ሁዋዌ የተጣለበት እገዳ የስልኩ ተጠቃሚዎች ላይ ተጽዕኖ ያሳድራል?

አንድሮይድ ሁዋዌ Image copyright Reuters

ሁዋዌ የቅርብ ጊዜ ሥራዎቹን ለማስተዋወቅ የተለየዩ አገራት ጋዜጠኞችን ወደለንደን ቢጋብዝም፤ ጉግል የጣለበት እገዳ በምርቶቹ ላይ ተጽዕኖ ሊያሳድር ይችላል።

ከአሜሪካ ጋር ያለውን እሰጥ አገባ ተከትሎ ሁዋዌ የአንድሮይድ መተግበሪያን እንዳይጠቀም ጉግል ማገዱ ይታወሳል።

የጉግል ተቋም አንድሮይድ ስልክ በማምረት በዓለም ሁለተኛ ከሆነው ሁዋዌ ጋር እስከወዲያኛው ተቆራርጦ መቅረት የሚፈልግ አይመስልም። ጉግል፤ ከግማሽ ቢሊየን በላይ ተጠቃሚዎች ላሉት ሁዋዌ ዳግም ፍቃድ እንዲሰጥ የአሜሪካ ኢንዱስትሪና ደህንነት ቢሮ ማዘዝ ይችላል።

ሁዋዌ አንድሮይድን እንዳይጠቀም ገደብ ተጣለበት

ሆኖም በሁለቱ አካላት መካከል እርቅ ካልወረደስ?

አሜሪካዊው ጉግል ከሁዋዌ ጋር የነበረውን የንግድ ልውውጥ ቢያቆምም፤ ሁዋዌ ሁሉንም የአንድሮይድ አገልግሎት አያጣም። ምክንያቱም ማንኛውም አምራች ያለፍቃድ መተግበሪያውን አሻሽሎ መጠቀም ይችላል።

ቢሆንም ጉግል እንደ 'ፕሌይ አፕ ስቶር' እና 'ጂሜል' ያሉ መገልገያዎችን ስለሚቆጣጠር ያለጉግል ፍቃድ መሥራት ፈታኝ ይሆናል።

የሁዋዌ ተጠቃሚዎች ላይ ተጽእኖ ያሳድራል?

የሁዋዌ ወይም ኦነር ስልክ ተጠቃሚዎች የጉግል መተግበሪያዎችን ጭነው እየተጠቀሙ ስለሆነ አገልግሎቱ አይቋረጥባቸውም።

የሁዋዌ ባለቤት ልጅ ካናዳ ውስጥ ታሠረች

ጉግል በሁዋዌ በኩል ማለፍ ሳያስፈልገው አዳዲስ ምርቶቹን ለሁዋዌ ስልክ ተጠቃሚዎች ማቅረብ ይችላል። ነገር ግን ደህንነት የሚጠብቁ መተግበሪያዎችን የተሻሻለ ምርት ለመጫን (አፕዴት ለማድረግ) አስቸጋሪ ይሆናል።

በቀድሞው አሠራር ጉግል እነዚህን ማሻሻያዎች ለአንድሮይድ አምራቾች ከሰጠ በኋላ ወደተጠቃሚዎች ያደርሷቸዋል። አንድሮይድ አምራቾች ማሻሻያውን ከጉግል የሚያገኙት ከወር በፊት ሲሆን፤ ለተጠቃሚዎች ምቹ መሆኑንና ከሌሎች መተግበሪያዎች ጋር አለመጣረሱን ማጣሪያ ጊዜም ይሰጣቸዋል።

አሁን ግን ሁዋዌ ማሻሻያዎቹ ከመተግበራቸው በፊት መረጃ አያገኝም። ስለዚህም ተጠቃሚዎቹ የሚያስፈልጋቸውን ማሻሻያ ሳያደርግ ለቀናት ወይም ሳምንታት ሊቆይ ይችላል።

ሁዋዌ ለመግዛት ያሰቡ ተጠቃሚዎችስ?

ከዚ በኋላ ሁዋዌ ስልክ ለመግዛት ያሰቡ ግለሰቦች በሚሸምቱት ስልክ ላይ እንደ 'ዩ ቲዩብ'፣ 'ጉግል ማፕ' እና 'ጉግል ፎቶስ' ያሉ የጉግል አገልግሎቶችን አያገኙም።

አሜሪካ ሁዋዌ እና የፋይናንስ ኃላፊዋን ከሰሰች

ሌሎች መተግበሪያዎችን ከተለያዩ ገጾች መጫን ቢችሉም፤ ጉግል ፍቃድ የሌላቸው ስልኮችን ተጠቅሞ ምርቶቹን መጠቀምን ያግዳል።

ስልኩ ላይ የተጫኑት ሌሎች መተግበሪያዎችም የጉግልን አገልግሎት ማግኘት ስለማይችሉ፤ መተግበሪያዎቹ የሚሰጡት ጥቅም ይወሰናል።

ሚሻል ራሀማን የተባሉ ባለሙያ እንደተናገሩት፤ ትዊተርን ጨምሮ በጉግል 'ኖቲፊኬሽን' የሚላኩ መተግበሪያዎች መጠቀም አይቻልም። ገመድ አልባ የድምጽና ምስል ስርጭትን ማግኘትም አይችሉም።

ሁዋዌ አሁን እየተጠቀመበት ካለው አንድሮይድ ማለፍ አይችል ይሆናል የሚሉ አሉ። ይህም ከሌሎች ስልክ አምራች ድርጅቶች ጋር እንዳይወዳደር ምክንያት ሊሆን ይችላል።

እንደ ሁዋዌና ሳምሰንግ ያሉ ስልክ አምራቾች ማሻሻያዎች ለሕዝብ ይፋ ከመደረጋቸው በፊት ስለሚሰጣቸው፤ የመፈተሽና ከራሳቸው ምርት ጋር የማጣጣም ጊዜ ያገኛሉ።

ሚሻል ራሀማን "ሁዋዌ ከሌሎች ስልክ አምራች ድርጅቶች ዘግይቶ ማግኘቱ ተጽእኖ ያሳድርበታል" ይላሉ።

አምስት ካሜራ ያለው ተንቀሳቃሽ ስልክ

ምን ተሻለ?

ሁዋዌ ለቢቢሲ እንደገለጸው ከአንድሮይድ ጋር መሥራት ቢሻም ካልተቻለ ሌሎች አማራጮች ይጠቀማል።

የሁዋዌ የእንግሊዝ ቢሮ ምክትል ፕሬዘዳንት ጀርሚ ቶምሰን "በነገሩ ሁዋዌ ደስተኛ አይደለም። ነገር ግን እንወጣዋለን። ሌላ አማራጭ የምንዘረጋበት መንገድ አለን። ተጠቃሚዎቻችንን ያስደስታል ብለን እናምናለን" ብለዋል።

ውሳኔው ቻይና ውስጥ የሚገኙ የሁዋዌ ተጠቃሚዎችን እምብዛም አይጎዳም። ምክንያቱም ቻይና ውስጥ የሚጠቀሙባቸው ለቻይና ተብለው የተሠሩ እንደ 'ዊ ቻት' ያሉ መተግበሪያዎች ከሌላ መተግበሪያ ጋር አይጋጩም።

ታጣፊው የሳምሰንግ ስልክ የ'ስክሪን' መሰበር ወቀሳ ቀረበበት

ሆኖም በሌሎች ሀገሮች የሁዋዌ ምርትን መጠቀም ከባድ ይሆናል።