አማዞን ነፍሰ ጡር ሠራተኞቹን ከሥራ በማሰናበት ተከሰሰ

አማዞን

አሜሪካዊቷ ትሠራበት የነበረው አማዞን ነፍሰ ጡር ነሽ ብሎ በማባረሩ ፍርድ ቤት ልትገትረው መሆኑ ተሰማ። አማዞን ባለፉት ስምንት ዓመታት ብቻ ተመሳሳይ ክሶች ሲቀርቡበት ነበር።

ባለፉት ስምንት ዓመታት ተመሳሳይ ክስ ሲያቀርቡ የነበሩ ሴቶች እንደሚሉት፤ ይሠሩበት የነበረው ድርጅት ፍላጎታቸውን ሊያሟሟላቸው ፈቃደኛ አልነበረም።

አማዞን በበኩሉ ምን ሲደረግ ነፍሰ ጡር የሆኑ ሠራተኞቼን አባርራለሁ ሲል ክሱን አስተባብሏል።

ሥራ ቀጣሪና አባራሪ እየሆነ የመጣው ሮቦት

"አማዞን ሠራተኞቹን በማርገዛቸው ብቻ አባረረ የሚለው ክስ ፍፁም ውሸት ነው" ሲል ለቢቢሲ ምላሽ ሰጥቷል።

አክሎም "ድርጅታችን ሁሉንም በእኩል የሚያይ ነው" ብለዋል።

"ሠራተኞቻችን የሚያስፈልጋቸውን የሕክምና እገዛ የምናደርግ ሲሆን፤ ይህ ደግሞ ነፍሰ ጡር ለሆኑ እናቶችም ይሠራል።" በማለት ልጅ ለወለዱ እናቶችም ሆነ አባቶች የወሊድ ፈቃድ እንደሚሰጥም ያስረዳሉ።

ባለፉት ዓመታት ለቀረቡባቸውና ከሕግ ውጪ ስለፈቷቸው ጉዳዮች ግን አስተያየታቸውን ከመስጠት ተቆጥበዋል።

"ዳቪንቺ ሞናሊዛን ያልጨረሰው ስለታመመ ነው"

በቅርቡ የደረሰባትን በደል ወደ ፍርድ ቤት የወሰደችው ቤቨርሊ ሮዜልስ፤ በሰኔ ወር በካሊፎርኒያ ከፍተኛው ፍርድ ቤት ጉዳይዋ ይታያል ተብሏል።

አማዞን ከ613ሺህ በላይ ሠራተኞች ያሉት ሲሆን በገና ሰሞን ብቻ እስከ 100 ሺህ ጊዚያዊ ሠራተኞችን ይቀጥራል።

ማይክሮሶፍት ጽሁፍን የሚያቀል አሠራር ፈጠረ

የአማዞን ሠራተኞች ድርጅታቸው ላይ ተመሳሳይ ቅሬታ ሲያቀርቡ ነበር። ቢቢሲ ያነጋገራትና ስሟ እንዳይገለፅ የጠየቀች እናት እንደተናገረችው፤ ነፍሰ ጡር በነበረች ወቅት ለአለቃዋ እርጉዝ መሆኗን ተናግራ ወደ ሌላ ክፍል እንድትዘዋወር ብትጠይቅም ሳይፈቀድለት ቀርቷል።

ሥራዋ ከባድ ጋሪ መግፋት፣ ከባድ እቃ ማንሳትና ጎንበስ ቀና ማለት ስለሚበዛው ጤናዋ ላይ ችግር ገጥሟት እንደነበር አትረሳም።

አማዞን ግን ማንነታቸውን በግልፅ ስላልተናገሩ ሠራተኞቹ አስተያየት ከመስጠት እንደሚቆጠብ ገልጾ፤ ነፍሰ ጡር መሆናቸውን ካሳወቁ ሠራተኞቹ ጋር በቅርበት እንደሚሠራ ተናግሯል።

በእንግሊዝ የሚገኘው ጂኤምቢ የሠራተኞች ማኅበር ቃል አቀባይ የሆኑት ግለሰብ እንደሚሉት "በአማዞን የሚሠሩ ነፍሰ ጡር እናቶች የሚነግሩን ለ10 ሰዓት ያህል ቆመው እንደሚሰሩ ነው። እንደ አማዞን ያሉ ድርጅቶች ሠራተኞቻቸውን በአግባቡ መያዝ ይጠበቅባቸዋል፤ እንደ ሮቦት ሊያሠሯቸው አይገባም" ብለዋል።

በዚህ ዘገባ ላይ ተጨማሪ መረጃ