በኬንያ ከኢቦላ ጋር የሚመሳሰሉ ምልክቶች ያለባት ታማሚ ተገኘች

ከኡጋንዳ የሚመጡ ተጓዦችን ማጣሪያ Image copyright DANIEL IRUNGU

በደቡብ ምዕራብ ኬንያከፍተኛ ሙቀት፣ ራስ ምታት፣ የመገጣጠሚያ ችግሮች፣ የጉሮሮ መቁሰል እንዲሁም ማስመለስ ምልክቶች የታዩባት አንዲት ታማሚ ኢቦላ ሊሆን ይችላል በሚል ግምትም ምርመራው ቀጥሏል።

በመጀመሪያ ወባ ነው በሚል በአካባቢው በሚገኝ ሆስፒታል እየታከመች የነበረ ሲሆን፤ ውጤቷ ግን ወባ እንደሌለባት እንዲሁም ሁኔታዋ በመባሱ ወደ ሌላ ሆስፒታል ተዛውራለች።

ለብቻዋም ተገልላ እንድትታከም እየተደረገች ነው።

ኢቦላ ዳግም አገረሸ

ኢቦላ ወደ ኡጋንዳ እየተዛመተ ነው

ሕይወት ከኢቦላ ወረርሽኝ በኋላ

ወደ በኋላም ተቅማጥ የታየባት ሲሆን በአሁኑ ወቅት ጤናዋ እየተሻሻለ እንደሆነ ተገልጿል።

መጀመሪያ የታየችበት የግል ክሊኒክ ኢቦላ ተከስቶበታል ወደ ተባለው ኡጋንዳ ድንበር ጉዞ አድርጋ ነበር በሚል በጥንቃቄ እንድትያዝ የገለፀ ቢሆንም እሷ የሄደችበት የምስራቅ ኡጋንዳ ክፍል ምንም ነገር እንዳልተከሰተ ተገልጿል።

በባለፈው ሳምንት በኡጋንዳ ኢቦላ የተከሰተው በምዕራብ የኃገሪቱ ክፍል ሲሆን ይህም ከዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኦፍ ኮንጎ በሚያዋስናት ድንበር እንደሆነ ተገልጿል።

የደም ናሙናዋ ለኢቦላ ምርመራ ወደ ናይሮቢ ተልኳል ተብሏል።