ሞሃመድ ሃምዳን ዳጋሎ "ሄሜቲ"፦ የሱዳንን መፃዒ ዕድል የሚወስኑት የጦር አበጋዝ

ሄመቲ- የሱዳንን መፃዒ እድል የሚወስኑት የጦር አበጋዝ Image copyright Getty Images

ሞሃመድ ሃምዳን ዳጋሎ "ሄሜቲ" የሱዳን አስተዳዳሪ ለሆነው የመከላከያ ኃይል ምክትል ፕሬዝዳንትና እጅጉን ተጽዕኖ ፈጣሪ ሰው ናቸው።

በቀውስ ላይ ያለችውን ሱዳን የመጠገን አቅም አላቸው። ነገር ግን ኮማንደሩ ዳርፉር ላይ በተከሰተው የሚሊሻዎች ጭፍጨፋ ይከሰሳሉ። አሁን ላይም ካርቱም ውስጥ በተካሄዱት ግድያዎች እጃቸው አለበት የሚሉ ወገኖች በርካቶች ናቸው።

ሄሜቲ የዳርፉሩን ጭፍጨፋ በተመለከተ "እርምጃው ንዑሃንን ለመጠበቅ ሲባል አስፈላጊ ነበር" ሲሉ የካርቱሙን ጉዳይ ደግሞ ገለልተኛ ወገን ገብቶ ያጠናዋል፤ የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።

የኢትዮጵያ ተፈናቃዮች አይንና ጆሮ እንደተነፈጋቸው ተገለፀ

"ማንኛውም ሰው ድንበሩን ካለፈም መቀጣት አለበት" ብለዋል። የተቃዋሚዎችን መብት አፍናችኋል የተባሉት ኮማንደሩ ሰልፈኞቹ በአጭበርባሪዎችና በአደንዛዥ እፅ ነጋዴዎች የተደለሉ ሰዎች ናቸውም ሲሉ ተደምጠዋል።

"ቀውስ እንዲፈጠር አንፈልግም ወደ ቀደመ እምነታችንም አንመለስም" የሚሉት ሄሜቲ "ወደኋላ የምንመለስበት ምክንያት የለም። የሃገሪቱን ክብር በሕግ እናስከብራለን" ብለዋል።

አሜሪካ፡ የመድኃኒት ዋጋ ሰማይ የደረሰባት ሃገር

ቲና የሱዳን ተቃውሞ

ሄሜቲ የቀድሞው የሱዳኑ ፕሬዝዳንት ኦማር አል በሽር የቅርብ ሰው ነበሩ። ነገር ግን ተቃውሞዎች በታህሳስ ሲጀምሩ ወዳጅነታቸውን ቀንሰዋል።

የተቃውሞ ሰልፎች ሲጀመሩ ከከፍተኛ የመንግሥት ኃላፊዎች መካካል ድጋፍ በመስጠት ሄሜቲ የመጀመሪያው ናቸው። መንግሥትንም "ለዜጎች ተገቢ አገልግሎት በመስጠት ኑሯቸውን ሊያሻሽል ይገባል" ብለዋል። ሚያዝያ 11 ኮማንደሩ ፕሬዝዳንት አል በሽር ሥልጣን እንዲለቁ ካስገደዱ ከ2 ቀናት በኋላ የጊዜያዊ ወታደራዊ አስተዳደሩ ምክትል ፕሬዝዳንት ሆነው መጡ።

"ደላላው ወደ ቤቱ ወሰደኝ፤ በዚያው ቀን አስገድዶ ደፈረኝ"

ቲ ለምን ጠንካራ ልጣን አገኙ?

ምንም እንኳ የወታደራዊ ጊዜያዊ አስተዳደሩ ፕሬዝዳንት አብደል ፈታህ አል ቡርሃን ቢሆኑም ከምዕራባውያን ዲፕሎማቶች ጋር ሲደራደሩ የሚታዩት ግን ሄሜቲ ናቸው። የዐረብ ቡድን የሆነውና በምዕራብ ሱዳን የሚገኘው የጃንጃዊድ ወታደር ፖለቲከኞች እንደሚደግፏቸውም ይነገራል። የቢቢሲ አፍሪካ አርታኢው ፈርጋል ኪን እንደሚለው "ተቃውሞውን መቀልበስ የሚችሉ መሪና ከወታደሩም የተለየ አመለካከት ያላቸው" ይላቸዋል።

የ 'ምን ልታዘዝ' ድራማ ሰምና ወርቅ

ከግብፅ፣ ሳዑዲ ዐረቢያና የተባበሩት ዐረብ ኤምሬቶች የሚሰጣቸው ድጋፍም ሌላኛው የሄሜቲ የኃይል ምንጭ ነው ይባላል።

እነዚህ የዐረብ ሃገራት፤ የሱዳንን መረጋጋት ስለሚፈልጉት ምንም ዓይነት ማዕቀብ በወታደራዊ አስተዳደሩ ዙሪያ መጣል አይፈልጉም። በእርግጥ ሳዑዲ ዐረቢያ የቀጠናው አለመረጋጋት እንደሚያሳስባትና ሁለቱ አካላት መደራደር እንዳለባቸው ጥሪ ማቅረቧ ይታወሳል።

የምሥራቅ ሸዋ ፖሊስ የተዘረፈውን ቡና እየፈለገ ነው

የአልጀዚራ ሪፖርት እንደሚያሳየው ሄሜቲ በግንቦት ወር መጀመሪያ አካባቢ ወደ ሳዑዲ ዐረቢያ በመሄድ ልዑል ሞሃመድ ቢን ሳልማንን አግኝተዋቸዋል። በዚህም ከሁሉም ጥቃትና ስጋት ሃገሪቱን ለመከላከል፣ ከኢራንና ከሁቱ ሚሊሻዎች የሚሰነዘረውን ጥቃት ለመመከት እንዲሁም ሳዑዲ በየመን ለምታካሂደው የቅንጅት ጦርነት ሱዳን ወታደር እንደምትልክም ቃል ገብተው ተመልሰዋል። ምናልባትም የሳዑዲው ልዑል በአፀፋው ከሄሜቲ ጋር ጠንካራ ወዳጅነትን መርጠው ሊሆን ይችላል።

ከግመል ነጋዴነት ወደ ጦር መስፍንነት

ሄሜቲ ከቻዳዊ የዐረብ ጎሣ ነው የተወለዱት።

ጦርነትን በመሸሽ በ1980ዎቹ በዳርፉር መኖር ጀመሩ። እ.አ.አ 2003 ላይ በዳርፉር ጦርነት ተቀሰቀሰ። መብታችን ተረግጧል የሚሉ ጥቁር ነዋሪዎች አማፂ ቡድንን ፈጠሩ። የመንግሥት ወታደርም ጃንጃዊድ ከሚባለው ቡድን ጋር በመሆን ጥቃት ፈፀመ። በዚህም ግመል የሚያረቡ ሰዎች ተገደሉ፣ ሴቶች ተደፈሩ፣ ማንኛውንም ያገኙትንም ንብረት ዘረፉ።

''ወደ ኢትዮጵያ የምናደርገውን ጉዞ አንሰርዝም''

ከ2005 ጀምሮም ዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት የዘር ፍጅት እና በንፁሃን ላይ በተከፈተ የጦር ወንጀል ጥናት አድርጓል። በዚህም በርካታ የሱዳን ባለሥልጣናት፣ የጃንጂዊድ እና የአማፂ ቡድኑ ጥፋተኛ ተብለዋል።

በሱዳንና ቻድ ድንበር ያለውን አካባቢ ከተቆጣጠሩት የዐረብ ጎሣዎች መካከል የሄሜቲ አጎት ጁማ ዶንጎሎ ዋናው ናቸው። ሄሜቲ የአንደኛ ደረጃ ትምህርታቸውን አቋርጠው የግመል ንግድ ይሠሩ የነበር ሲሆን በዳርፉር ጦርነት ወቅትም ለተዋጊዎች ግመል ያከራዩ ነበር። በዚህ ሥራቸው የንግድ ሰው እና ባለፀጋ መሆንም ችለዋል።

ወደ ለንደን የሚሄደው አስደናቂው የትራምፕ ጓዝ

በ2003 የዳርፉር አማፂያን እንቅስቃሴ ሲያደርጉ ሄሜቲ ዘላኖችን በማደራጀት መንግሥትን እንዲያግዙ አድርገዋል። ከዓመት በኋላ ደግሞ ይህ ቡድን መደበኛ ወታደር መሆኑን መንግሥት ይፋ አደረገ። በዚህም ሄሜቲ በፕሬዝዳንት አል በሽር ድጋፍ አገኙ። ወዲያውም ዳርፉር አካባቢ ለሚገኘው የድንበር ጠባቂ ጦር መሪ ሆነው ተመረጡ።

በ2013 መደበኛ ሠራዊቱን ለማገዝ "ፈጥኖ ደራሽ ኃይል" ተቋቋመ። ከዓመት በኋላ ደግሞ ቡድኑ መደበኛ ሠራዊት እንዲሆን በመንግሥት እውቅና ተሰጠው። ተንታኞች እንደሚሉት ግን ጃንጂዊድን እንደገና ማቋቋም ነው።

አውታር - አዲስ የሙዚቃ መሸጫ አማራጭ

የሰብዊ መብት ጥሰት

ዳርፉር ላይ በተፈጠረው የዘር ፍጅት፣ የጦር ወንጀለኝነትና በሰብዓዊ ቀውስ የቀድሞው ፕሬዝዳንት ኦማር አል በሽር በዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት ይፈለጋሉ። በዓለም አቀፉ ፍርድ ቤት ስማቸው ባይጠቀስም የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች ግን በግርፋት እና ሴቶች በብዛት እንዲደፈሩ በማድረግ ሄሜቲን ተጠያቂ ያደርጋሉ።

ስለአልኮል ማስታወቂያ ክልከላ የሚዲያ ባለሙያዎች ምን ይላሉ?

የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች እንደሚሉት በ2014/15 በተካሄደ አመፀኞችን የማፅዳት ዘመቻ መድፈር፣ ቤቶችን ማቃጠል፣ ነዋሪዎችን በጅምላ መግደል በሱዳን ወታደርና በጃንጃዊድ ሚሊሻዎች ተፈፅሟል።

ግንቦት 19፣ 2014 እርምጃው የዳርፉር ንፁሃንን ለመጠበቅ የተወሰደ መሆኑን ሄሜቲ ገልፀው ነበር። ጦሩ ማንኛውንም የፀጥታ ስጋት የሚፈጥር አካል ላይ እርምጃ እንዲወስድም አስጠንቅቀዋል። በካርቱም በሚካሄደው ተቃውሞም ዳርፉር ጎልቶ ስሟ ተነስቷል። ሁላችንም ዳርፉር ነን፣ ዳርፉር ቤታችን ነው የሚሉ ድምፆች ተሰምተዋል።

የታኮ ጫማ ውዝግብ በጃፓን

ሄሜቲ በዳርፉርም በካርቱምም ጨካኝነታቸው በተግባር ቢታይም ሰላማዊ ተቃዋሚዎቹ ግን መብታችንን ለማስጠበቅ እጅ አንሰጥም እያሉ ነው።

በዚህ ዘገባ ላይ ተጨማሪ መረጃ