደርጉትን ጉዞ በመሰረዙ በትዊተር ከፍተኛ ውግዘት ደርሶበት ነበር። ጉዞው የተሰረዘው ጠፈርተኛዋ አኒ ማክሌን ከዚህ በፊት ትለብስ የነበረው የህዋ ጉዞ ልብስ ትልቅ የነበረ ቢሆንም ሙሉ የሴት ቡድን በሚያደርገው ጉዞ ላይ ግን መካከለኛ መጠን ያለው ልብስ የበለጠ ልኳ ስለሆነ እሱን እለብሳለሁ በማለቷ ነበር።

ሴቶች 'ፌሚኒስት' መባልን ለምን ይጠላሉ?

የህዋ ልብሶቹ ወንዶችን ብቻ ታሳቢ አድርገው የሚሰሩ በመሆናቸው ትልቅ፣ በጣም ትልቅና ምናልባትም መካከለኛ መጠን ብቻ እንዲኖራቸው ተደርገው ነው የተሰሩት፤ ትንሽ ሚባል ነገር የለም።

በወቅቱ በናሳ ሁለት መካከለኛ መጠን ያላቸው የህዋ ልብሶች የነበሩ ቢሆንም ለጉዞ ዝግጁ ተደርጎ የነበረው ግን አንዱ ብቻ ነበር።

የጦር መሳሪያዎች

እንደ አውሮፓውያኑ በ2016 አሜሪካ ቀደም ሲል ወንዶችን ብቻ ትመለምልበት ለነበረው የምድርና ባህር ኃይል ክፍል ሴቶችን መመልመል ብትጀምርም በእነዚህ ክፍሎች ያሉ የጦር መሳሪያዎች ሁሉ ግን ለወንድ ብቻ እንዲመቹ ሆነው የተሰሩ ናቸው።

የዲሞክራቲክ ፓርቲዋ የኮንግረስ አባል ኒኪ ሶንጋስ ይህ የአገሪቱ ጦር ኃይል ምን ያክል ለሴት አባላቱ ፍላጎቶች ምላሽ እንደማይሰጥ ማሳያ መሆኑን ተናግረው ነበር።

ብቻቸውን ወደ መዝናኛ ስፍራ የሚሄዱ ሴቶች ፈተና

በዚህ ምክንያት ሴት ወታደሮች መሳሪያ ለመተኮስና የጥይት መከላከያ ልብሶችን መልበስ እንኳ እንደሚቸገሩ ተናግረዋል።

እንደ አውሮፓውያኑ ባለፈው ዓመት የጦር ኃይሉ ለሴቶች ምቹ የሆኑ መሳሪያዎችን እንደሚያቀርብ አስታውቆ ነበር።

በሴቶች የወታደራዊ አገልግሎት ላይ ጥናት የሰሩት አሌክስ ኤሊያስ "ሴቶች እስከ 2018 ለወንዶች በተሰሩ መሳሪያዎች በኢራቅና በአፍጋኒስታን ተሰማርተው ነበር" ብለዋል።

Image copyright Getty Images

ስማርት ስልኮች

የስማርት ስልክ መተግበሪያዎችና የስልኮቹ መጠን ራሱ ለወንዶች እንዲሆኑ ተደርገው ተሰርተዋል ብለው የሚያስቡ ብዙ ሴቶች ናቸው።

በአማካይ የሴቶች እጅ ከወንዶች በአንድ ኢንች የሚያንስ ሲሆን የስማርት ስልክ አምራች ኩባንያዎች ደግሞ የስልኮቹን መጠን እያሳደጉ መምጣታቸው ችግር ነው ይላሉ።

12 ሴ.ሜ በሆነ ወይም በትልቅ አይፎን በአንድ እጅ ስልክን ይዞ መልዕክት መላክ ለበርካታ ሴቶችና ትንሽ እጅ ላላቸው ወንዶች ከባድ ወይም የማይቻል ነው።

የስፖርት ልብሶች

ታዋቂው የአሜሪካ የቅርጫት ኳስ ተጫዋች ስቴፈን ከሪ አዲስ የህፃናት የስፖርት ጫማ ንድፍ ሲያወጣ የሰራው ለወንዶች ብቻ የነበረ ሲሆን፤ አንዲት የዘጠኝ ዓመት ህፃን ለምን የወንዶች ብቻ የሚል ደብዳቤ ፅፋለት ነበር።

"የሴቶችን የሩጫ ስፖርት እንደምትደግፍ አውቃለሁ ምክንያቱም ሁለት ሴቶች ልጆች አሉህ" በማለት ስህተቱን እንደሚያርም ተስፋ እንደምታደርግ ገልፃ ነበር።

ሴቶች በሰሜን ኮሪያ ሠራዊት ውስጥ

እሱም ህፃኗን ስለደብዳቤዋ አመስግኖ ስለተፈጠረው ነገር ማብራሪያ ሰጥቷል።

ሳይንሳዊ መሳሪያዎች

በካንሳስ አልያንስ የባይሎጂ ተመራማሪ የሆኑት ጀሲካ ማውንትስ በቤተ ሙከራ የሚጠቀሟቸው የምርምር መሳሪያዎች በሙሉ ለወንድ ተብለው የተሰሩ እንደሆኑ ለቢቢሲ ተናግረዋል።

በአለም ላይ በየቀኑ 137 ሴቶች በህይወት አጋሮቻቸውና በቤተሰቦቻቸው ይገደላሉ

ይህ መሆኑ ደግሞ የሚረብሽ ብቻ ሳይሆን ለአደጋ ስጋት እንደሚሆንም ይናገራሉ። ሰፋፊ ገዋኖች እንቅስቃሴ ላይ በቁሳቁሶች ሲያዙ ትልልቅ ቡትስ ጫማዎች ደግሞ ለመውደቅ ይዳርጋል።

ሥራ ቦታዎች

የታሪክና ሌሎችም ምሁራን ወንበሮችና ሌሎችም የቢሮ እቃዎች ለወንዶች ምቹ እንዲሆኑ ተደርገው መሰራታቸውን የሚመለከቱ ጥናቶችን አድርገዋል።

ከእነዚህ መካከል አንዷ የሆኑት የታሪክ ምሁሯ ዋጅዳ ሺርሊ በኩባንያዎች ውስጥ ሁሌም ስለ ቡድን ሥራ ውጤታማነት እንደሚወራ፤ ነገር ግን ይህ ትርጉም እንደማይሰጥ "ምቹ በሆነ አካባቢ ሳይቀመጥ ማን ስለ ቡድን ስራ ሊጨነቅ ይችላል?" በማለት ያስረዳሉ።

በዚህ ዘገባ ላይ ተጨማሪ መረጃ