'መንፈስ ቅዱስ' ከቅጣት የጋረደው አሽከርካሪ

እርግብ ከገንዘብ ቅጣት የታደገችው ሾፌር Image copyright Viersen District Police

ጀርመን ውስጥ ነው። አንድ ሾፌር መንዳት ከሚገባው ፍጥነት በላይ እየከነፈ ሲጓዝ፤ በትራፊክ ፖሊስ ካሜራ እይታ ውስጥ ይገባል።

ጀርመን ውስጥ ከፍጥነት ወሰን በላይ ማሽከርከር 105 ዩሮ (2600 ብር ገደማ ) ያስቀጣል። ትራፊክ ፖሊሶችም ግለሰቡን ለመቅጣት የደህንነት ካሜራውን ሲመለከቱ ያልጠበቁት ገጠማቸው።

የግለሰቡ መኪና ፊት ለፊት አንዲት ነጭ እርግብ ትበራለች። እርግቧ ትበር የነበረው በሾፌሩ መቀመጫ ትክክል ስለነበረ የግለሰቡን ማንነት መለየት አልተቻለም። ፖሊሶቹም እርግቧ "የመንፈስ ቅዱስ አምሳያ ናት" ብለው፤ ግለሰቡን ላለመቅጣት ወሰኑ።

ፖሊሶቹ እርግብ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ መንፈስ ቅዱስን መወከሏን አጣቅሰው፤ ለግለሰቡ ከለላ ስለሰጠችው ከቅጣት ተርፏል ብለዋል።

ተዓምራዊቷ ቅድስት ማርያም ውቕሮ ገዳም

ደቡብ ኮሪያዊው ፓስተር በአስገድዶ መድፈር ወንጀል ታሰሩ

"ግለሰቡ በእርግብ አምሰያ የተላከለትን መልዕክት ተረድቶ ከዚህ በኋላ የፍጥነት ወሰን አይጥስም ብለን ተስፋ እናደርጋለን" ሲሉም ፖሊሶች ተናግረዋል።

ግለሰቡ ያሽከረክር የነበረበት ጎዳና የፍጥነት ወሰን በሰዓት 34 ኪሎ ሜትር ሲሆን፤ እሱ ግን በ54 እየነዳ ነበር።

ፖሊሶቹ መቅጣት ፈልገው የነበረው ግለሰቡን ብቻ ሳይሆን እርግቧንም ጭምር ነበር። "እርግቧ እጅግ በፍጥነት በመብረሯ ልንቀጣት ፈልገን ነበር። ግን የት ለመድረስ እንደምትከንፍ ስላላወቅን ይቅር ብለናታል" ብለዋል።

ተያያዥ ርዕሶች