ምርጫው በተያዘለት ጊዜ እንደሚካሄድ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ገለፀ

ወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳ

ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በቀጣይ ለሚደረገው ምርጫ ያስፈልገኛል ያለውን 3.7 ቢሊዮን ብር ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የበጀት ኮሚቴ መጠየቁን የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳ ዛሬ በሰጡት መግለጫ ተናግረዋል።

ወጪው ከህዝብ ቁጥር መጨመርና አንዳንድ ምክንያቶች ጋር ተያይዞ ከዚህ በፊት ከነበሩት ምርጫዎች ጋር ሲወዳደር ከፍተኛ መሆኑን የተናገሩት ወ/ት ብርቱካን ከዚህም ውስጥ 900 ሚሊዮን ብር ከአጋር ድርጅቶች ለማግኘት ታቅዷል።

የቦርዱ ማሻሻያና የብርቱካን ሹመት ምንና ምን ናቸው?

ከቀጣዩ ምርጫ ጋር ተያይዞ በተለያዩ አካላት ዘንድ የፀጥታ ችግር በተለያዩ ቦታዎች የሚነሱ የማንነትና ራስን የማስተዳደር ጥያቄዎች ስጋቶች ጋር ተያይዞ በቀጣዩ ምርጫ ላይ ፈታኝ ሁኔታዎች ሊደቀኑ እንደሚችሉ የተለያዩ አካላቶች እየገለፁ ሲሆን ይህንን የቦርዱ ኃላፊ ጉዳዩን እንደሚረዱት ገልፀዋል።

በተለይም ከጥቂት ወራት በፊት መካሄድ የነበረበት ኃገራዊ የህዝብና የቤቶች ቆጠራ በተለያዩ ምክንያቶች ካለመከናወኑ ጋር ተያይዞ፤ ቀጣዩ ምርጫ እንዴት ሊካሄድ ይችላል የሚሉ ጥያቁ የተጠየቁት የቦርድ ኃላፊዋ በኢትዮጵያ ባለው የምርጫ አሰራር አወቃቀር መሰረት የመራጮች ምዝገባ ከቤትና ከህዝብ ቆጠራው ጋር ቀጥታ የሚመሰረት እንዳልሆነ ነው።

ነገር ግን ምርጫውና የህዝብ ቆጠራው ቢደጋገፉ ጠቃሚ መሆኑንም አልደበቁም።

"ቀጣዩን ምርጫ ከዳር ሆኜ ባልታዘብም ተወዳዳሪ ግን አልሆንም" ብርቱካን ሚደቅሳ

በተለይም አገሪቱ ካለችበት የፀጥታ ስጋቶች ጋር ተያይዞ ምንም እንኳን ምርጫው ሊራዘም ይችላል የሚሉ አስተያየቶች ከተለያዩ አካላት ቢሰሙም ምርጫ ቦርዱ ማንኛውንም ስራ እያከናወነ ያለው ምርጫው በህገ መንግሥቱ በተያዘለት ቀነ ቀጠሮ ይከናወናል በሚል እሳቤ እንደሆነና፤ በተለያዩ ምክንያቶች ግን ጊዜው ሊቀየር እንደሚችል ጠቆም አድርገዋል።

"እስካሁን ባለው ሁኔታ እኛ እየሰራን ያለነው ምርጫው በተያዘለት ጊዜ እንደሚከናወን ታሳቢ አድርገን፤ በዛን ጊዜ ለመድረስ ነው።" ብለዋል።

ተያያዥ ርዕሶች