ማርክ ዙከርበርግ ከፌስቡክ ኃላፊነቱ እንዲነሳ ሊጠየቅ ይችላል

ማርክ ዙከርበርግ Image copyright Reuters

ዛሬ በሚካሄደው የፌስቡክ ዓመታዊ ጉባዔ ላይ ማርክ ዙከርበርግ ከፌስቡክ አስተዳዳሪነት እንዲነሳ ምርጫ ይደረጋል ተብሎ ይጠበቃል።

ማርክ ዙከርበርግ የፌስቡክ የቦርድ ዳይሬክተሮች ኃላፊና የፌስቡክ አስተዳዳሪም ነው። ከኃላፊነቱ እንዲነሳ የሚፈልጉ አካላት፤ ማርክ በተቋሙ አስተዳደር ላይ ብቻ እንዲያተኩር ይፈልጋሉ።

ማርክ በድርጅቱ 60 በመቶ ድርሻ ስላለው በምርጫው ሊሸነፍ የሚችልበት እድል ጠባብ ነው። ሆኖም ሌሎች የድርጅቱ ባለድርሻዎች ስለአመራር ብቃቱ ምን እንደሚያስቡ የሚታይበት ምርጫ ይሆናል።

ፌስቡክ የተጠቃሚዎችን ግላዊ መረጃ መበርበሩን አመነ

ፌስቡክን ለልጆች?

ማርክ እንዲነሳ ከሚፈልጉት መካከል ከድርጅቱ ወደ ሰባት ሚሊየን ዶላር ገደማ ድርሻ ያለው 'ትሪለም አሴት ማኔጅመንት' ይገኝበታል።

የ'ትሪለም አሴት ማኔጅመንት' ምክትል ፕሬዘዳንት እንዳሉት፤ አሁን ማርክ በሁለት ሥራ ተጠምዷል። ማርክ በድርጅቱ አስተዳደር ላይ ብቻ እንዲያተኩርና የቦርድ ኃላፊነቱን ቦታ ሌላ ሰው መሸፈን አለበት።

እንደምሳሌ የጠቀሱት ቢል ጌትስ የማይክሮሶፍት ፈጣሪ እንጂ የቦርድ ኃላፊ አለመሆኑን ነው። ማርክም ተመሳሳይ እርምጃ ከወሰደ እሱና ሌሎችም የድርጅቱ ባለድርሻዎች ተጠቃሚ እንደሚሆኑ አክለዋል።

በያዝነው ወር ማርክ ከፌስቡክ ኃላፊነት እንዲነሳ በቀድሞው የፌስቡክ ደህንነት ክፍል ኃላፊ አሌክስ ስታሞስ መጠየቃቸው ይታወሳል። ማርክ ፌስቡክ ውሰጥ "ከፍተኛ ኃይል አለው" ብለው ነበር።

ፌስቡክ ሦስት ቢሊዮን አካውንቶችን አገደ

ከዚህ ቀደም ማርክ የአስተዳደር ቦታው ላይ መቀመጡ ተገቢ እንደሆነ ሲናገር ተደምጧል።

"እንደፌስቡክ ያለ ዓለም ላይ ታይቶ የማይታወቅ ነገር ሲጀመር ስህተቶች ሊፈጠሩ ይቸላሉ። ከስህተታችን እየተማርን መሆኑን ሰዎች እንዲገነዘቡ እፈልጋለሁ" ብሎም ነበር።