"ይሁዳ የተደበደበበት መንገድ ልክ አይደለም" - አይሁዳውያን

ቅርጹን ልጆች በእንጨት ቀጥቅጠውታል Image copyright AFP
አጭር የምስል መግለጫ ቅርጹን ልጆች በእንጨት ቀጥቅጠውታል

ነገሩ የተከሰተው ፖላንድ ውስጥ። የክርስትና ሀይማኖት ተከታዮች ስቅለትን እያከበሩ ነበር።

በየዓመቱ እንደሚያደርጉት ዘንድሮም እየሱስ ክርስቶስን አሳልፎ የሰጠውን ይሁዳ የሚወክል ቅርጽ ሠርተው ነበር። የሠሩትን ቅርጽ መሬት ላይ ጥለውም በከፋ ሁኔታ ደብድበውታል።

«ፕሬዝደንት 'ጥላቻ'፤ ከተማችንን ጥለው ይውጡ» የትራምፕ ተቃዋሚዎች

ይህን የሚያሳይ ቪድዮ በፖላንድ የዜና ድረ ገጽ ላይ ከተሰራጨ በኋላ፤ ዓለም አቀፉ የአይሁዳውያን ተቋም (ወርልጅ ጄዊሽ ኮንግረስ) ቅሬታ አሰምቷል። ተቋሙ እንዳለው፤ ይመታ የነበረው ቅርጽ አይሁዳዊ ይመስላል።

በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወቅት ከሦስት ሚሊየን በላይ ፓላንዳዊ አይሁዳውያን መገደላቸው ይታወሳል።

አብራሞቪች እስራኤላዊ ዜግነት ለማግኘት ብቁ ናቸው

Image copyright AFP
አጭር የምስል መግለጫ ቅርጹ ተሰቅሎም ተቃጥሏል

ፖላንድ ውስጥ በየዓመቱ ለስቅለት ህጻናት የተሠራውን ቅርጽ ይመታሉ። በእድሜ ገፋ ያሉ ሰዎች ደግሞ መንገድ ላይ ይጎትቱታል። በይሁዳ ቅርጽ የሚሠራው ትልቅ ቀይ አፍንጫ ያለው፣ ጥቁር ኮፍያ ያደረገም ነው።

ባለፉት ዓመታት የፖላንድ ካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ይህን ባህል ከልክላ ነበር።

«ጠቅላይ ሚኒስትሩ ስለ በረከት አናግረውናል» የአቶ በረከት ስምዖን ባለቤት

ባለፈው ዓመት ፓላንድና እስራኤል እሰጣ ገባ ውስጥ ገብተው እንደነበረ ይታወሳል። የፖላንድ መንግሥት፤ ፓላንድን ከናዚ ጭፍጨፋ ጋር አያይዞ መጥቀስ ወንጀል ነው ብሎ ነበር። አሜሪካ ሕጉን ተችታውም ነበር።

ጥናቶች እንደሚያሳዩት፣ ብዙ ሺ ፖላንዳውያን ከናዚ ጀርመን ጋር አብረዋል። በተቃራኒው በርካታ ፖላንዳውያን አይሁዳውያንን ከጭፍጨፋው ለመታደግ ሕይወታቸውን አደጋ ውስጥ ጥለው ነበር።

ተያያዥ ርዕሶች