ሰላሳ ሰባት ማዳበሪያ ዕፀ ፋርስ ወደ ውጭ ሊወጣ ሲል በያቤሎ መቆጣጠሪያ ላይ ተያዘ

ካናቢስ Image copyright ከኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን ገፅ የተወሰደ

በትናንትናው ዕለት 37 ማዳበሪያ ዕፀ ፋርስ ከሀገር ሊወጣ ሲል ያቤሎ መቆጣጠሪያ ላይ መያዙን በገቢዎች ሚኒስትር የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክተር አቶ አዲሱ ይርጋ ለቢቢሲ ገልፀዋል።

የሰሌዳ ቁጥር 57519 ET ኮድ 3 የሆነ የግንባታ ጠጠር የጫነ ሲኖትራክ ተሽከርካሪ ላይም ዕፀ ፋርሱ ተጭኖ እንደነበር ተገልጿል።

ዕፀ ፋርስ የጫነው መኪና የተነሳበትን ትክክለኛ ቦታ ለማወቅ ፖሊስ ምርመራ ላይ እንደሆነ የገለፁት አቶ አዲሱ ወደ ውጭ ሊወጣ እንደነበር ግን ተረጋግጧል።

አብዛኛውን ጊዜ በቁጥጥር ላይ ሲውሉ አሽከርካሪዎቹ መኪኖቹን ትተው የሚጠፉ ሲሆን በዚሁም አጋጣሚ አሽከርካሪው መኪናውን አቁሞ እንዳመለጠ ይናገራሉ።

"ዕፀ ፋርስ በመሸጥ ልጆቼን አሳድጋለሁ" የሌሴቶዋ አምራች

በተደጋጋሚ ከሀገር ሊወጣ ሲል ዕፀ ፋርስ የሚያዝ ሲሆን፤ ባለፈው ሳምንት ቶጎ ጫሌ ላይ የተያዘውም ተጠቃሽ ነው።

የጉምሩክ ስርአቱ አደረጃጀቱና ላይ ከፍተኛ መሻሻል እንዳለ የሚናገሩት አቶ አዲሱ በየኬላው የሚገኙ ፈታሾች አጥብቀው እንደሚቆጣጠሩ ይገልፃሉ።

አሜሪካዊው ዶክተር ለአራት አመት ህፃን ዕፀ ፋርስ አዘዘ

ከዚህ በፊት የፌደራል ፖሊስ በአገሪቱ የሚገኙትን 94 ኬላዎች ይቆጣጠሩ የነበረ ሲሆን ነገር ግን በቦታው ላይ ተመድበው የሚሰሩት በተጨማሪ ስራነት በመሆኑ ግዳጅ በሚሄዱበት ጊዜ ኬላዎች ክፍት ስለሚሆኑ እሱን ክፍተት ለመሙላትም ራሳቸውን የቻሉ የጉምሩክ ፖሊሶች እንዲቋቋሙ ተደርጓል።

የካናዳ ፓርላማ ዕፀ-ፋርስን ለመዝናኛነት ህጋዊ አደረገ

ሙሉ ጊዜያቸውን ለኮንትሮባንድና ለየጉምሩክ ስራ የሚያውሉ ለእያንዳንዱ ኬላ 1400 የጉምሩክ ፖሊሶች የሚያስፈልጉ መሆኑን የጠቀሱት አቶ አዲሱ ተጠሪነታቸውም ለፌደራል ፖሊስ ነው። ከነዚህም ውስጥ የተወሰኑትም ወደ ስራ እንደገቡ አቶ አዲሱ ይናገራሉ።

ተያያዥ ርዕሶች