የፌደራል ዋና ኦዲተር፡ የተሟላ የወጪ ማስረጃ ሳይቀርብ ከ1.4 ቢሊየን ብር በላይ ወጪ ተደርጓል

ዋና ኦዲተር አቶ ገመቹ ዱቢሶ
አጭር የምስል መግለጫ ዋና ኦዲተር አቶ ገመቹ ዱቢሶ

የፌደራል ዋና ኦዲተር አቶ ገመቹ ዱቢሶ ዛሬ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባቀረቡት ሪፖርት፤ የሂሳብ አያያዝ ግድፈቶች፣ የውስጥ ቁጥጥር ድክመቶችና አፈጻጸማቸው ከሕግ ውጪ የሆኑ የተባሉ የአሠራር ችግሮችን ይፋ ተደርገዋል።

በሪፖርቱ መሰረት፤ በውጪ ጉዳይ ሚንስቴር 810,060፣ በሰመራ ዩኒቨርስቲ 123,599፣ በጅግጅጋ ዩኒቨርስቲ 27,173 በድምሩ 960,832 ብር ጉድለት ተገኝቷል።

"ሕዝብ እንዲጠይቅ አድርገናል" ዋና ኦዲተር ገመቹ ዱቢሶ

በበጀት ዓመቱ መጨረሻ በሂሳብ መግለጫ ሪፖርት የተደረገውና በቆጠራ የተገኘው ጥሬ ገንዘብ መካከል በሁለት የገቢዎችና ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶች፤ ቆጠራው ከመዝገብ ጋር ሲነጻጸር 102,532 ብር በማነስ ልዩነት እንደታየበትም ተመልክቷል።

በተጨማሪም በ14 መሥሪያ ቤቶችና በ14 ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤቶች የተለያዩ የጥሬ ገንዘብና የባንክ ሂሳብ አያያዝ ድክመቶች መኖራቸው መረጋገጡን ዋና ኦዲተሩ ገመቹ አሳውቀዋል።

በ129 መሥሪያ ቤቶችም 4,252,562,207 ብር በወቅቱ ሳይወራረድ መገኘቱ ተገልጿል።

"በራሷ ገቢ የምትተማመንና መቆም የምትችል ሀገር ማየት እሻለሁ"ወ/ሮ አዳነች አቤቤ

በወቅቱ ያልተወራረደ ውዝፍ ተሰብሳቢ ሂሳብ ከተገኘባቸው መሥሪያ ቤቶች ውስጥ የብሔራዊ አደጋ ስጋትና ሥራ አመራር ኮሚሽን 608,731,337 ብር፣ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ 441,828,292 ብር፣ አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ 322,520,418 ብር፣ የቀድሞ ውሀ መስኖና ኤሌክትሪክ ሚኒስቴር 282,965,014 ብር፣ መቀሌ ዩኒቨርስቲ 250,218,048 ብር፣ የትምህርት ሚኒስቴር 232,084,916 ብር፣ ኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ 160,457,088 ብር፣ የውጪ ጉዳይ ሚንስቴር 108,079,052 ብር እንዲሁም የመንግሥት ግዢና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት 111,362,647 ብር ይገኙበታል።

በዘጠኝ መሥሪያ ቤቶችና በስድስት ቅርንጫፍ መሥሪያ ቤቶች ከመቼ ጀምሮ በተሰብሳቢነት እንደተመዘገበና በማን እንደተመዘገበ በቂ መረጃ ያልተገኘበት 1,298,391,518 ብር መገኘቱን ዋና ኦዲተሩ የገለጹ ሲሆን፤ በዚህ ከፍተኛውን ድርሻ የያዙት የአገር መከላከያ ሚንስቴርና የውጪ ጉዳይ ሚንስቴር ናቸው ተብሏል።

መሰብሰብ የሚገባቸውን ገቢ ካልሰበሰቡ መሥሪያ ቤቶች መካከል በቀድሞው ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ዋና መሥሪያ ቤትና በሥሩ ባሉ 15 ቅርንጫፍ መሥሪያ ቤቶች 302,835,172 ብር ሳይሰበሰብ ቀርቷል።

የኦነግ ጦር መሪ በትግላችን እንቀጥላለን አለ

በኦዲት ሪፖርቱ እንደተገለጸው፤ በ100 መሥሪያ ቤቶችና ስምንት ቅርንጫፍ መሥሪያ ቤቶች በጨረታ መፈጸም ሲገባቸው ያለጨረታ 802,199,221 ብር በቀጥታ ግዢ ተፈጽሟል።

ከዚህ በተጨማሪ ግልጽ ጨረታ ማውጣት ሲገባቸው በዋጋ ማወዳደሪያ የተፈጸሙ፣ የዋጋ ማወዳደሪያ ሳይሰበሰብ ግዢ የተፈጸሙ በአጠቃላይ የመንግሥት የግዢ አዋጅ፣ ደንብና መመሪያ ያልተከተለ የ 956,822,601 ብር ግዢ ተገኝቷል።

ከግዢ አዋጅና መመሪያ ውጪ ግዢ ፈጽመዋል ከተባሉ መሥሪያ ቤቶች መካከል የብሔራዊ የአደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን፣ የውጪ ጉዳይ ሚንስቴርና የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ሕግ ይገኙበታል።

የቦይንግ ኃላፊ የሟቾችን ቤተሰቦች በይፋ ይቅርታ ጠየቁ

የትምህርት ሚንስቴር፣ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ጽሕፈት ቤትና ሌሎችም ተቋሞች ደንብና መመሪያ ሳይጠብቁ ክፍያ መፈጸማቸውን የፌደራል ዋና ኦዲተሩ አቶ ገመቹ የገለጹ ሲሆን፤ በአጠቃላይ በ77 መሥሪያ ቤቶችና በሰባት ቅርንጫፍ መሥሪያ ቤቶች 145,676,300 ብር ከደንብና መመሪያ ውጪ ተከፍሎ ተገኝቷል።

63 መሥሪያ ቤቶች የተሟላ የወጪ ማስረጃ ሳይቀርብ የ1,475,867,250 ብር ወጪ ማድረጋቸው የተገለጸ ሲሆን፣ ከነዚህ መካከል ብሔራዊ አደጋ ሥራ አመራር ኮሚሽን፣ አገር መከላከያ ሚነስቴርና የውጪ ጉዳይ ሚንስቴር እና ጋምቤላ፣ ወልቂጤ፣ ዋቻሞ እና ጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲዎች ይገኙበታል።

የንግድ ሥራ ፍቃድ፣ የግብር ከፋይነት ምዝገባ ሰርተፍኬት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢነት ሰርተፊኬት እና የውል ስምምነት የወጪ ማስረጃ ሆነው ሊቀርቡ የሚችሉ ማስረጃዎች ናቸው።

የተሟላ የወጪ ማስረጃ ሳይቀርብ ከ1.4 ቢሊየን ብር በላይ ወጪ ተደርጓል

አራት ዩኒቨርሲቲዎች የግንባታ ሥራ ፕሮጀክት የማማከር ፍቃድ በሌላቸው የግንባታ ጽህፈት ቤቶች 114,959,683 ብር ወጪ አድርገዋል። አንድ ዩነቨርስቲ በአማካሪ ባልጸደቀ የክፍያ የምስክር ወረቀት 36,232,839 ብር ክፍያ መፈጸሙንም ዋና ኦዲተሩ ተናግረዋል።

ትምህርት ሚኒስቴር ተጨማሪ ሥራ ውል ስምምነት ሳይፈርም 18,629,844 ብር፤ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ደግሞ ሕግ የሚፈቅደው የመጀመሪያው ውል እስከ 30 በመቶ ሆኖ ሳለ ከተፈቀደው በላይ የ1,270,586 ብር ውል መግባቱ ተገልጿል።