አፍሪካውያን ስደተኞች በደቡብ አሜሪካ አድርገው አሜሪካ ለመግባት ተሰልፈዋል

ቴክሳስ የሚገኘው ዴል ሪዮ ድንበረር Image copyright Getty Images

ቴክሳስ የሚገኙ የአሜሪካ ድንበር ጠባቂዎች ባለፉት ሳምንታት ብቻ በመቶዎች የሚቆጠሩ አፍሪካውያንን ድንበር ሊያቋርጡ ሲሉ መያዛቸውን ገልፀዋል።

የአሜሪካ ጉምሩክና ድንበር ተቆጣጣሪ መሥሪያ ቤት ድንበር ላይ የሚደርሱ አፍሪካውያን ቁጥር "በከፍተኛ ቁጥር እየጨመረ"መሆኑን ገልፆ ሁኔታውም "ሰብዓዊ ቀውስ" ነው ብሎታል።

ባለፉት ስምንት ቀናት ብቻ ከ500 በላይ አፍሪካውያን ስደተኞች ዴል ሪዮ ድንበር ላይ በቁጥጥር ስር ውለዋል።

አብዛኞቹ ስደተኞች ከአንጎላ፣ ካሜሮንና ከሪፐብሊክ ኮንጎ የመጡ ቤተሰቦች መሆናቸውን የድንበር ተቆጣጣሪው መሥሪያ ቤት አስታውቋል።

ባለፈው ሳምንት 116 አፍሪካውያን ስደተኞች በአሜሪካ ደቡባዊ ድንበር ላይ መድረሳቸው ታውቋል።

እግር ኳስ ተጫዋቹ ወንድወሰን ዮሐንስ እንዴት ተገደለ?

የአክሱም ሙስሊሞች ጥይቄ መቼ ምላሽ ያገኝ ይሆን?

የደብረብርሃን ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ስጋት ላይ ነን ይላሉ

የዴል ሪዮ ድንበር ተቆጣጣሪ የበላይ ኃላፊ በሰጡት መግለጫ እንዳስታወቁት ከስደተኞቹ ጋር ባለው የባህልና የቋንቋ ልዩነት ምክንያት መግባባት አልቻሉም። ይህም "ተጨማሪ የቤት ስራ" እንደሆነባቸው አስረድተዋል።

አብዛኞቹ ስደተኞች ከዴል ሪዮ ተነስተው ቴክሳስ ወደምትገኘው ሳን አንቶኒዮ ለመድረስ 240 ኪሎ ሜትር መጓዝ ይጠበቅባቸዋል።

የሳን አንቶኒዮ ከተማ አስተዳደር ቃል አቀባይ ለቢቢሲ እንደገለፁት ከበጎ አድራጎት ድርጅቶች ጋር በጋራ በመሆን ለስደተኞቹ ሁሉን አቀፍ አገልግሎት የሚሰጥ ማዕከል እያቋቋሙ ነው።

የአካባቢው ባለስልጣናት ፈረንሳይኛ ተናጋሪ በጎ ፈቃደኞችን እየፈለጉ ሲሆን በሚቀጥሉት ቀናት ብቻ 300 ስደተኞች ወደ ከተማቸው ይደርሳሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ተናግረዋል።

አፍሪካውያኑ እንዴት አሜሪካ ድንበር ደረሱ?

አፍሪካውያኑ እስካሁን ድረስ የትኛውን መስመር ተከትለው አሜሪካ ደጃፍ እንደተገኙ በግልፅ የታወቀ ነገር የለም።

ነገር ግን በቅርቡ በተደረገ አንድ ቃለምልልስ አፍሪካውያን ቤታቸውን ጥለው በቅድሚያ ወደ ብራዚል እንደሚጓዙ መረጃ አለ። ከዛም ወደ ሰሜናዊ ኮሎምቢያ እና ማእከላዊ አሜሪካ በመሄድ ወደ አሜሪካ ድንበር እግራቸውን ያስጠጋሉ።

ይህ ግን በርካታ ሳምንታት የሚፈጅና አድካሚ ጉዞን ይጠይቃል። ከዚህ በኋላ ያለው መላ ምት አሜሪካን ከሜክሲኮ የሚለየውን ሪዮ ግራንዴ ወንዝን ተጠቅመው አሜሪካ ይገባሉ የሚል ነው።

እስካሁን ድረስ 19 ሺህ ስደተኞች ድንበር ሊያቋርጡ ሲሉ መያዛቸውን የአካባቢው ባለስልጣናት ይናገራሉ።

"በማረሚያ ቤት 4ሺህ ስደተኞች ሲኖሩን ከፍተኛ ቁጥር እንዳለን ይሰማን ነበር" ያሉት ኃላፊዎቹ "6 ሺህ ሲኖሩን እንደ ቀውስ እንቆጥረዋለን፤ አሁን ግን 19 ሺህ አሉን ይህ ደግሞ ከአቅማችን በላይ ነው" ሲሉ ተደምጠዋል።

በግንቦት ወር 144 ሺህ 278 ስደተኞች የአሜሪካ ድንበርን የረገጡ ሲሆን ከእነዚህ መካከል 100 ሺዎቹ ቤተሰቦችና ህፃናት ናቸው።

ከባለፈው አመት መስከረም ወር ጀምሮ በአሜሪካ ድንበር ተቆጣጣሪዎች በቁጥጥር ስር ከዋሉ መካከል ስድስት ህፃናት በማቆያ እያሉ መሞታቸው ይታወቃል።

በዚህ ዘገባ ላይ ተጨማሪ መረጃ