ኦሮምያ ክልል ውስጥ ወደ ቤልጄም ሊላክ የነበረ ቡና መዘረፉ ተሰማ

የምሥራቅ ሸዋ ፖሊስ

ወደ ቤልጄም ሊላክ፤ ወደ ጅቡቲ ወደብ እየተጓጓዘ የነበረ 40 ቶን ቡና መዘረፉ ተሰማ።

በተሳቢ መኪና ተጭኖ በሁለት ኮንቴይነር ወደ ጅቡቲ እየተጓጓዘ የነበረው ቡና በኦሮሚያ ክልል፣ ምስራቅ ሸዋ ዞን፣ ሎሜ ወረዳ እንደተዘረፈ የዞኑ ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ሂደት ባለቤት የሆኑት ኮማንደር ተስፋሁን ታደሰ ለቢቢሲ አረጋግጠዋል።

የኩሩ ኢትዮጵያ ኮፊ ዴቬሎፕመንት ባልደረባ የሆኑት አቶ ቴዎድሮስ ተፈሪ በበኩላቸው፤ ሰኞ እለት ሁለት ተሳቢ መኪና ቡና ተጭኖ ወደ ጅቡቲ ይሄድ እንደነበረ አስታውሰው፤ ዝርፊያ የተፈፀመበት ተሳቢ ከቀኑ 10 ሰዓት ከአዲስ አበባ እንደተንቀሳቀሰ ተናግረዋል።

አቶ ቴዎድሮስ ቡናው በሁለት ኮንቴይነር የተጫነ 690 ኬሻ (40 ቶን ገደማ) መሆኑን ተናግረው፤ ዘረፋው የተፈፀመው ከምሽቱ ሦስት ሰዓት አካባቢ መሆኑን፣ በሹፌሩም ላይ ድብደባ እንደደረሰበት ገልጸዋል።

ወደ ለንደን የሚሄደው አስደናቂው የትራምፕ ጓዝ

ኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያን ስደተኞች ከሊቢያ ወደ ጣልያን ተወሰዱ

በአተት ሳቢያ የአምስት ሰዎች ሕይወት አለፈ

ኮማንደር ተስፋሁን ዝርፊያው የተፈጸመው ሰኞ ግንቦት 19 ቀን 2011 ዓ. ም. ምሽት መሆኑን አረጋግጠው፤ ቡናውን የጫነው መኪና 39 ሺህ 900 ኪሎ ግራም ቡና ጭኖ ነበር ብለዋል። ፓሊስ ባደረገው ክትትልም ከተዘረፈው ቡና ማግኘት የቻለው 5ሺህ 514 ኪሎ ግራም ቡና ብቻ መሆኑን ጠቅሰዋል።

አቶ ቴዎድሮስ ሹፌሩ "በመልክ የማውቀው የጅቡቲ ሹፌር ነው" ያለውን ግለሰብ አዳማ ከመድረሱ በፊት ጭኖ እንደነበር መናገሩን ገልጸው፤ ማታ ሦስት ሰዓት ላይ መኪናውን ሲያቆም ዘራፊዎች እንደያዙት መስማታቸውን ይናገራሉ።

ኮማንደሩ እንዳሉት፤ ዝርፊያውን የፈጸሙት ግለሰቦች የተጠቀሙበት ቪትስ መኪና እንዲሁም አንድ ተጠርጣሪ በቁጥጥር ሥር የዋለ ሲሆን፤ ቀሪዎቹን ተጠርጣሪዎች ለመያዝ ክትትል እያደረጉ ነው።

ኮማንደር ተስፋሁን ጉዳዩ ምርመራ ላይ ስላለ ዝርዝር ማብራሪያ ለመስጠት እንደሚቸገሩ በመግለፅ፤ ቡናውን ጭኖ የነበረው ተሳቢ መኪና በኅብረተሰቡ ጥቆማና ትብብር ተገኝቷል ብለዋል። አክለውም የዝርፊያው ተባባሪ ናቸው የተባሉ ሰዎችን የማጣራት ሥራ እየተከናወነ ነው ብለዋል።

ተያያዥ ርዕሶች