ለዘመናት በስልጣን ላይ ያሉት ስድስቱ አፍሪካውያን መሪዎች

ለዘመናት በስልጣን ላይ የቆዩ 6 አፍሪካውያን መሪዎች Image copyright Getty Images
አጭር የምስል መግለጫ ከግራ ወደ ቀኝ፦ ቲዮዶር ኦኒያንግ-ኢኳቶሪያል ጊኒ፣ ፖል ቢያ-ካሜሩን፣ ዩዌሪ ሙሴቪ- ኡጋንዳ፣ ኢድሪስ ዴቢ-ቻድ፣ ኢሳያስ አፈወርቂ-ኤርትራ፣ ዴኒስ ሳሶኡ ናጉኤሶ-ሪፓብሊክ ኦፍ ኮንጎ

አምባገነን የአፍሪካ መሪዎች ሳይወዱ በግድ በህዝባዊ ተቃውሞ አልያም ሞት ካላሸነፋቸው በቀረ ስልጣን አሳልፈው ሲሰጡ ማየት የተለመደ አይደለም። ለዚህም የዚምባብዌው ሮበርት ሙጋቤ፣ የሊቢያው ሙአመር ጋዳፊ እንዲሁም ትናንት ከስልጣን የተነሱት የሱዳኑ ኦማር አልበሽር ማሳያ ናቸው።

ዛሬስ ለዘመናት በስልጣን ላይ ተደላድለው እንደሉ የሚገኙ የሚገኙ የአፍሪካ መሪዎች እነማን ናቸው?

1. ቲዮዶር ኦኒያንግ ጉኤማ ባሶጎ፦ የኢኳቶሪያል ጊኒ ፕሬዝደንት

ቲዮዶር ኦኒያንግ ጉኤማ ባሶጎ በመካከለኛው አፍሪካ የምትገኘውን ኢኳቶሪያል ጊኒን ከ1971 ዓ.ም ጀምሮ ሲያስተዳድሩ ቆይተዋል። ይህም ለ40 ዓመታት ያክል ማለት ነው። ቲዮዶር ወደስልጣን የመጡት አጎታቸውን በመፈንቅለ መንግሥት ከስልጣን ካባረሩ በኋላ ነበር። ከስልጣን የተባረሩት የቲዮዶር አጎት በመንበራቸው ላይ ሳሉ ፈጽመውተል ለተባሉበት ወንጀል የሞት ብይን ተፈጽሞባቸዋል።

የሙጋቤ ሕይወት በምስል

ቲዮዶር በዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ተከራካሪዎች ''እጅግ ጨካኙ መሪ'' ተብለው ተፈርጀዋል። ቲዮዶር ከድሃ ሃገራቸው ሀብት ዘርፈው በፈረንሳይ ቪላዎች ገንብተዋል፤ ቅንጡ መኪኖችን ገዝተዋል ተብለው በፈረንሳይ መንግሥት ምርመራ እየተካሄደባቸው ነው።

ቲዎዶር ልጃቸውንም የሃገሪቱ ምክትል ፕሬዝደንት አድርገው ሾማዋል። የቲዮዶር ልጅም ቢሆን በአሜሪካ በስሙ ተመዝገቦ የሚገኘው ንብረት ከሀገሪቱ በተሰረቀ ንብረት ነው የተገዛው በማለት የአሜሪካ መንግሥት የምክትል ፕሬዝዳንቱን ንብረት እንዳይንቀሳቀስ ለማድረግ ጉዳዩን ፍርድ ቤት ቢወስደውም የቲዎዶር ልጅ ግን ንብረቱን ያፈራሁት በህጋዊ መልኩ በተገኘ ገቢ ነው በማለት እየተከራከረ ይገኛል።

2. ፖል ቢያ፦ የካሜሩን ፕሬዝደንት

ፖል ቢያ ከ1975 ዓ.ም ጀምሮ ካሜሮንን በፕሬዝደንትነት እየመሩ ይገኛሉ።

በወቅቱ የካሜሩን ፕሬዝደንት ከነበሩት ፕሬዝደንት አሀመዱ አሂድጆ ጋር መልካም ግነኙነት የነበራቸው ቢያ ፕሬዝደንት ሆነው ከመመረጣቸው በፊት የካሜሮን ጠቅላይ ሚንስትር በመሆን አገልግለዋል። በወቅቱ የነበረው የካሜሮን ህግ ጠቅላይ ሚንስትሩ የፕሬዝደንቱ ተተኪ ይሆናሉ ይላል። ፕሬዝደንት አሂድጆ ባልተጠበቀ ሁኔታ በፍቃዳቸው ስልጣናቸውን መልቀቃቸውን ተከትሎ ፖል ቢያ መንበረ ሥልጣኑን ተቆጣጠሩ።

ቢያ 1976 ላይ የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራ ቢደረግባቸውም ሳይሳካ ቀርቷል። መንበረ መንግሥታቸው ተቃውሞ የማይለየው ቢያ፤ ከአንድ ዓመት በፊት በተደረገው እና በተቀውሞ በታጀበው ምርጫ ለ7ኛ ጊዜ አሸንፊያለሁ በማለት ካሜሮንን ማስተዳደራቸውን ቀጥለዋል።

3. ዩዌሪ ሙሴቪኒ፦ የኡጋንዳ ፕሬዝደንት

ሙሉ የመዝገብ ስማቸው ዩዌሪ ካጉታ ሙሴቪኒ ሲሆን ከ1976 ጀምሮ ኡጋንዳን በፕሬዝደንትነት ሲመሩ ቆይተዋል።

ሙሴቪኒ ወደ መንበረ ስልጣን የመጡት በጭካኔ የሚታወቀውን የኢዲያሚን ዳዳ መንግሥትን ከስልጣን በማባረር ነበር። ሙሴቪኒ ወደ ስልጣን ሲመጡ በወሰዷቸው እርምጃዎች በምዕራባውያን ሃገራት ዘንድ ተቀባይነትን አግኝተው ነበር።

ሙሴቪኒ ኤችአይቪ ኤድስን በመከላከል ረገድ ያስመዘገቡት ድል ብዙ ጊዜ ይወሳላቸዋል። በሰሜን ዩጋንዳ፣ ሱዳን እና ዲሞክራቲክ ሪፓብሊክ ኦፍ ኮንጎ በስፋት የሚንቀሳቀሰው እና በጆሴፍ ኮኔ የሚመራው ''ሎርድ ሬዚስታንስ አርሚ'' ለሙሴቪኒ ፈተና ሆኖ ቆይቷል።

ኦማር አል-ባሽር: ከየት ወደየት?

ሎርድ ሬዚስታንስ አርሚዎች ዩጋንዳ በመድበለ ፓርቲ ዲሞክራሲ እና በአስርቱ ትዕዛዛት እንድትመራ ማድረግ ዓላማቸው አድርገው ይታገላሉ። የሙሴቪኒ እና የአሜሪካ ጦር የሎርድ ሬዚስታንስ አርሚ መሪ የሆነውን ጆሴፍ ኮኔን ለመግደል በርካታ ኦፕሬሽኖችንን ቢያደርግም እስካሁን ጆሴፍ ኮኔ ያለበት አይታወቅም።

ሙሴቪኒ በቅርቡ በሕገ-መንግሥቱ ላይ ሰፍሮ የሚገኘውን ስልጣን ላይ የመቆየት የዕድሜ ጣሪያን ለማስቀነስ እና መንበረ ስልጣን ላይ ለመቆየት ባደረጉት ጥረት ከፍተኛ የሆነ ተቃውሞ ገጥሟቸዋል።

4. ኢድሪስ ዴቢ፦ የቻድ ፕሬዝደንት

ኢድሪስ ዴቢ ኢትኖ ቻድን ላለፉት 29 ዓመታት ሲመሩ ቆይተዋል። ኢድሪስ ዴቢ በአሜሪካ እና ፈረንሳይ ድጋፍ ስልጣን ላይ የወጡትን ፕሬዝደንት ሃይሴኔ ሃብሬ በማስወገድ ነበር ስልጣኑን የተቆናጠጡት። ስልጣን ላይ ከወጡ ከስድስት ዓመታት በኋላ የመጀመሪያ መድብለ ፓርቲ በመመስረት ሃገራዊ ምርጫ አሸነፉ።

አነስተኛ የህዝብ ድጋፍ እንዳላቸው የሚነገረው ዴቢ፤ የራሳቸውን ጎሳ ከሃገር ያስቀድማሉ ሲባሉ ይወቀሳሉ።

የጉበት ህመም ወደ ፈረንሳይ ለህክምና በተደጋጋሚ የሚያመላልሳቸው ዴቢ፤ በቅርቡ ፓርላማው የስልጣናቸውን ኃያልነት የሚጨምር ህግ አስተላልፏል።

5. ኢሳያስ አፈወርቂ፦ የኤርትራ ፕሬዝደንት

ከጋዜጠኞች ጋር ባደረጉት የትኛውም ቃለ መጠይቅ ምንም አይነት ነገር ስለ ግለ ህይወታቸው አውርተው የማያውቁት የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ፤ ጥቂት የሚባሉ ሰዎች ብቻ ስለ እርሳቸው ያውቃሉ። ኢሳያስ አፈወርቂ በ1936 ዓ.ም በአስመራ ከተማ ነው የተወለዱት። የሁለተኛ ደርጃ ትምህርታቸውን በልዑል መኮንን ሁለተኛ ደርጃ ት/ቤት ተከታትለዋል።

ያስመዘገቡት ከፍተኛ ነጥብ የቀድሞ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ በአሁኑ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የኢንጂነሪንግ ትምህርት እንዲከታተሉ ቢያስችላቸውም በ1958 ዓ.ም ትምህርታቸውን አቋርጠው የኤርትራ ነጻ አውጪ ግንባርን ለመቀላቀል ወደ ሱዳን ተጓዙ።

"ኢትዮጵያ የከሸፈች ሀገር እየሆነች ነው" ሻለቃ ዳዊት

ኢሳያስ አፈወርቂ የኤርትራ ነጻ አውጪ ግንባር አባል ከነበሩት ሳባ ኃይሌ ጋር ትዳር መስርተው የሁለት ወንዶችና የአንድ ሴት ልጅ አባት ሆነዋል።

ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ በአፍሪካ ለረጅም ዓመታት በሃገር መሪነት በስልጣን ላይ የቆዩ መሪ ብቻም ሳይሆኑ በቁመት ረጅም ከሚባሉት የሃገር መሪዎች መካከል አንዱ ናቸው።

የ1985ቱን ህዝበ-ውሳኔን ተከትሎ ኢሳያስ አፈወርቂ የኤርትራ የመጀመሪያው ፕሬዝዳንት እና የብሔራዊ ምክር ቤቱ ዋና ጸሀፊ ሆነው የተመረጡ ሲሆን፤ ይህም የመንግሥትን የሥራ አስፈጻሚ እና የፍትህ አካሉን በቁጥጥራቸው ስር እንዲሆን አስችሏቸዋል።

ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ የሚመሩት ህዝባዊ ግንባር ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ በሃገሪቱ የሚገኘው ብቸኛው የፖለቲካ ፓርቲ ሲሆን ከመስራቾቹ መካከልም አንዱ ናቸው። በ1989 ዓ.ም ጸድቆ የነበርው ሕገ-መንግሥትም ሥራ ላይ ሳይውል ቀርቷል።

በኢሳያስ አፈወርቂ የሚመራው የኤርትራ መንግሥት በተለያዩ አጋጣሚዎች በሰብዓዊ መብቶች ጥሰት እና በሃገሪቱ ውስጥ ዲሞክራሲያዊ ለውጥ አላመጣም ተብሎ በተደጋጋሚ ይወቀሳል።

ስለ ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ምን ያህል ያውቃሉ?

6. ዴኒስ ሳሶኡ ናጉኤሶ፦ የሪፓብሊክ ኦፍ ኮንጎ ፕሬዚደንት

ዴኒስ በሃገሪቱ ጦር አማካኝነት በ1970ዎቹ መጀመሪያ ላይ የሪፓብሊክ ኦፍ ኮንጎ ፕሬዚደንት ተደርገው ተሰየሙ። ከ14 ዓመታት የስልጣን ዘመን በኋላ በተካሄደ ምርጫ ተሸነፉ። ይህ ያልተዋጠላቸው ዴኒስ ሳሶኡ ናጉኤሶ ከ5 ዓመታት በኋላ በእርስ በርስ ጦርነት ስልጣን ላይ ወጡ።

ከሶስት ዓመታት በፊት በተደረገ ምርጫ ለ7ኛ ጊዜ ምርጫ አሸንፌያለሁ በማለት ስልጣን ላይ ተደላድለው ተቀምጠዋል።

በአጠቃላይ ለ38 ዓመታት ገደማ ስልጣን ላይ የቆዩት ዴኒስ የስልጣን ላይ ቆይታቸውን ለማራዘም በማሰብ ሕገ-መንግሥቱ እንዲሻሻል ማድረጋቸው ክፉኛ አስኮንኗቸዋል።

የኢትዮጵያና አሜሪካ የተለየ ግንኙነት እስከምን ድረስ?

አየር ወለዱ ኮረኔል ለምዕራባውያን ሃገራት ነዳጅ እንዲያወጡ ፍቃድ በመስጠት ይታወቃሉ። ይህም ብቻ ሳይሆን ዴኒስ ሳሶኡ እጃቸው በሙስና ተጨማልቋል የሚል ክስ በተደጋጋሚ ይነሳባቸዋል። የፈረንሳይ ፍርድ ቤት ዴኒስ በፈረንሳይ ቅንጡ ቪላዎች እና መኪኖችን አፍርተዋል በሚል ለቀረበባቸው ክስ ምርመራ እንዲካሄድ ትዕዛዝ ሰጥቶ ነበረ።

በዚህ ዘገባ ላይ ተጨማሪ መረጃ