የቀድሞው የሱዳን ፕሬዝዳንት አል በሺር በሙስና ወንጀል ክስ ተመሰረተባቸው

የቀድሞው የሱዳን ፕሬዝዳንት አል በሺር Image copyright AFP

የቀድሞው የሱዳን ፕሬዝዳንት አል በሽር በሙስና ወንጀል ክስ ተመሰረተባቸው። አቃቤ ሕግ ክሱ የተመሰረተው "ያልተገባ ሀብት በማካበትና እና የአስቸኳይ ጊዜ ትዕዛዝ በመስጠት" በሚል መሆኑን ገልጿል።

ፕሬዝዳንት አል በሽር ባለፈው ሚያዚያ ወር ላይ ነበር ከረዥም ጊዜ ሕዝባዊ ተቃውሞ በኋላ በከፍተኛ የሃገሪቱ ጦር ሠራዊት ባለስልጣናት ከመንበራቸው እንዲወርዱ የተደረጉት።

ሐሙስ እለት የወታደራዊ ኃይሉ ቃል አቀባይ እንደተናገሩት የሲቪል አስተዳደር እንዲመሰረት የተካሄደው ተቃውሞ እንዲያበቃ ትዕዛዝ ሲሰጥ ስህተት ተከስቷል ብለዋል።

ለረዥም ጊዜ የተካሄደው ተቃውሞ በወታደራዊ ኃይሉ እንዲቆም መደረጉን ተከትሎ 61 ሰላማዊ ሰልፈኞች መሞታቸውን ባለስልጣናት ቢናገሩም ከተቃዋሚዎች ጋር ግንኙነት ያለው የሐኪሞች ቡድን ግን የሞቱት 118 ናቸው ሲል ገልጿል።

በዲሞክራቲክ ኮንጎ የተከሰተው የኢቦላ ወረርሽኝ ስርጭት "እጅግ አስበርጋጊ" ነው ተባለ

በተበከለ ደም አራት ወንድሞቹ የሞቱበት እንግሊዛዊ

የሜክሲኮ ፕሬዝዳንት ሕገ-ወጥ ስደትን ለመቀነስ አውሮፕላናቸውን ሊሸጡ ነው

ንፁሃን ዜጎች መገደላቸውን ተከትሎ የሽግግር መንግሥቱን በሚመራው ወታደራዊ ኃይልና በተቃዋሚዎች መካከል የሚደረገው ውይይት ተቋርጦ ነበር።

ያንን ተከትሎም ተቃዋሚዎች በመላው ሀገሪቱ የሚካሄድ ሕዝባዊ አመፅ የጠሩ ቢሆንም በኋላ ግን በሁለቱ ወገኖች መካከል የሚደረገው ንግግር እንዲቀጥል በመስማማታቸው ተቃውሟቸውን አቋርጠዋል።

የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤት የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ፀሐፊ የሆኑት ቲቦር ናዠ እና ሌተናንት ጄነራል አብደል ፈታህ አል ቡርሀን ከተገናኙ በኋላ አሜሪካ "ገንቢ ሚና" ትጫወታለች ብለው እንደሚያምኑ ገልፀዋል።

ፕሬዝዳንት አል በሽር ሱዳንን ለ30 ዓመት ካስተዳደሩበት መንበር ከወረዱ በኋላ ለሕዝብ ታይተው አያውቁም።

ግንቦት ወር ላይ ተቃዋሚ ሰልፈኞችን እንዲገደሉ ትዕዛዝ በመስጠትና በመሳተፍ ክስ ተመስርቶባቸው ነበር።

ተያያዥ ርዕሶች