"እስከ ሰኔ መጨረሻ ሁሉም ተፈናቃዮች ወደ ቀያቸው ይመለሳሉ" የሰላም ሚንስቴር

ወ/ሮ ሙፈሪያት ካሚል

የሰላም ሚንስቴር ሚንስትር ወ/ሮ ሙፈሪያት ካሚል ዛሬ በሰጡት መግለጫ እስከ ሰኔ መጨረሻ ድረስ ተፈናቃዮችን ወደትውልድ ቀያቸው የመመለስ እቅድ እንዳላቸው አሳውቀዋል።

ሚንስትሯ እንዳሉት፤ ከቀያቸው የተፈናቀሉ ሰዎችን ወደቀደመ ሕይወታቸው መመለሱ በሦስት ደረጃ የሚከናወን ሲሆን፤ ወደቀያቸው መመለስ የማይፈልጉ ግለሰቦችን ግን አያስገድዱም።

"የመከላከያ ሚኒስቴርን በተሻለ መልኩ መምራት ይቻላል" ኢንጂነር አይሻ መሀመድ

"የተፈናቀሉ ሰዎች ወደቀያቸው መመለስ ያለባቸው በፈቃዳቸው ነው። ክብራቸው ተጠብቆና ዘላቂነት ባለው ሁኔታ የሚከናወንም ነው" ያሉት ሚንስትሯ የመመለስ ሂደቱ በዘፈቀደ የሚደረግ እንዳልሆነም ተናግረዋል።

ኢትዮጵያ ውስጥ ካሉት 2.3 ሚሊዮን ተፈናቃዮች መካከል 1.2 ሚሊዮን የሚሆኑት የተፈናቀሉት ከግንቦት 2011 ዓ. ም. በፊት ሲሆን፤ የተቀሩት 1.1 ሚሊዮን ሰዎች የተፈናቀሉት ከግንቦት ወዲህ ነው።

ከ2.3 ሚሊዮኑ ተፈናቃዮች 1.7 የሚሆኑት የተፈናቀሉት በግጭት፣ ባለመረጋጋትና በደረሰባቸው ጥቃት ሳቢያ ነው። 400 ሺህ የሚሆኑት ከተፈጥሯዊ አደጋ ጋር በተያያዘና በምግብ እጥረት ከትውልድ ቀያቸው መፈናቀላቸውን ወ/ሮ ሙፈሪያት ተናግረዋል።

አምስት ነጥቦች ስለጌዲዮ ተፈናቃዮች

ከተፈናቀሉት ሰዎች 1. 5 ሚሊዮን የሚሆኑት ይኖሩበት በነበረው ክልል የተፈናቀሉ ሲሆን፤ የተቀሩት ተፈናቅለው ወደሌላ ክልል የሄዱ ናቸው።

ሚንስትሯ ተፈናቃዮች ወደቀያቸው ከመመለሳቸው በፊት ውይይት እንደሚደረግ ገልጸው፤ "ምን እንደሚፈልጉ፣ የት መኖር እንደሚፈልጉ እንጠይቃቸዋለን" ብለዋል።

መፈናቀልን ለግል ጥቅማቸው ለማዋል የሚሞክሩ እንዳሉ ገልጸው፤ ተፈናቀዮች ላይ የአካል ጥቃት የሚያደርሱ መኖራቸውንም አክለዋል። ተፈናቃዮች ወደ ትውልድ ቀያቸው እንዲመለሱ የማይፈልጉ አካሎች ተፈናቃዮቹ ለመመለስ መኪና ሲሳፈሩ ጥቃት እንደሚያደርሱባቸው ተናግረው፤ "እነዚህ ግን ብዙ አይደሉም" ብለዋል።

ሚንስትሯ "የግጭት ነጋዴዎች" ያሏቸው ላይ እርምጃ መውሰድ እንደሚቀጥሉ ተናግረዋል።

የብሔር ግጭት የሚንጣት ሀገር

በአንዳንድ አካባቢዎች መሣሪያ ታጥቀው፣ ተደራጅተው የሚንቀሳቀሱ እንዳሉና እርምጃ እየተወሰደባቸው መሆኑን የሰላም ሚንስትሯ ተናግረዋል። "ሁለት መንግሥት የለም፤ ሁለተኛ መንግሥት መሆን የሚችልም የለም" ብለዋል።

በየወረዳው ያሉ አስተዳዳሪዎች "የኛ ናቸው" የሚሏቸውን ሰዎች መደበቅ እንዲያቆሙ የሰላም ሚንስትሯ አሳስበዋል። እስካሁን ሰዎችን በማፈናቀል ምክንያት ከተጠረጠሩ 75 በመቶ የሚሆኑት በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን ተናግረዋል።

ኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያን ስደተኞች ከሊቢያ ወደ ጣልያን ተወሰዱ

ወ/ሮ ሙፈሪያት በዛሬው መግለጫቸው ከተፈናቃዮች ጉዳይ ውጪ ስለመሥሪያ ቤታቸው እንቅስቃሴም የተናገሩ ሲሆን፤ ወደ 100 ሺህ ሰልጣኞች ሰላም ለማስፈን ስልጠና እየወሰዱ መሆኑን ጠቁመዋል።

"በፖሊስና በደህንነት ተቋሞች በሙያ የተካኑ ሰዎችን ለመምጣት እየሠራን ነው" ያሉት ሚንስትሯ፤ በአገሪቱ ሰላም ለማስፈን ለቀጣይ አስር ዓመታት የሚሆን ፍኖተ ካርታ መዘጋጀቱን ተናግረዋል።

አክለውም በየአካባቢው ሰላም ለማስፈን በጎ ፍቃደኞች እየተሰማሩ እንደሆነና እንደሚቀጥልም ገልጸዋል።

ተያያዥ ርዕሶች