ባንግላዲሽ ለ65 ቀናት አሳ ማጥመድ ከለከለች

አሳ አስጋሪ ያጠመዳቸውን አሶች ተሸክሞ ወደ ገበያ ሲሄድ Image copyright Getty Images

ባንግላዲሽ በውቂያኖስ ዳርቻዎች ለ65 ቀናት አሳ ማጥመድ ከለከለች። ክልከላው የተጣለው የአሳ ምርት በማሽቆልቆሉ መሆኑ ተነግሯል።

የባንግላዲሽ ባለስልጣናት ለቢቢሲ እንዳሉት፤ እገዳው ማንኛውም በአሳ ማስገር ተግባር ላይ የተሰማሩ ጀልባዎችን ያካትታል። ከትናንት ጀምሮ የባህር ዳርቻዎቹ ጠባቂዎች እገዳውን ማስፈፀም ጀምረዋል።

መንግሥት እገዳው የሚቆይባቸው ስልሳ አምስት ቀናት የአሳዎቹ የመራቢያ ወቅት ናቸው ቢልም፤ በሺዎች የሚቆጠሩ አሳ አጥማጆች "ያለ ገቢ ምንጭ እንቀራለን" በማለት የተቃውሞ ሰልፍ ለማካሄድ አስበዋል።

ከጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ ጋር ማዕድ የቀረቡት ምን ይላሉ?

ባለ ዲግሪዋ ቆሎ ሻጭ፤ የህወሐት የቀድሞ ታጋይ ብርሃ አፅብሃ

"እምቦጭን ለማጥፋት የመጡት ጢንዚዛዎች አልጠፉም"

"ይህን ሀብት በአግባቡ ካልተጠቀምንበት መመናመኑ አይቀርም" ያሉት የአሳ እና የእንስሳት ሚኒስትሩ አሽራፍ አሊ ካህን ካስሩ፣ "አሳዎች እንዲራቡና እንዲያድጉ ልናደርግ ይገባል፤ አለበለዚያ ወደፊት ማጣፊያው ሊያጥረን ይችላል" ብለዋል።

ከዚህ ቀደም ለንግድ ማስገር ታግዶ የነበረ ሲሆን፤ አሁን ግን ማንኛውም በማጥመድ ሥራ ላይ የተሰማራ ጀልባና ትንንሽ አሳ አጥማጆችም ለረዥም ጊዜ ታግደው መቆየታቸው እርምጃውን ለየት አድርጎታል።

መንግሥት በየዓመቱ በዚህ ወቅት እገዳው ይጣላል ሲል አስታውቋል።

የአሳ አስጋሪዎች ማኅበር በበኩሉ፤ ጠቅላይ ሚኒስትሩ እገዳውን ዳግም እንዲያጤኑት የጠየቁ ሲሆን ካሳ እንደሚጠይቁም ገልፀዋል።

ተያያዥ ርዕሶች