እንግሊዝ፡ አንዲት ሴት መደብር ውስጥ ወለደች

የ21 ዓመቷ እንግሊዛዊት ካይል ሀጀር መገበያያ ውስጥ ሳለች ልጅ መውለዷ ተሰምቷል Image copyright Vivienne Hagger

የ21 ዓመቷ እንግሊዛዊት ካይል ሀጀር መደብር ውስጥ ሳለች ልጅ መውለዷ ተሰምቷል። ካይል ወንድ ልጅ የተገላገለችው በመገበያያ የሚገኝ መጸዳጃ ቤት ውስጥ ነበር።

ብዙዎች የተገረሙት ካይል መጸዳጃ ውስጥ ገብታ ምጧ እስኪመጣ ድረስ እርጉዝ መሆኗን ባለማወቋ ነው። ሀኪሞች በቦታው ከመድረሳቸው በፊት የመደብሩ ሠራተኞች እናቲቱን እየተንከባከቡ ነበር።

ሰማይ ላይ ወልዳ አሥመራ የምትታረሰው ኢትዮጵያዊት

የካይል እናት እንዳሉት፤ የሁለት ልጆች እናት የሆነችው ካይል እርጉዝ መሆኗን ስለማታውቅ የልጅ ልብስ አላዘጋጀችም ነበር። የመደብሩ ሠራተኞች ለካይል የልጅ ልብስ ሰጥተዋታል።

መገበያያ ውስጥ የነበሩ ሰዎችም እሷን ለመርዳት አላቅማሙም። ካይልም "ተአምራዊ ቀን" ስትል እለቱን ገልጻዋለች።

እናት አልባዎቹ መንደሮች

ካይል በፌስቡክ ገጿ ትብብር ያደረጉላትን ሰዎች በአጠቃላይ አመስግናለች። "መታቀፊያ፣ ልጅ ማጠቢያና ሌላም መገልገያ የሰጣችሁኝን አመሰግናለሁ፤ እኔም ልጄም በጣም ደህና ነን" ብላለች።

የመገበያያ መደብሩ ባለቤት ቶኒ ብራውን፤ ካይሊን ያዋለዷት ሠራተኞችን አመስግነዋል። መደብራቸው ውስጥ ልጅ ሲወለድ የመጀመሪያው ባይሆንም፤ ከሌሎች እናቶች በተለየ የካይል አስገርሟቸዋል።

ተያያዥ ርዕሶች