ዋትስአፕ ሲጠቀሙ እንዴት ራስዎን ከጥቃት መከላከል እንደሚችሉ ያውቃሉ?

የዋትስአፕ መለያ Image copyright Getty Images

ዋትስአፕን ኢላማ ያደረጉ ጥቃቶች ደረሱ ሲባል 1.5 ቢሊየን የዋትስአፕ ተጠቃሚዎች ይደናገጣሉ።

እርሰዎም "እንዴት የመረጃዎቼን ደህንነት መጠበቅ እችላለሁ?" ብለው ሀሳብ ገብቶዎት ይሆናል።

በተለይ ጋዜጠኛ፣ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ወይም ጠበቃ ከሆኑ ለጥቃቱ ተጋለጭ ነዎት። ዋትስአፕ ሲጠቀሙ መውሰድ ያለብዎትን ጥንቃቄ እንነግርዎታለን።

1. 'አፕዴት' ያድርጉ

በዚህ ሳምንት የኮምፒውተር መረጃ መዝባሪዎች (ሀከርስ) ዋትስአፕን ተጠቅመው የስለላ መተግበሪያ ጭነው እንደነበር ሲሰማ ብዙዎች መደናገጣቸው አልቀረም።

ዋትስአፕ በተደጋጋሚ መልዕክት ማጋራትን አገደ

ጥቃቱ እንደደረሰ የታወቀው በዚህ ወር መባቻ ላይ ሲሆን፤ የፌስቡክ የደህንት ሰዎች እንዳሉት የስለላ መተግበሪያውን መጫን የተቻለው የዋትስፕ የድምፅ ጥሪን በመጠቀም ነበር።

ዋትስአፕ ጥቃቱ መድረሱን እንዳወቀ ተጠቃሚዎች የዋትስአፕ መተግበሪያ በድጋሚ እንዲጭኑ (አፕዴት እንዲያደርጉ) ጠይቆ ነበር።

እርስዎም ራስዎን ለመከላከል የዋትስአፕ መተግበሪያዎትን አዘውትረው 'አፕዴት' ማድረግ አለብዎት።

በዋትስአፕ የሚላላኩትን መልዕክት ከእርሰዎና ከመልዕክት ተቀባዩ ውጪ ማየት ባይቻልም፤ ሀከሮች ኢላማ የሚያደርጉት የሚለዋወጡትን መልዕክት ነው። ስለዚህም 'አፕዴት' በማድረግ ራስዎን መከላከል አይዘንጉ።

2. 'ባክ አፕ' ሲያደርጉ ይጠንቀቁ

ዋትስፕ ላይ የሚላላኩት መልዕክት በእርስዎና በተቀባዩ መካከል የሚጠበቅ ቢሆንም፤ መልዕክቶቹ ወደጉግል ድራይቭ እንዲሸጋገሩ 'ባክ አፕ' ካደረጉ ክፍተት ይፈጠራል።

'ባክአፕ' የሚደረግ መልዕክትን ደህንነት ዋትስአፕ አይጠብቅም። ስለዚህ አንድ ሰው ወደጉግል ክላውድዎ መድረስ ከቻለ መልዕክቶቹን ያገኛቸዋል።

'ዋትስአፕ' በቻይና እክል ገጥሞታል

የሚለዋወጡትን መልዕክት መጠበቅ ከፈለጉ ዋትስአፕ መልዕክቶችዎን 'ባክአፕ' እንዳያደርግ ይዘዙ።

'ሴቲንግ' ውስጥ ገብተው 'ቻት ባክአፕ' የሚለውን ማጥፋት ይችላሉ።

3. 'ቱ ፋክተር አውተንቲኬሽን'

Image copyright Getty Images

'ቱ ፋክተር አውተንቲኬሽን' የመረጃዎትን ደህንነት መጠበቅ የሚችሉበት መንገድ ነው።

ዋትስአፕን ጨምሮ የተለያዩ መተግበሪያዎችን ለመጠቀም የሚሞክሩ ሰዎችን ትክክለኛ ማንነት ለማወቅ የሚረዳ መንገድ ነው።

በሞባይልዎ የኢንተርኔት ወጪ ተማረዋል?

ተጠቃሚዎች መጀመርያ ላይ ስማቸውን ይጽፉና የይለፍ ቃል (ፓስወርድ) ያስገባሉ። ወደተንቀሳቃሽ ስልክ በሚላክ መልዕክት የግለሰቡን ማንነት ማረጋገጥም ይቻላል።

4. ዋትስአፕዎን ይቆጣጠሩ

ዋትስአፕና ሌሎችም መተግበሪያዎች ደህንነትዎን የሚጠብቁበት አሠራር አላቸው። ዋትስፕ ላይ 'ሴቲንግ' ውስጥ ገብተው 'አካውንት' የሚለውን ከመረጡ በኋላ የተለያዩ አማራጮች ያገኛሉ።

ወደ ድብቁ የዋትስአፕ መንደር ስንዘልቅ

'ላስት ሲን' ዋትስአፕ የተጠቀሙበትን የመጨረሻ ሰአት ማሳወቅ ወይም መደበቅ የሚችሉበት አማራጭ ነው። ፎቶዎ ወይም ያሉበትን ቦታ ማሳወቅና መሸሸግም ይችላሉ።

የመረጃዎትን ደህንነት ለመጠበቅ ከሚረዱ መንገዶች አንዱ የሚልኩትን መልዕክትና የዋትስአፕ እንቅስቃሴዎን የሚያዩ ሰዎችን መምረጥ የሚችሉበት አሠራር ነው።