ቢሊየነሯ ማኬንዚ ቤዞስ የሀብታቸውን ግማሽ ለበጎ አድራጎት ለመስጠት ወሰኑ

ጄፍ ቤዞስና ማኬንዚ ቤዞስ Image copyright Getty Images

የአማዞን ኃላፊ ጄፍ ቤዞስ የቀድሞው ባለቤት ማኬንዚ ቤዞስ የሀብቷን ግማሽ ለበጎ አድራጎት ለመስጠት ቃል ገባች።

ልግስናዋ ከቢሊየነሮቹ ዋረን ቡፌትና የማይክሮሶፍት መስራች ቢል ጌትስ ጎራ እንድትቀላቀል አድርጓታል። ሀብት ለመለገስ ቃል መግባት የተጀመረው በነዋረን ቡፌትና ቢል ጌትስ ሲሆን፤ ሌሎች ከበርቴዎችም ሀብታቸውን እንዲለግሱ ተጠይቋል።

የሶማሌ ላንድ መስጊዶች ድምፅ እንዲቀንሱ ተጠየቁ

'መንፈስ ቅዱስ' ከቅጣት የጋረደው አሽከርካሪ

የምልክት ቋንቋ በብዛት የሚነገርባት መንደር

የቤዞስ ሀብት 37 ቢሊየን ዶላር ይገመታል። ከቀድሞ ባለቤቷ ጋር በዚህ ዓመት ሲፋቱ በኩባንያው ውስጥ የ4 በመቶ ድርሻ እንዲኖራት ተደርጓል።

"ተፈጥሮ ከለገሰችኝ ሀብት በተጨማሪ ለሌሎች ማካፈል የምችለው ከፍተኛ ገንዘብ አለኝ" በማለት በበጎ አድራጎት ተግባር ላይ ያተኮረ ሥራዋን እንደምትገፋበት ገልጻለች። ሥራው ጊዜ፣ ጥረትና ጥንቃቄ እንደሚያሻውም አክላለች።

ሀብት ለመለገስ ቃል የሚገባበት ሰነድ በ23 አገራት በሚገኙ 204 ግለሰቦች፣ ጥንዶችና ቤተሰቦች ተፈርሟል።

በ2010 ላይ የቀድሞው የኒው ዮርክ ከንቲባ ማይክል ብሎምበርግ፣ የሲኤንኤን መስራች ቴድ ተርነር እና የመዝናኛ ኢንዱስትሪው ከበርቴ ባሪ ዲለር ቃል መግቢያ ሰነዱን ፈርመዋል።

ተያያዥ ርዕሶች

በዚህ ዘገባ ላይ ተጨማሪ መረጃ