በዲሞክራቲክ ኮንጎ ከአንድ ሺህ በላይ ሰዎች በኢቦላ ሞቱ

የጤና ባለሙያ በኢቦላ ምክንያት ሕይወቱ ያጣን ግለሰብ ስም በመስቀል ላይ ሲፅፍ Image copyright Reuters

በዲሞክራቲክ ኮንጎ በኢቦላ ወረርሽኝ ምክንያት የሞቱ ሰዎች ቁጥር ከአንድ ሺህ በላይ መድረሱን የሀገሪቱ ጤና ጥበቃ ሚኒስትር አስታወቀ።

በሀገሪቱ እጅግ አደገኛ የተባለለት የኢቦላ ወረርሽኝ ለሁለተኛ ጊዜ የተከሰተው ባለፈው ዓመት ነሐሴ ወር ላይ ነበር።

የዓለም የጤና ድርጅት ምክትል ዳይሬክተር ዶ/ር ማይክል ራያን እንዳሉት ከሆነ በሀኪሞች ላይ እምነት ማጣት እና አመፅ ወረርሽኙ ወደ ሀገሪቱ ምስራቃዊ ክፍል የሚያደርገውን ስርጭት ለመግታት የሚደረገውን ጥረት እክል ውስጥ ጥሎታል።

ዶክተር ራያን አክለውም ከታሕሳስ ወር ጀምሮ በጤና ተቋማት ላይ የደረሱ 119 ጥቃቶች ተመዝግበዋል ብለዋል።

ዓለማችን የኩፍኝ ወረርሽኝ ያሰጋታል

ሕይወት ከኢቦላ ወረርሽኝ በኋላ

አለማችን የኩፍኝ ወረርሽኝ እንደሚያሰጋት አለም አቀፉ ጤና ድርጅት አስጠነቀቀ

የዓለም ጤና ድርጅት ባለሙያዎች የወርሽኙ ስርጭት ሊቀጥል እንደሚችል መተንበያቸውን በጄኔቫ በሰጡት መግለጫ ላይ አስታውቀዋል።

የጤና ባለሙያዎች በርካታ ክትባቶች በእጃቸው ላይ እንደሚገኝ የተናገሩት ኃላፊው፤ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች የህክምና ክትትሉን ጀምረዋል ብለዋል።

ነገር ግን የታጠቁ አማፂያን የሚፈፅሟቸው ጥቃቶች እንዲሁም በሕክምና ባለሙያዎች ላይ እምነት ማጣት የመከላከል ጥረቱን እንዳይጎዳው ዶ/ር ራያን አስታውቀዋል።

"አሁንም የማህበረሰብቡን ቅቡልነትና እምነት የማግኘት ፈተና አለብን" ብለዋል።

በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ በኢቦላ ብቻ ሳይሆን በኩፍኝ ወረርሽኝም ከአንድ ሺህ በላይ ሰዎች ሕይወታቸውን ሲያጡ፤ 50 ሺህ ሰዎች መታመማቸው ተመዝግቧል።

የዓለም አቀፉ ጤና ድርጅት ኩፍኝ በሀገሪቱ ካሉ 26 ግዛቶች በ14ቱ መከሰቱን አስታውቋል። ይህ ደግሞ ከተማና ገጠርን ሳይለይ መሆኑን አስምረውበታል።

ኢቦላ በሀገሪቱ ሁለት ግዛቶች ብቻ የተከሰተ ሲሆን ስርጭቱን ለመግታት ግን ባለው ግጭት ምክንያት አዳጋች ሆኗል። እንደ ዓለም አቀፉ የጤና ድርጅት ከሆነ ወደ ቀሪው የዓለም ክፍል የመሰራጨት እድሉ የመነመነ ቢሆንም የኮንጎ ጎረቤት ሀገራትን ግን ያሰጋል።

ኢቦላ ከ2013 እስከ 2016 በምዕራብ አፍሪካ ሀገራት ተከስቶ ከ 11 ሺህ ሰዎች በላይ መሞታቸው ይታወቃል።

በዚህ ዘገባ ላይ ተጨማሪ መረጃ