በአፋር ታጣቂዎች በከፈቱት ተኩስ አንድ ሰው ገድለው ሌላ አቆሰሉ

የኢትዮጵያ - አፋር ክልል ካርታ

በአፋር ክልል ገዋኔ አካባቢ በባጃጅ ይጓዙ የነበሩ ሰዎች ላይ ተኩስ ተከፍቶ አንድ ሰው መሞቱን የአፋር ክልል የሰላምና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ አሕመድ መሐመድ ለቢቢሲ ገልጸዋል።

ኃላፊው እንደተናገሩት፤ ጥቃቱ የተፈጸመው በባለሦስት ጎማ ተሽከርካሪ (ባጃጅ) ሲጓዙ በነበሩ የግብርና ኮሌጅ መምህራን ላይ ነው። ታጣቂዎቹ በጥቃቱ አንድ ሰው ሲገድሉ ሌላኛውን አቁስለዋል።

የሠላም ተጓዧ ሉሲ (ድንቅነሽ) ምን ደረሰች?

"ታጣቂዎቹ በአፋርና ኢሳ መካከል ግጭት አስነስተዋል ተብለው በመንግሥት እየተፈለጉ ያሉ ናቸው" ሲሉ ኃላፊው ተናግረዋል።

አቶ አሕመድ እንዳሉት፤ ከዚህ ቀደም ታጣቂዎች ገዋኔ ከተማ ገብተው አንድ ሰው ገድለው፤ አንድ ሰው አቁስለዋል። አንድ የስምንት ዓመት ሕፃንም አግተውም ወስደዋል ብለዋል።

ሃላፊው ጨምረውም ከሳምንታት በፊት ለአንድ ሰው ሞት ምክንያት በሆነው በትግራይ ፖሊስ የእግር ኳስ ተጫዋቾች ላይ የተፈጸመው ጥቃትም ከዚሁ ታጣቂ ቡድን ጋር የተያያዘ እንደሆነ አመልክተዋል።

ገዋኔ አካባቢ በርካታ ጥቃቶች እየደረሱ በመሆኑ ምን እየተሠራ ነው ስንል ኃላፊውን ጠይቀናቸው ነበር። መንግሥት በጉዳዩ ክትትል እያደረገ እንደሆነና የጸጥታ ኃይል መሰማራቱንም ገልጸው፤ ሕዝቡን ራሱን እንዲጠብቅም አሳስበዋል።

"የመከላከያ ሚኒስቴርን በተሻለ መልኩ መምራት ይቻላል" ኢንጂነር አይሻ መሀመድ

በአካባቢው በተደጋጋሚ ጥቃት እየተሰነዘረ ስለሆነ የመከላከያ ሠራዊት ጥበቃ እንዲያደረግ መሰማራቱን ገልጸው፤ "ጥቃቱን እየፈፀሙ ያሉት መንግሥት እየፈለጋቸው ያሉ ሰዎች ናቸው" ብለዋል።

ተያያዥ ርዕሶች