ሱዳናውያን ፕሬዚዳንታቸውን ከስልጣን ይውረዱ እያሉ ነው

ተቃዋሚ ሰልፈኞች የሰላም ምልክት እያሳዩ Image copyright Reuters

ሱዳናውያን ፕሬዝዳንታቸውን ኦማር አል በሽር ከስልጣን እንዲወርዱ በመጠየቃቸው ከደህንነት አካላት የተለያዩ እርምጃዎች ቢወሰድባቸውም አሁንም አደባባይ ከመውጣት አላቆሙም።

በሺህዎች የሚቆጠሩ ሰልፈኞች በመናገሻ ከተማዋ ካርቱም በፕሬዝዳንቱ መኖሪያ ቅጥር ግቢ ፊት ለፊት በመገኘት የይውረዱ ጥያቄያቸውን አቅርበዋል።

ሰኞ ዕለት ከመከላከያ ኃይሉ ጋር የሽግግር መንግሥት መመስረት በሚቻልበት ጉዳይ ላይ መነጋገር የሚፈልግ የተቃዋሚ ፓርቲዎች ጥምረት ተቃውሞ አካሂዷል።

እንደ ሀገሪቱ ባለስልጣናት ከሆነ ከቅዳሜ ዕለት ጀምሮ ሰባት ተቃዋሚ ሰልፈኞች ሕይወታቸውን አጥተዋል። የሀገር ውስጥ ጉዳዮች ሚኒስትሩ ለሀገሪቱ የህዝብ እንደራሴ ተወካዮች ሰኞ ዕለት እንዳሉት ስድስቱ ሰዎች በካርቱም አንዱ ደግሞ በዳርፉር ተገድለዋል።

የሩዋንዳ ዘር ጭፍጨፋ 25ኛ አመት እየታሰበ ነው

በሰሜን ሸዋ ዞኖች የፀጥታ አስከባሪ ተቋማት እርምጃ እንዲወስዱ ታዘዘ

ሕዝብ ስለመሪው ምን እንደሚያስብ እንዴት እንወቅ?

አክለውም 15 ተቃዋሚ ሰልፈኞች እና 42 የፀጥታ አካላት ጉዳት ሲደርስባቸው 2ሺህ አምስት መቶ ሰዎች ደግሞ በቁጥጥር ስር ውለዋል ሲሉ አስረድተዋል።

ፕሬዝዳንት አል በሺር እ.ኤ.አ ከ 1989 ጀምሮ ሱዳንን ያስተዳደሩ ሲሆን 'ስልጣን ይብቃዎት፤ ይውረዱ' የሚል የሕዝብ ድምፅ በአደባባይ መሰማት ከጀመረ ወራት ተቆጥሯል።

Image copyright Reuters

የተቃውሞ ሰልፉ መነሻ ሰበብ የኑሮ ውድነት የነበረ ሲሆን አሁን ግን ፕሬዝዳንቱን ይውረዱ ወደሚል ተቀይሯል።

በሳምንቱ መጨረሻ ላይ በርካታ ቁጥር ያላቸው ተቃዋሚ ሰልፈኞች ካርቱም በሚገኘው የመከላከያ ኃይሉ እና የፕሬዝዳንቱ ዋና ቢሮ ፊት ለፊት በመሰባሰብ ተቃውሟቸውን አሰምተዋል።

ተቃዋሚ ሰልፈኞቹ ወታደሩ ለመንግሥት ያለውን ወገንተኝነት እንዲተው ጠይቀዋል።

ሰኞ እለት ምሽት የተቃዋሚ ሰልፈኞቹ ተወካዮች ከመከላከያ ኃይሉ ጋር የሽግግር መንግስት ስለሚመሰረትበት መነጋገር እንደሚፈልጉ ገልፀዋል።

ኦማር ኤል ዲጊር የሚባሉ ጎምቱ የተቃውሞ ፖለቲካ አስተባባሪ ለፈረንሳዩ የዜና ወኪል "የአብዮቱን ፍላጎት የሚወክል መንገድ" እየፈለግን ነው ብለዋል።

ምንም እንኳ የፀጥታ ኃይሎች የተቃውሞ ሰልፉን ለመበተን የተለያዩ ነገሮች ቢያደርጉም ሰኞ ዕለት ግን የመቀመጥ አድማው ለሶስተኛ ጊዜ ተካሂዷል።

መንግሥት ተገቢ ያልሆነ ኃይል ሰልፈኞቹ ላይ በመጠቀም በመብት ተሟጋጮች ስሙ እየተብጠለጠለ ይገኛል።

ተያያዥ ርዕሶች

በዚህ ዘገባ ላይ ተጨማሪ መረጃ