አሜሪካዊቷ እናት አምስት ልጆቿን የገደለው ሰው የሞት ፍርድ አይገባውም ትላለች

አሜሪካዊቷ እናት አምስት ልጆቼን የገደለው ሰው የሞት ፍርድ አይገባውም ትላለች Image copyright CBS

አሜሪካዊቷ እናት አምስት ልጆቿን ያለርህራሄ የገደለው ግለሰብ የሞት ፍርድ አይገባውም ስትል ምስክርነቷን ሰጥታለች።

አምበር ኪዘር የአምስት ልጆች እናት ነበረች፤ ነገር ግን ጨካኝነቱ ጥግ ባጣ አባታቸው ተገድለዋል። እናታቸውን ግን ግለሰቡ ሞት አይገባውም ባይ ነች።

ለምስክርነት የተጠራችው እናት «አባታቸው ለልጆቼ ቅንጣት ታክል ርህራሄ ባያሳይም፤ ልጆቼ ግን ከልባቸው ይወዱት ነበር» ስትል ሳግ እየተናነቃት ተናግራለች።

ደቡብ ኮሪያዊው ፓስተር በአስገድዶ መድፈር ወንጀል ታሰሩ

ግለሰቡ ዕድሜያቸው ከአንድ እስከ ስምንት የሆኑትን ሕፃናት የገደለው 2014 ወርሃ ነሃሴ ላይ ነበር። ግለሰቡን ወንጀለኛ ሆኖ ያገኘው ፍርድ ቤት የሞት ፍርድ ወይስ እሥር የሚለው ላይ እየመከረ ነው።

ጥንዶቹ ለዘጠኝ ዓመታት ያክል በትዳር ከቆዩ በኋላ ነበር የተፋቱት፤ ምክንያቱ ደግሞ ሰውዬው ወ/ሮ አምበርን መበደል በመጀመሩ ነው።

ግለሰቡ ከወ/ሮ አምበር የተሻለ ገቢ ስለነበረው የአሳዳጊነት ድርሻውን ወስዶ አምስቱን ልጆች ያሳድጋቸው ያዘ። እናት ደግሞ ዘወትር እሁድ እንድትጎበኛቸው ሆነ።

የቀድሞው ፕሬዝደንት ልጅ በጉልበት ብዝበዛ ወንጀል ተፈረደባቸው

«ልጆቼ በምንም ዓይነት ስቃይ እንዳለፉ ሰምቻለሁ። እንደ አንድ እናት የፊቱን ቆዳ ብገፈው አልጠላም። ውስጤ የሚመኘው ያንን ነው።»

እናት፤ እኔ ድሮም ቢሆን ማንም ሰው የሞት ፍርድ አይገባውም የሚል እምነት አለኝ ስትል ለፍርድ ቤቱ አስረድታለች።

የስድስት ዓመት ልጃቸው በኤሌክትሪክ ገመድ ሲጫወት ያገኘው አባት መጀመሪያው የስድስት ዓመቱን ልጅ ለጥቆም የተቀሩትን ሕፃናት አንቆ ገድሏል ሲል ፍርድ ቤቱ ብይን ሰጥቷል።

ግለሰቡ የአእምሮ ጤና በሽተኛ ነኝና ወንጀለኛ ልባል አይገባም ሲል ተከራክሯል። ጠበቃዎቹም 'ስኪትዞፍሬኒያ' የተሰኘው የአእምሮ በሽታ ተጋላጭ በመሆኑ ነፃ ሊሆን ይገባል እያሉ ነው።

ነብሰ ጡር ጓደኛቸውን ያስገደሉት ባለሥልጣን

በዚህ ዘገባ ላይ ተጨማሪ መረጃ