የትራምፕ እና የለንደኑ ከንቲባ ሳዲቅ ካህን ምን አገናኛቸው?

የትራምፕ እና የሎንዶኑ ከንቲባ ሳዲቅ ካህን እሰጥ አገባ Image copyright PA

የአሜሪካው ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ የለንደኑን ከንቲባ ሳዲቅ ካህን ወርፈዋቸዋል፤ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ሁለተኛው መሆኑ ነው።

የእንግሊዝን ዋና ከተማ እያጠፋ ያለ 'ብሔራዊ ኀፍረት' ሲሉ ነው ትራምፕ የለንደኑን አስተዳዳሪ ያጣሏሏቸው።

ለንደን፤ በ24 ሰዓት ጊዜ ውስጥ አምስት ሰዎች በጩቤ እና በጥይት መገደላቸውን ተከትሎ ነው ትራምፕ ከንቲባውን ከላይ ታች ያከናነቧቸው።

ትራምፕ ቱርክን አስጠነቀቁ

የሌበር ፓርቲ መሪ ጀረሚ ኮርቢን ግን ትራምፕ የሰዎችን ሞት ተጠቅመው ከንቲባውን እንዲህ መናገራቸው 'በጣም የወረደ' ተግባር ነው ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል።

በለንደኑ ከንቲባ ሳዲቅ ካህን እና ዶናልድ ትራምፕ መካከል እሰጣገባ ሲነሳ ይህ የመጀመሪያው አይደለም፤ ምንም እንኳ ብዙ ጊዜ ጠብ የሚጭሩት ዶናልድ ቢሆኑም።

አሁንም ለንደን ውስጥ የተከሰተውን ግድያ ተከትሎ ወደ ትዊተር ያቀኑት ትራምፕ ከታች የተመለከተውን ዘለፋ ፅፈዋል።

የከንቲባ ካህን ቃል አቀባይ 'ከንቲባው በተፈጠረው ነገር ወገን ላጡ ቤተሰቦች መፅናናት ይመኛል። ለመሰል ዘለፋዎች ምላሽ በመስጠት ግን ጊዜያችንን አናባክንም' ሲል አትቷል።

ጠብ አጫሪና ጥቃት አድራሽ የፌስቡክ ፖስቶችን እንዴት ሪፖርት ማድረግ ይቻላል?

የለንደን ፖሊስ ከግድያው ጋር በተያያዘ የጠረጠራቸውን፤ ታዳጊዎችን ጨምሮ 14 ግለሰቦች በቁጥጥር ሥር አውያለሁ ብሏል።

አርብ ዕለት ከሰዓት ነበር በደቡብ ሎንዶን የ18 ዓመት ታዳጊ በጩቤ ተወግቶ የተገደለው፤ ከደቂቃዎች በኋላ ደግሞ የ19 ዓመት ግለሰብ በጥይት ሕይወቱን አጣ።

ዕለተ ቅዳሜ ረፋዱ ላይ ሁለት ግሰለቦች በጩቤ የመገደላቸው ዜና ተሰምቶ ሳያበቃ ከሰዓቱን በ30 ዕድሜ ክልል የሚገኝ ሰው የቢላ ሲሳይ ሆነ።

ክስተቱ በዚህ ዓመት ብቻ ሎንዶን ውስጥ በግድያ ምክንያት ሕይወታቸውን ያጡ ግለሰቦች ቁጥር 56 አድርሶታል።

በወርሃ ሰኔ መባቻ እንግሊዝን የጎበኙት ዶናልድ ትራምፕ ከሳዲቅ ካህን ጋር የቃላት ጦርነት ውስጥ ከገቡ ቢቆዩም ዋነኛ መንስዔ የነበረው ክንቲባው ትራምፕ እንግሊዝ ውስጥ ቀይ ምንጣፍ ሊዘረጋላቸው አይገባም ማለታቸውን ተከትሎ ነው።

ለጎንደር ጥልቅ ፍቅር ያለው ኬንያዊ ቤተ መንግሥት ሊገባ ሲል ተያዘ