የሰሜን ኮሪያው ኪም ጆንግ ኡን ከፑቲን ጋር ለመምከር ሩስያ ገብተዋል

የፎቶው ባለመብት, Reuters
የሰሜን ኮሪያ መንግሥት ቴሌቪዥን ኪም ጆንግ ኡን ወደ ሩስያ ሲያቀኑ አሳይቷል
የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን ከሩስያው አቻቸው ቭላድሚር ፑቲን ጋር ለሚያደርጉት ውይይት በሚል ወደ ሞስኮ ማቅናታቸው ተሰምቷል።
የሰሜን ኮሪያ መንግሥት ቴሌቪዥን ኪም በግል ባቡራቸው ወደ ሩስያ እንዳመሩ ጠቁሟል።
ሁለቱ መሪዎች እርስ በርስ ለማውጋት ሲገናኙ ይህ ለመጀመሪያ ጊዚ ነው።
ከሩስያ ቤተ መንግሥት ክሬምሊን የወጡ ወሬዎች እንደሚጠቁሙት ሁለቱ መሪዎች ሐሙስ ዕለት ቭላዲቮስቶክ በተሰኘችው የወደብ ከተማ ተገናኝተው ስለ ኮሪያ ሰርጥ ይመክራሉ።
የሰሜን ኮሪያው ቴሌቪዥን ጣቢያ ግን የውይይታቸው መቼት ገና ውሉ እንዳለየ ነው የዘገበው። ቢሆንም የወደብ ከተማዋ ቭላዲቮስቶክ በሰሜን ኮሪያ እና ሩስያ ሰንደቅ ዓላማ ከወዲሁ ደምቃለች።
የፖለቲካ ተንታኞች ኪም ከአሜሪካው ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ ጋር የነበራቸው ወይይት ያልተሳካ በመሆኑ ነው ፊታቸውን ወደ ፑቲን ያዞሩት ይላሉ።
በያዝነው የፈረንጆቹ ዓመት መባቻ ትራምፕ እና ኪም ተገናኝተው ችግራቸውን ለመፍታት ቢሞክሩም ያለስምምነት መለያየታቸው ይታወሳል።
የቭላድሚር ፑቲን ቀኝ እጅ የሆኑት የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ አማካሪው ዩሪ ዩሻኮቭ በኮሪያ ሰርጥ ያለው ፖለቲካዊ አለመረጋጋት አሁን ላይ ትንሽ ጋብ ብሏል ይላሉ።
የሰሜን ኮሪያው ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በበኩላቸው ሩስያ የእኛን ርዕይ የምትጋራ ሀገር ናት ሲሉ የሁለቱን ሀገራት ወዳጅነት የሚያጠናክር ሃሳብ ሰንዝረዋል።
ሰሜን ኮሪያ በያዝነው ከጥቂት ሳምንታት በፊት የአሜሪካው ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማይክ ፖምፖዮ 'ኒውክሊዬር ማውደም' ዓላማው ካደረገው ውይይት ይውጡሉን ስትል የተሰማችው። ምክንያቷ ደግሞ 'ሰውዬው ዝም ብለው ይቀበጣጥራሉ' የሚል ነው።
ኒውክሊዬር እስከ አፍንጫዋ ታጥቃለች የሚባልላት ሰሜን ኮሪያ አሁን ቢሆንም አውዳሚውን የጦር መሣሪያ ማብላላት አለማቆሟ እየተገነረ ነው።

• ኪም ሌሎች አማራጮችም አሉ ሲሉ አስጠነቀቁ
የሰሜን ኮሪያ መሪ ኪም ጆንግ-ኡን ሌሎች አማራጮችም አሉ ሲሉ አስጠነቀቁ