የሚንቀለቀል እሳተ ገሞራ ጉድጓድ ውስጥ የገባው አሜሪካዊ ወታደር ተረፈ

ሀዋይ የሚገኘው የእሳተ ገሞራ Image copyright Getty Images
አጭር የምስል መግለጫ ሀዋይ የሚገኘው የእሳተ ገሞራ

አንድ አሜሪካዊ ወታደር 21 ሜትር ጥልቀት ያለው የእሳተ ገሞራ ጉድጓድ ውስጥ ገብቶ ህይወቱ መትረፉ ተሰምቷል።

የ32 ዓመቱ ወታደር ሀዋይ ውስጥ የሚገኘው እሳተ ገሞራ አቅራቢያ የሄደው ለስልጠና ነበር።

እሳተ ገሞራው አናት ላይ ቆሞ ሳለ መሬቱ ከድቶት ጉድጓዱ ውስጥ ወድቋል ተብሏል።

'የእሳተ ገሞራ ቱሪዝም'፡ አፍቃሬ እሳተ ገሞራዎች

እሳተ ገሞራው የሚገኝበት ፓርክ ኃላፊዎች ግለሰቡ ከባድ ጉዳት እንደደረሰበት አሳውቀዋል።

"ነፍስ አድኖች በገመድ ታግዘው ጎትተውታል። የመከላከያ ሚኒስቴር ሄሊኮፕተርም ረድቶናል" የሚል መግለጫ አውጥተዋል።

በሞቃታማውና አሲዳማው የአፋር ክፍል ህይወት ያለው ነገር ተገኘ

ወታደሩ ወደ ጉድጓዱ ከወደቀ በኋላ አንድ የድንጋይ ጠርዝ ላይ አርፎ ባይቆም ኖሮ እሳተ ገሞራው መሀል ላይ ይገባ ነበር።

እሳተ ገሞራው የፈነዳው ባለፈው ዓመት ሲሆን፤ ወደ 700 ቤቶች አውድሟል።

ኪላውያ የተባለው ይህ እሳተ ገሞራ ዓለም ላይ ሁሌም ህያው ከሆኑ እሳተ ገሞራዎች አንዱ ነው።

ተያያዥ ርዕሶች

በዚህ ዘገባ ላይ ተጨማሪ መረጃ