የትራምፕ አሜሪካ በኢትዮጵያውያን ላይ እያደረሰ ያለው ተፅእኖ ምንድን ነው?

ኢትዮጵያውያን በአሜሪካ Image copyright The Washington Post

ከምርጫ ቅስቀሳቸው ጀምሮ የስደተኞችን ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ ለመቀነስ ቃል እየገቡ የመጡት ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከትላንት በስትያ ብዙዎች አግላይ ያሉትን ንግግር አድርገዋል።

በንግግራቸው ከዚህ በኋላ አሜሪካ የምትቀበላቸው ስደተኞች "ወጣት፣ የተማሩና እንግሊዝኛ ቋንቋ የሚችሉትን ነው" ብለዋል። የስደተኞች የጥገኝነት ጥያቄ ተቀባይነት የሚያገኘው አቅማቸው ታይቶ ሲሆን፤ የአሜሪካን የሥነ ዜጋ ትምህርት ተፈትነው ማለፍ እንደሚኖርባቸውም ገልፀዋል።

የኢትዮጵያና አሜሪካ የተለየ ግንኙነት እስከምን ድረስ?

የዓለምፀሐይ፣ የፍስሃ እና የካሳሁን አዲስ ተስፋ

ብዙዎች ይህን ንግግራቸውን "ዘረኝነት የተሞላበት"፤ "ፀረ ስድተኛና ፀረ-ጥቁር ነው" ሲሉ ተደምጠዋል።

በብዙ ሃገራት ተቀባይነት ያለው የተባበሩት የመንግሥታት የስደተኞች ድርጅት ኮንቬሽን፤ ጦርነት፣ መፈናቀል፣ ግድያንና ሌሎችም ችግሮችን ፈርተው የሚሰደዱ ሰዎች በሦስተኛ አገር ነፃነታቸው ተጠብቆ ሊኖሩ እንደሚገባ ቢያትትም፤ ፕሬዚዳንት ትራምፕ በንግግራቸው ይህንን ሰብአዊ መብት እየጣሱት መሆኑን ብዙዎች ይተቻሉ።

ከነዚህም ውስጥ ትውልደ ሶማሊያዋ የኮንግረስ አባል ኢልሃን ኦማር ትገኝበታለች። "ጥገኝነት ለሚጠይቁ ግለሰቦች ጀርባችንን ልንሰጣቸው አይገባም። የትራምፕ ንግግር በጣም ተስፋ አስቆራጭ ነው። በተለይም ከፍተኛ ፈተናን አምልጠው፣ አዲስ ተስፋን ሰንቀው የሚመጡ ሰዎች ላይ እንዲህ አይነት ንግግር ማድረጋቸው ሀዘኔን የበለጠ ይጨምረዋል። ምክንያቱም እኔም ከነሱ አንዷ ነበርኩ" ብላለች።

"ውሳኔው የአሜሪካ እና የኢትዮጵያን የጋራ ጥቅም ከግምት ውስጥ ያስገባ አይደለም" ዶ/ር ነገሪ ሌንጮ

የኢልሃንን ሀሳብ ተጋርተው የፕሬዚዳንቱ ንግግር አግላይና ዘረኛ ነው የሚሉት በአትላንታ የኢሚግሬሽን የሕግ ባለሙያ የሆኑት አቶ ማንችሎት ገበየሁ ጓዴ ናቸው።

ነገር ግን ይህ ንግግራቸው ፖሊሲ ወይም ሕግ ሳይሆን ለዋይት ሃውስ የሕግ አቅጣጫ ማሳያ የሚሆን ነው ይላሉ። የትራምፕ ንግግር ወደሕግነትና ፖሊሲነት የመቀየር አቅሙ ዝቅተኛ እንደሆነም የሕግ ባለሙያው ያስረዳሉ።

ትራምፕ የስደተኞችን ቁጥር ለመቀነስ በተደጋጋሚ ውሳኔ ቢያሳልፉም በተለያዩ ምክንያቶች ሳይተገበሩ ቀርተዋል። እንደምሳሌ በርካታ ሙስሊሞች የሚኖሩባቸው ሀገራት ላይ ገደብ መጣል ይጠቀሳል። ምንም እንኳን አንዳንዶቹ ውሳኔዎች ኮንግረስ ላይ ቢቀርቡም፤ ኮንግረሱ ሳያሳልፋቸው እንደቀሩ የሕግ ባለሙያው ይናገራሉ።

"በአስቸኳይ አዋጅ አውጀው ፍርድ ቤት የገደባቸው ውሳኔዎችም አሉ። ስለዚህ ፕሬዚዳንት ትራምፕ ያወሯቸውን ነገሮች ለመተግበር ጥረት ቢያደርጉም፤ አፈፃፀሙን በተመለከተ ወደሕግነትና ፖሊሲነት ተቀይሮ ተግባር ላይ እንዳይውል በተለያየ መንገድ ውድቅ ሆኗል" ይላሉ።

"የእስላማዊ ፍርድ ቤቶች ኅብረትን እናጠፋለን ብለን አልሸባብን ፈጠርን"

Image copyright Tom Williams

አቶ ማንችሎት ለዚህ እንደምክንያትነት የሚጠቅሱት በአሜሪካ የሕግ መወሰኛው ምክር ቤት ሴኔቱ ሪፐብሊካኖች ሲሆኑ፤ ኮንግረሱን የሚቆጣጠሩት ደግሞ ዴሞክራቶች መሆናቸውን ነው።

"ሕጉን የማሻል አቅማቸው በጣም ደካማ ነው። ሪፐብሊካኖችንና ዴሞክራቶችን የማሳመን ሥራ መሥራት አልቻሉም። በአስቸኳይ ጊዜ እንዲሁም የሥራ አስፈፃሚነት ኃይላቸውን ተጠቅመው ሲያዙም፤ ፍርድ ቤቶች ወዲያው ስለሚያግዱባቸው ያን ያህል የተለየ ነገር ይመጣል ብዬ አልጠብቅም" ሲሉ ያስረዳሉ።

የታሪክ መማሪያ መጻሕፍት ለምን ይከለሳሉ?

ሆኖም የፕሬዚዳንቱ ንግግር እንደቀላል መወሰድ እንደሌለበት አቶ ማንችሎት ይናገራሉ። በተለይም አሜሪካ ካላት የምጣኔ ሀብትና የጦር ኃያልነት ጋር ተያይዞ ስደተኞች የሚመጡባቸው አገሮችን መጠለያ ላፍርስ ቢሉ ተቀባይነት ሊኖራቸው እንደሚችል አቶ ማንችሎት አልደበቁም።

በተለይም ዓለም አቀፉ ሕግ የሀብታም አገራት ፍላጎት ማስፈፀሚያ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ፤ ትራምፕም የሁለትዮሽ ግንኙነትን በመጠቀም ሀሳባቸውን ሊያሳኩ እንደሚችሉ የሕግ ባለሙያው ጠቆም አድርገዋል።

የሕግ ባለሙያው እንደማስረጃ የሚያነሱት ፕሬዚዳንቱ በተደጋጋሚ ያደረጉት ንግግር ከነጭ ማኅበረሰቡ ውጭ ያለውን ጥቁርም ሆነ ሌሎች ማኅበረሰቦችን የሚቃወም ቢሆንም ከመተቸት አልፎ በፕሬዚዳንት ትራምፕ ላይ አሉታዊ ተፅእኖ የሚወስድ መንግሥት እስካሁን አለማየታቸውን ነው።

ኢትዮጵያ ሀይቆቿን መጠበቅ ለምን ተሳናት?

"ኬንያ የሚገኘውን የስደተኞች ካምፕ አፈርሳለሁ ቢሉ አቅም ከመኖር የሚመነጭ ስለሆነ የኬንያ መንግሥት ሊተባበራቸው ይችላል። ስለዚህ አንዳንድ አገሮች ከአሜሪካ የሚያገኙትን ድጋፍ ታሳቢ በማድረግ የፕሬዚዳንት ትራምፕን ንግግርና ተፅእኖ ተግባራዊ ሊያደርጉ ይችሉ ይሆናል" ይላሉ።

ፕሬዚዳንቱ የሥራ አስፈፃሚነት ኃይላቸውን የሚጠቀሙ ከሆነ በተለያዩ አገራት ያሉ ስደተኞችን በዛው መገደብ እንዲሁም በመጠረዝ ሊመልሷቸው እንደሚችሉ በመጠቆም፤ በዚህ ሂደትም ብዙ ኢትዮጵያውያን ሊጎዱ እንደሚችሉ ይናገራሉ።

"ማህበሩ የማያልፈው ቀይ መስመር የስራ ማቆም አድማ ነው"-ዶ/ር ገመቺስ ማሞ የኢትዮጵያ ህክምና ማህበር ፕሬዚዳንት

በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ ወደአሜሪካ የሚሄጡ ኢትዮጵያውያን ላይ ከፍተኛ ተፅእኖ እያደረሰ መሆኑንም አቶ ማንችሎት ያስረዳሉ።

በብዙዎች ዘንድ እንደገነት ወደምትቆጠረው አሜሪካ ለመሄድ ግለሰቦች ከቤት ባለቤትነት ጀምሮ፣ ንብረታቸውንና ላለመቅረታቸው የተለያዩ ማስረጃዎች ማቅረብ የሚጠበቅባቸው ሲሆን፤ ፕሬዚዳንት ትራምፕ ከመጡ በኋላ 'ቬቲንግ' (የማጣራት ሂደቱ) ወይም ቪዛ የማግኘት ሂደቱ ጠበቅ ማለቱን አቶ ማንችሎት ገልፀዋል።

ለዚህ ምክንያቱ ደግሞ ቀጥተኛ ሕግ ባይኖርም የተለያዩ አገራትን ኤምባሲ የሚቆጣጠረው የፕሬዚዳንት ትራምፕ ዋይት ሃውስ መሆኑ ነው።

በአጠቃላይ በተለያየ ምክንያት ወደአሜሪካ በሚሄዱ ሰዎች ላይ ክልከላው እንደጨመረ ነው።

ትራምፕ ፕሬዚዳንት ከመሆናቸው በፊት ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ግለሰቦች ወደአሜሪካ ያቀኑ የነበረ ቢሆንም አሁን ካለው አሠራር ጋር ተያይዞ ብዙ ገደቦች እንደተጣሉ ነው።

አቶ ማንችሎት እንደ ምሳሌ የሚያነሱት በትራምፕ አሜሪካ በጋብቻ የሚሄዱ ሰዎች ጋብቻቸው የውሸት ነው ተብሎ ስለሚታሰብ ተጋቢዎች የተለየ ማስረጃ ማቅረብ እንደሚኖርባቸው ነው።

በደቡብ ሱዳን የምሽት ክለቦች ታገዱ

"ኢትዮጵያ ውስጥ ባሉ ጋብቻዎች አንድ ሰው ሕጉ የሚፈቅደውን ማስረጃ ከማቅረብ በተጨማሪ ጋብቻው የእውነት መሆኑን የማስረዳት ሸክም ይኖርበታል" ይላሉ።

በዚህም መሰረት ፕሬዚዳንት ትራምፕ ስልጣን ከያዙ በኋላ ቤተሰብን ማምጣት፣ ሚስት ማምጣት፣ ልጅ ማምጣት የሚባለው ሂደት በጣም ጥብቅ ስለሆነ አንድ ዓመት ይወስድ የነበረው ሂደት ሁለት ዓመት እንደሚወስድም ያስረዳሉ።

"የኢትዮጵያ የህክምና ታሪክ አልተጠናም" ዶክተር አሰፋ ባልቻ

ከዚህ ሁሉ በላይ ከፍተኛ ተፅእኖ እያደረሰ ያለው ፕሬዚዳንት ትራምፕ ስልጣን ከመቆናጠጣቸው በፊት በተለያየ ምክንያት የሚሄዱ ኢትዮጵያውያን የጥገኝነት ጥያቄያቸው በቀላሉ ተቀባይነት ያገኝ የነበረ ሲሆን፤ አሁን ግን የማጣራት ሂደቱ ረዥም ጊዜ እየወሰደ ስለሆነ ተቀባይነት የሚያገኙ ስደተኞች ቁጥር መመናመኑን አቶ ማንችሎት ገልፀዋል።

"ብዙዎች ተጠርዘዋል፤ ወደአሜሪካ ትሄዳላችሁ የተባሉ ስደተኛች እንደገና የማጣራቱን ሥራ እያራዘሙባቸው ነው" ይላሉ።

ተያያዥ ርዕሶች