በጃፓን በተፈጸመ ጥቃት ከሞቱት ሦስት ሰዎች መካከል አንዲት ህጻን ትገኝበታለች

የአደጋ ሰራተኞች ጥቃቱ በደረሰበት አካባቢ ድንኳን ጥለው የህክምና እርዳታ ሲሰጡ Image copyright Reuters

ወደ ትምህርት ቤት ለመሄድ አውቶቡስ እየጠበቁ የነበሩ ሕፃናት በስለት ጉዳት እንደደረሰባቸው ተነገረ።

ጥቃቱ የተፈፀመው በደቡባዊ ቶኪዮ ሲሆን 18 ሰዎች ጉዳት ሳይደርስባቸው እንዳልቀረ ተገልጿል። አንዲት የመጀመሪያ ደረጃ ተማሪ እና አንድ የ39 አመት ጎልማሳ በጥቃቱ መገደላቸው ታውቋል።

ጥቃቱን አድርሷል የተባለ እድሜዎቹ በ50ዎቹ የሚገመት ግለሰብ ራሱን በያዘው ስለት አንገቱ አካባቢ የወጋ ሲሆን በፖሊስ በቁጥጥር ስር ከዋለ በኋላ እንደሞተ ተነግሯል።

ጥቃቱ የደረሰባቸው 16 ሕፃናት ሴት ተማሪዎች መሆናቸው የታወቀ ሲሆን ወንጀሉ የተፈፀመበትን ሁለት ቢላ ፖሊስ በእግዚቢትነት ይዟል።

ምርጫ ቦርድ በቀጣይ ለሚካሄደው ምርጫ 3.7 ቢሊዮን ብር ጠየቀ

የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ይቅርታ ጠየቀ

ጋዜጠኛ ታምራት አበራ በመታወቂያ ዋስ ተለቀቀ

ተማሪዎቹን ወደ ትምህርት ቤታቸው ለመውሰድ በስፍራው ተገኝቶ የነበረው አሽከርካሪ እንደተናገረው ጥቃት አድራሹ ወደ መኪናው ለመግባት ተራ ይዘው የነበሩ ተማሪዎችን በስለት መውጋት እንደጀመረ እና በኋላም ወደ መኪናው በመግባት ውስጥ ያሉትንም እንደወጋቸው አስረድቷል።

አንድ የአይን ምስክር "በአውቶቡስ ማቆሚያው አካባቢ አንድ ሰው ወድቆ ደም ሲፈስሰው አይቻለሁ" በማለት ለቢቢሲ ተናግሯል። ''ተማሪዎችም ወድቀው ተመልክቻለሁ... ሰላማዊ አካባቢ ነበር። እንዲህ አይነት ነገር ማየት ያስፈራል'' ሲል የተሰማውን ለጋዜጠኞች ተናግሯል።

የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች በስፍራው ደርሰው የተጎዱትን እርዳታ እያደረጉ ሲሆን ለይፋዊ የስራ ጉብኝት አሜሪካ የሚገኙት ዶናልድ ትራምፕም የተሰማቸውን ሐዘን ገልጠዋል።

ጃፓን እንዲህ አይነት ጥቃቶች በስፋት ከማይስተዋልባቸው ሀገራት መካከል አንዷ ስትሆን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን በስለት የሚደርሱ ጥቃቶች ቁጥር እየጨመረ መጥተዋል።

ተያያዥ ርዕሶች