የኢትዮጵያን አደራዳሪነት የሱዳን ህዝብ እንዴት ይመለከተዋል?

አምባሳደር ሙሐመድ ድሪር Image copyright MARWAN ALI

የሱዳን ተቃዋሚዎችና ወታደራዊ ኃይሉ በኢትዮጵያ አደራዳሪነት በድጋሚ በጠረጴዛ ዙሪያ ለመነጋገር ተስማምተዋል።

ሁለቱን የሱዳን ኃይሎች በድጋሚ ወደ ውይይት እንዲመለሱ በማድረጉ ላይ የኢትዮጵያ አስተዋጽኦ ምን ይመስል እንደነበር የጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ ልዩ መልእክተኛ በመሆን ካርቱም የሚገኙት አምባሳደር ሙሐሙድ ድሪር ለቢቢሲ አብራርተዋል።

አምባሳደር ሙሐሙድ ''ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አህመድ ሱዳን በነበራቸው አጭር ቆይታ ሁሉንም ሊባል በሚችል መልኩ የፖለቲካ ኃይሎች አነጋግረዋል'' ይላሉ። ሱዳን ሰላማዊ ሂደት ውስጥ እንድትገባ፣ ሽግግሩ ከመስመር ወጥቶ ወደ ግጭት እንዳያመራ እና ሁሉንም ኃይሎች ለማቀራረብ በማሰብ ኢትዮጵያ የማደራደር ኃላፊነት ውስጥ እንደገባች ይናገራሉ።

በዓመት አንዴ ብቅ የምትለው ከውሃ በታች ያለችው መንደር

ኢትዮጵያ ሁለቱን ኃይሎች በማሸማገሉ ላይ ከሌሎች ሃገራት ድጋፍ አግኝታ እንደሆነ የተጠየቁት አምባሳደሩ፤ የኢትዮጵያ መንግሥት እንደ አንድ የአፍሪካ ሃገር የሱዳን ጉዳይ እንደሚያሳስበው ያስረዳሉ። ''ሱዳን የኢጋድ አባል ሃገር እና ጎረቤት ሃገር እንደመሆኗ ይሄንን ጉዳይ በዚህ አስተሳሰብ እና አመለካከት ነው የምንመለከተው።'' ብለዋል።

የሱዳንን ወቅታዊ ፖለቲካዊ ለውጥ በቅርበት የሚከታተሉ ተንታኞች፤ ወታደራዊው የሸግግር መንግሥቱ በቅርብ ጊዜ ስልጣኑን ለሲቪል መንግሥት አሳልፎ ላይሰጥ ይችላል ይላሉ። ይህ በአንዲህ እንዳለ ለተቃውሞ አደባባይ የሚወጡ ሰልፈኞች ወታደራዊ የሽግግር መንግሥቱ ስልጣኑን በፍጥነት ለሲቪሎች አሳልፎ እንዲሰጥ እየጠየቁ ይገኛሉ።

አምባሳደር ሙሃሙድ ድሪር በርካቶች በሱዳን ጉዳይ የመሰላቸውን ሃሳብ ሊሰጡ ይችላሉ፤ ''በዋናነት ግን የሱዳን ህዝብ፣ የሽግግር መንግሥቱ እና የተቃዋሚ ኃይሉ አሁን የተደረሰበትን ስምምነት እንደ እፎይታ ነው የሚመለከተው። የኢትዮጵያንም ሚና በማድነቅ እና በማመስገን እያየው ነው። በቀጣይም ሁሉም የየበኩሉን እንደሚወጣ ነው የምንገነዘበው።'' ብለዋል።

''ሱዳናውያን ጎረቤት ሃገር ኢትዮጵያ በቁርጥ ቀን ደርሳልናለች የሚል አስተሳሰብ አላቸው'' በማለት አምበሳደር ሙሐሙድ የኢትዮጵያ አሸማጋይነት በሱዳናውያን ዘንድ ተቀባይነት እንዳለው ይናገራሉ።

'''ይህ ወገን ስልጣን ላይ ለመቆይት ይፈልጋል፤ ይህ ወገን ሌላኛውን እየተጋፋ ነው' ወደሚል አይነት አደራዳሪነት አንገባም።'' ብለዋል የጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ ልዩ መልእክተኛ አምባሳደር ሙሐሙድ ድሪር።

አምባሳደር ሙሐመድ ድሪር ትናንት ለጋዜጠኞች እንደተናገሩት ወታደራዊ የሽግግር መንግሥቱ በቁጥጥር ስር ያዋላቸውን የፖለቲካ እስረኞች ለመልቀቅ ተስማምቷል።

ተቃዋሚዎች አሁንም የሲቪል አስተዳደር እንዲመሰረት እየጠየቁ ነው።

የአክሱም ሙስሊሞች ጥያቄ መቼ ምላሽ ያገኝ ይሆን?

በተቃዋሚዎችና በወታደሩ መካከል እየተደረገ የነበረው ውይይት የተቋረጠው በርካታ ተቃዋሚ ሰልፈኞች መገደላቸውን ተከትሎ ነበር። ከዚያ ጊዜ ጀምሮ ተቃዋሚዎች በጠሩት ሕዝባዊ አመፅ በርካታ የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ የስራ ማቆም አድማ ተመትቷል።

ሐኪሞች የተገደሉት 118 ሰዎች ናቸው ሲሉ የመንግሥት ባለስልጣናት ግን 61 ሰዎች ከልዩ ኃይሉ በተተኮሰ ጥይት መሞታቸውን ይናገራሉ።

ወታደሮች የካርቱምን አውራ ጎዳናዎች የሚጠብቁ ሲሆን በርካታ የንግድ ተቋማት ተዘግተዋል።

ማክሰኞ ዕለት ኢትዮጵያ አሸማጋይ ሆና በተቀመጠችበት ጠረጴዛ ሁለቱም ወገኖች የሲቪል አስተዳደር ለመመስረት መስማማታቸው ተነግሯል። ተቃዋሚዎችም ከዛሬ ጀምሮ ዜጎች በሥራ ገበታቸው ላይ እንዲገኙም ጥሪ አቅርበዋል።

የሕዝባዊ አመፁን በቅድሚያ የጠራው የሱዳን የሙያ ማህበራት ዜጎች ወደ ሥራ ገበታቸው ይመለሱ የሚለውን ስምምነት ተቀብሎታል።

ወታደራዊ ኃይሉ በይፋ ውይይቱን ለመቀጠል መስማማት አለመስማማቱን አልተናገረም።

ነገር ግን የሽግግር መንግሥቱ አባል የሆኑት ሳላህ አብደልካሀልክ ለቢቢሲ አረብኛ ፕሮግራም እንደተናገሩት ከተቃዋሚዎች ጋር ስልጣንን እኩል ለመጋራት ስምምነት ላይ ሳይደረስ አልቀረም ብለዋል።

በአማራ ክልል በተከሰቱ ግጭቶች 224 ሰዎች በቁጥጥር ሥር ዋሉ

ቢሆንም ግን አሁንም የሽግግር መንግሥቱ ሊቀመንበር ከወታደሩ እንዲሆን እንደሚፈልጉ አልሸሸጉም።

ወታደራዊ ኃይሉ ፕሬዝዳንት ኦማር አል በሺርን ከስልጣን በማውረድ ላይ ቁልፍ ሚና የተጫወተ ሲሆን በርካታ የወታደሩ ሹማምንቶች አሁንም በእስር ቤት ይገኛሉ ሲሉ ተናግረዋል።

ነገር ግን የሽግግር መንግሥቱ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ለመደራደር ዝግጁ ነው ሲሉ አክለዋል።

በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ላይ የአሜሪካ ልዑካን ቡድን ወደ ሱዳን እንደሚያቀናና ሁለቱ ወገኖች ንግግር እንዲጀምሩ ለማድረግ እንደሚጥር አስታውቆ ነበር።

አንዳንድ ከሱዳን የሚወጡ ሪፖርቶች እንደሚያሳዩት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ 15 አባላት ያሉት የሽግግር ምክር ቤት እንዲቋቋምና ስምንት አባላቱ ከተቃዋሚዎች ሰባቱ ደግሞ ከወታደሩ እንዲሆን ሀሳብ ማቅረባቸው ይነገራል።

በዚህ ዘገባ ላይ ተጨማሪ መረጃ