ኢቲ 302 ቦይንግ 737 ማክስ የተከሰከሰበት ምክንያት ቅድመ-ሪፖርት ዛሬ ይወጣል

ኢቲ 302 የተከሰከሰበት ምክንያት ቅድመ-ሪፖርት ዛሬ ይወጣል

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

የምስሉ መግለጫ,

በአደጋው ህይወታቸውን ከጡት መካከል

ከአዲስ አበባ ወደ ናይሮቢ ለመብረር ከተነሳ በጥቂት ደቂቃዎች ውስጥ የተከሰከሰውና የሁሉንም ተሳፋሪዎች ህይወት የቀጠፈው ቦይንግ 737 ማክስ 8 ሞዴል አውሮፕላን የተከሰከሰበት ምክንያት ቅድመ-ሪፖርት ዛሬ ይወጣል ተብሎ ይጠበቃል።

በትራንስፖርት ሚንስትር የኮሚኒኬሽን ኃላፊ የሆኑት አቶ ሙሴ ይሄይስ ለቢቢሲ እንዳረጋገጡት ዛሬ የአደጋውን ምክንያት ሲያጣራ የነበረው ቡድን ቅድመ-ሪፖርቱን ከረፋዱ 4፡30 ላይ ያቀርባል።

የትራንስፖርት ሚንስቴር ትናንት አመሻሽ ላይ ለመገናኛ ብዙሃን በላከው መግለጫ የዓለም አቀፉ ሲቪል አቪዬሽን ድርጅት አደጋው ከደረሰበት በመጀመሪያዎቹ 30 ቀናት ውስጥ ቅድመ ሪፖርት እንዲቀርብ በሚጠይቀው መሠረት ቅድመ ሪፖርቱ ዛሬ ይፋ ይሆናል።

ዛሬ ከረፋዱ 4፡30 ጀምሮ የትራንስፖርት ሚንስትር የሚያቀርበውን ቅድመ-ሪፖርት እንዲሁም ከዚሁ ጋር ተያይዞ የሚወጡ መረጃዎችን በቀጥታ ወደ እናንተ እናደርሳለን።