የሱዳን ፖሊስ አባላት ተቃዋሚ ሰልፈኞች ላይ እርምጃ እንዳይወስድ ታዘዙ

ተቃዋሚ ሰልፈኞች እየጮሁና የሱዳንን ባንዲራ እያውለበለቡ Image copyright AFP

የሱዳን ፖሊስ በሺዎች የሚቆጠሩ ተቃዋሚ ሰልፈኞች ላይ ምንም አይነት እርምጃ እንዳይወስድ አባላቱን አዘዘ። ተቃዋሚ ሰልፈኞቹ ከአርብ ዕለት ጀምሮ በጦር ኃይሉ ዋና መስሪያ ቤት ፊት ለፊት በመገኘት ተቃውሟቸውን እያሰሙ ነው።

ተቃዋሚ ሰልፈኞቹ ፕሬዝዳንት ኦማር አል በሺር ከስልጣን እንዲወርዱ የሚጠይቁ ናቸው።

ቀደም ብሎ ከዋና መስሪያ ቤቱ ቅጥር ግቢ ውጪ ከፍተኛ የተኩስ ድምፅ የተሰማ ሲሆን ይህ የሆነውም ወታደሮች ተቃዋሚ ሰልፈኞቹ ላይ የመንግሥት የደህንነት ኃይሎች እንዳይተኩሱባቸው ሲከላከሉ እንደሆነ ተሰምቷል።

የፖሊስ ቃል አቀባይ ባወጣው መግለጫ "ሁሉንም አባላቱን ሰላማዊ ሰልፈኞች ላይ እንዳይተኩሱ ታዟል።" ብሏል።

የዓለማችን ሃብታም ሴቶች

በሰሜን ሸዋ ዞኖች የፀጥታ አስከባሪ ተቋማት እርምጃ እንዲወስዱ ታዘዘ

በሊቢያ በስራ ላይ ያለ ብቸኛው አየር መንገድ ጥቃት ደረሰበት

"ፈጣሪ ሀገራችንን እንዲያረጋጋ እና ደህንነታችን እንዲጠብቅ .... ሱዳናውያን አንድ እንዲያደርገን....ሰላማዊ የስልጣን ሽግግር እንዲኖር መግባባት ላይ እንድንደርስ እንፀልያለን"ብለዋል በመግለጫቸው።

ከዚህ ቀደም ሰላማዊ ሰልፈኞቹን ለመበተን የሞከሩ የብሄራዊ ፀጥታና ደህንነት አባላት ከወታደሩ ጋር መጋጨታቸው ተዘግቧል።

የተቃውሞ ሰልፉ ከተጀመረ ቢያንስ ሁለት ወታደሮች ከዋና መስሪያ ቤቱ ውጪ መሞታቸው ተዘግቧል።

የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትሩ ሰባት ተቃዋሚ ሰልፈኞች መሞታቸውን 15 መጎዳታቸውን እና 42 የደህንነት ኃይሎች መጎዳታቸውን ገልፀው ነበር።

2ሺህ አምስት መቶ ሰዎችም በቁጥጥር ስር መዋላቸውን አስታውቀዋል።

ከተቃዋሚ ሰልፈኞቹ አንዱ ለቢቢሲ እንደገለፀው ሰልፉን ለመበተን አስለቃሽ ጋዝ፣ ጥይት በደህንነት ኃይሎች ተተኩሷል።

ወታደሮችም ተቃዋሚ ሰልፈኞችን በግቢያቸው እንዲደበቁ እንደረዷቸው ተናግሯል።

አክሎም "ኦማር አል በሺር ተቃዋሚ ሰልፈኞቹን ከአደባባዮች ላይ ዞር እንዲሉ ለማድረግ መሞከራቸው እርባና ቢስ ነው ምክንያቱም የትም አንሄድም " ብሏል።

ሌላ ተቃዋሚ ሰልፈኛ በበኩሉ ሁሉም የመከላከያ እና የፖሊስ አባላት ተቃዋሚ ሰልፈኞቹን እንደማይደግፉ ገልጧል።

ከፍተኛ ሹማምንቶቹ አሁንም ፕሬዝዳንቱን የሚደግፉ ሲሆን አነስተኛ ማዕረግ ያላቸውና ተራው ወታደርና አባል ግን ከሕዝቡ ጋር ነው ሲል ለቢቢሲ አስረድቷል።

አሜሪካ፣ እንግሊዝና ናርዌይ ሱዳን የፖለቲካ ሽግግር ለማድረግ መዘጋጀት እንዳለበት ገልፀዋል።

ተያያዥ ርዕሶች