ጀርመን ከናሚቢያ የወሰደችውን መስቀል ልትመልስ ነው

በርሊን ሙዝየም የሚገኘው የናሚቢያ ቅርስ Image copyright AFP/Getty

ጀርመን በቅኝ ግዛት ወቅት ከናሚቢያ የወሰደችውን የመስቀል ቅርጽ ልትመልስ እንደሆነ የጀርመን የታሪክ ሙዚየም አሳውቋል። በ15ኛው ክፍለ ዘመን ከድንጋይ የተሰራው መስቀል በደቡብ ምስራቅ አፍሪካ የተጓዦች ምልክት ነበር።

ተፅዕኖው እስከ አሁን የዘለቀው የባህል ቅኝ ግዛት

ናሚቢያ ቅርሱ እንዲመለስላት የጠየቀችው ባለፈው ዓመት ሲሆን፤ መስቀሉ ጀርመን፣ በርሊን የሚገኝ ሙዝየም ውስጥ ተቀምጧል። ሙዝየሙ መስቀሉን የፊታችን ነሀሴ ለናሚቢያ እንደሚያስረክብ አሳውቋል።

ጀርመን ቀድሞ ቅኝ ከገዛቻቸው አገሮች የተወሰዱ ቅርሶችና የሰዎችን ቅሪተ አካል ለየባለቤቶቻቸው ለመመለስ ቃል መግባቷ ይታወሳል።

ለነፃነት በተደረገ የተቃውሞ ሰልፍ ካሜሮናውያን ህይወታቸውን አጡ

የጀርመን ባህል ሚንስትር ሞኒካ ግሩተርስ፤ ጀርመን ለናሚቢያ መስቀሉን ለመመለስ መወሰኗ በቅኝ ግዛት ዘመን የተፈጸመችውን ጥፋት ለማመን ዝግጁ መሆኗን ያሳያል ብለዋል።

በጀርመን የናሚቢያ አምባሳደር አንድሬስ ጉቤብ፤ የቀደመው የቅኝ ግዛት ታሪክ ያሳደረውን ተጽዕኖ ለመጋፈጥና ወደፊት ለመራመድም የሚያግዝ ተግባር ነው ብለዋል።

"ቻይና በአፍሪካ ውስጥ የታይታ ፕሮጀክት የላትም" ፕሬዚዳንት ሺ ዢፒንግ

3. 5 ሜትር ርዝመት ያለውን መስቀል ፓርቹጋላዊው አሳሽ ዲዮጉ ካዮ እንደተከለው ታሪክ ያትታል። እንደ ጎርጎሮሳውያኑ አቆጣጠር በ1893 የጀርመን የባህር ኃይል ኮማንደር መስቀሉን ወስደውታል።

በርካታ የአፍሪካ አገራት በቅኝ ግዛት ወቅት ተዘርፈው አሁን የአውሮፓ ሙዝየሞች ውሰጥ የሚገኙ ቅርሶቻቻው እንዲመለሱ እየጠየቁ ነው።

የእየሱስ ትክክለኛ ገፅታ በታሪክ አጥኚዎች አይን

የፈረንሳይ ፕሬዘዳንት ኢማኑኤል ማክሮን፤ 26 ዘውድና ቅርጸ ቅጾችን ለቤኒን እንደሚመለሱ መናገራቸው ይታወሳል። የእንግሊዝ ሙዝየሞችም የተሰረቁ ቅርሶችን ለመመለስ መወሰናቸውን ይፋ አድርገዋል።

በእንግሊዝ ሀገር በሚገኘው የብሔራዊ ጦር ሙዝየም ይዞታው ሥር የቆየው የአፄ ቴዎድሮስ ቁንዳላ በቅርቡ ለኢትዮጵያ መመለሱ ይታወሳል።

ተያያዥ ርዕሶች