የኢትዮጵያ ብሔራዊ እርቅ ኮሚሽን አባላት በሐቅና እርቅ ጉዳዮች ላይ ልምድ ለመቅሰም ኬንያ ናቸው

የኢትዮጵያ ብሔራዊ እርቅ ኮሚሽን አባላት Image copyright Ethiopian Embassy in Kenya

11 አባላት ያሉት ብሔራዊ የእርቅ ኮሚሽን የልዑካን ቡድን የልምድ ልውውጥ ለማድረግ ናይሮቢ የሚገኙ ሲሆን በቆይታቸውም በኬንያና በደቡብ አፍሪካ የተካሄዱ የሐቅና እርቅ አፈላላጊ ኮሚሽን ሥራዎች ላይ ልምድ ይቀስማሉ ተብሏል።

ኤምባሲው ይህንን የልምድ ልውውጥ ያዘጋጀው መቀመጫውን እንግሊዝ ካደረገው በሰላም ግንባታ ላይ ከተሰማራ [Conciliation Resources ከተባለ መንግሥታዊ ያልሆነ ድርጅት ጋር በጋራ በመሆን ነው።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ፊቱን ወደ ቻይና እያዞረ ይሆን?

አምባሳደር መለስ የልምድ ልውውጡን ያዘጋጁበትን ምክንያት ለቢቢሲ ሲያስረዱ አንደኛው የኤምባሲዎች ሥራ የእውቀትና የክህሎት ሽግግር ማድረግ መሆኑን ገልፀው የብሔራዊ የእርቅ ኮሚሽን በሀገር ደረጃ ሲቋቋም የመጀመሪያው ስለሆነና አባላቱም ከተለያየ የሙያ ዘርፎች የተውጣጡ በመሆናቸው የተለያዩ ሀገራትን ልምድ መቅሰማቸው ለስራቸው ያግዛቸዋል በሚል ነው ብለዋል።

የኮሚሽኑ አባላት ኢትዮጵያ ውስጥ ብሔራዊ እርቅ እንዲመጣ ፍላጎት ቢኖራቸውም የሌሎች ሀገራትን ልምድ መውሰዳቸው ለሥራቸው አስተዋፅኦ ያደርጋል በማለት ያክላሉ።

ከእኛ ሀገር ጋር ተመሳሳይ ችግር የገጠማቸውን ሀገራት ልምድ መውሰድ ለኮሚሽኑ አባላት የወደፊት ስራ ጠቃሚ ነው ያሉት አምባሳደር መለስ ኬንያ እ.ኤ.አ በ2007ና 2008 ተመሳሳይ ችግር ገጥሟት ስለነበር የኮሚሽኑ አባላት ጠቃሚ ልምድ ይቀስማሉ በማለት ተናግረዋል።

የሱዳን አለመረጋጋት በኢትዮጵያ ላይ የሚያስከትለው ተጽእኖ ምንድነው?

የኮሚሽኑ አባላት በናይሮቢ ቆይታቸው ከሀገሪቱ የሀቅ፣ እርቅና ፍትሕ አፈላላጊ ኮሚሽን እና ብሔራዊ ጥምረት ስልጠና የሚሰጣቸው ሲሆን ከኬንያ በተጨማሪ ከደቡብ አፍሪካም በእርቅና አንድነት ላይ በመሥራት ልምድ ያላቸው ልዑካን በመምጣት ስልጠና እንደሚሰጧቸው ለማወቅ ተችሏል።

በኬንያ ቆይታቸው ከተለያዩ ከፍተኛ የመንግሥት አካላት ጋር ይገናኛሉ ተብሎም ይጠበቃል።

ከመቶ ቢሊዮን ብር በላይ ጭማሪ ያሳየው የኢትዮጵያ በጀት

በዚህ ዘገባ ላይ ተጨማሪ መረጃ