የአትሌቲክስ ቡድን ሀኪም 177 አትሌቶች ላይ ወሲባዊ ጥቃት አድርሷል ተባለ

ሀኪሙ 177 አትሌቶች ላይ ወሲባዊ ጥቃት አድርሷል Image copyright Getty Images

አሜሪካ፣ 'ኦሀዮ ስቴት ዩኒቨርስቲ' ውስጥ የሚገኝ የአትሌቲክስ ቡድን ሀኪም 177 አትሌቶች ላይ ወሲባዊ ጥቃት ማድረሱ ተገለጸ።

ዩኒቨርስቲው ባደረገው ምርመራ፤ ሀኪሙ እንደጎርጎሮሳውያኑ አቆጣጠር ከ1979 እስከ 1997 177 ወንድ ተማሪዎች ላይ ወሲባዊ ጥቃት ማድረሱ ተረጋግጧል።

ዶክተሩ 1998 ላይ በጡረታ ከሥራ ከተገለለ በኋላ 2005 ላይ ራሱን አጥፍቷል።

ሀኪሙ ተማሪዎችን ይጎነትል ነበር፤ በ16 አይነት ዘርፍ ያሰለጥናቸው ለነበሩ አትሌቶች "ምርመራ አደርጋለሁ" በሚል ሽፋንም ጥቃት ያደረስም ነበር ተብሏል።

የአሜሪካ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዕጩ ወሲባዊ ጥቃት አላደረስኩም አሉ

የዩኒቨርስቲው ተማሪዎች ጥቃት እየደረሰባቸው እንደሆነ ለተቋሙ ቢያስታውቁም አንዳችም እርምጃ አልተወሰደም።

ምርመራውን ያደረጉት ግለሰቦች ይፋ ባደረጉት ሪፖርት፤ ሀኪሙ በዩኒቨርስቲው የመታጠቢያ ክፍል፣ የፈተና ክፍልና ሌሎችም ቦታዎች ጥቃት ያደርስ እንደነበር ተመልክቷል።

ፖፑ የካቶሊክ ቄሶች ሴት መነኮሳትን የወሲብ ባሪያ ማድረጋቸውን አመኑ

ብዙ አትሌቶች "አላስፈላጊ የመራቢያ አካል ምርመራ ተደርጎብናል" በማለት ለተቋሙ አሳውቀው ነበር። ይደርስባቸው የነበረው ጥቃት የአደባባይ ሚስጥር ቢሆንም ዩኒቨርስቲው ሀኪሙ ላይ እርምጃ አልወሰደም።

የዩኒቨርስቲው ፕሬዝዳንት ማይክል ድሬክ "በተፈጠረው ነገር አዝነናል" ብለዋል።

ፕሬዘዳንቱ ወሲባዊ ጥቃቱ የደረሰው ከሀያ ዓመታት በፊት በመሆኑ የዩኒቨርስቲውን ነባራዊ ሁኔታ አያሳይም ብለዋል። ሆኖም የዩኒቨርስቲው የቀድሞ ተማሪዎች ክስ ያቀረቡ ሲሆን፤ ተቋሙ ለደረሰው ጥቃት ኃላፊነት እንዲወስድ ጠይቀዋል።

ወሲባዊ ትንኮሳን የሚከላከል ካፖርት ተፈለሰፈ

የቀድሞው የኦሀዮ ስቴት ዋናተኛ ኬንት ኪልጎር "የብዙዎች ህልም ተቀጭቷል። በደረሰብን ጉዳት ሳቢያ ሰው ለማመን እንቸገራለን። ልጆቻችንን አብዝተን ስለምንቆጣጠርም ከልጆቻችን ጋር ያለን ግንኙነት የሻከረ ነው" ብለዋል።