"ቃሊቲ ማረሚያ ቤት ትምህርት ቤት ሆኖኛል" ደበበ እሸቱ

ደበበ እሸቱ

በ1936 ዓ. ም. ነው የተወለደው፤ ደበበ እሸቱ። በሀገር ፍቅርና በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ (የአሁኑ ብሔራዊ ቴአትር) መድረክ ላይ ለረዥም ዓመታት በተዋናይነትና በአዘጋጅነት ነግሷል። በተለያዩ ፊልሞች ላይ በመሪ ተዋናይነት ተሳትፏል። ሆሊውድ በተሠራው 'ሻፍት ኢን አፍሪካ' በተሰኘው ፊልም ላይ በመሳተፍም ስሙን በደማቁ ፅፏል።

ከጋዜጠኛነት በተጨማሪ በራድዮና በቴሌቪዥን ሥራዎችም ላይ ተሳትፏል። 'ያላቻ ጋብቻ'፣ 'ሮሚዎና ዡልየት' እና 'ዳንዴው ጨቡዴ' ከተወነባቸው ሥራዎች ጥቂቶቹ ናቸው።

በእንግሊዘኛ ከሠራቸው ፊልሞች መካከል 'ዘ ሴይለር ፍሮም ጂብራልታር'፣ 'ጉማ'፣ 'ዘ አፍሪካን ስፓይ'፣ 'ዜልዳ'፣ 'ዘ ግሬቭ ዲገር' እና 'ዘ ግሬት ሪቤሊየን ' ይጠቀሳሉ።

ደበበ በአማርኛ ብቻ ሳይሆን በእንግሊዘኛ የተፃፉ ተውኔቶች ላይም ተሳትፏል። 'ዘ ጌም ኦፍ ቼዝ' ላይ በትወና ፣ 'ኦቴሎ' ላይ በመተወንና በማዘጋጀትም አሻራውን አኑሯል።

የአለማየሁ ተፈራ ፖለቲካዊ ካርቱኖች

ደበበ በ1995 ቀስተ ደመና ፓርቲን ተቀላቅሎ፤ በኋላም ቅንጅት ውስጥ የሕዝብ ግንኙነት ነበር። በዚህ የፖለቲካ ተሳትፎው ከአንድ ዓመት በላይ ታስሯል።

ይህ ጎሙቱ የሙያ ሰው ኬንያ፣ ናይሮቢ የሚገኘው ቢሯችን መጥቶ ነበር። እኛም ቀጣዮቹን ጥያቄዎች አቅርበንለታል።

ቢቢሲ፡ ጤናህ እንዴት ነው?

ደበበ እሸቱ፡ እግዚአብሔር ይመስገን ደህና ነኝ። አላማርርም።

'ባዶ እግር'ቴአትር ላይ ትሳተፋለህ ተብሎ ነበር፤ ግን አላየንህም። ለምን ነበር?

ደበበ እሸቱ፡ አንድ ጊዜ አሞኝ ሆስፒታል ገብቼ ነበር። እና ለጊዜው አቋርጬ ነበር። እየደከመኝም፣ አንዳንድ ጊዜ ከእድሜ አንፃር እያየሁት እንጂ በተቻለ መጠን እየሠራሁ ነው።

ከእስር ቤት ከወጣህ በኋላ እንደ አዲስ በተለያዩ ራዎች ወደ አድናቂዎችህ መጥተሀል። መጽሐፍም ተርጉመሀል። መጽሐፉ ምን ያህል ተነቧል?

ደበበ እሸቱ፡ ተነባቢነቱ ምን ያህል እንደሆነ መረጃው የለኝም። ነገር ግን ገበያ ላይ አልቋል።

ስንት ኮፒ ታትሞ ነው ያለቀው?

ደበበ እሸቱ፡አገር ውስጥ ወደ አስር ሺህ ኮፒ ሲሆን፤ በውጪም ታትሞ ለገበያ የቀረበው እንደዚሁ ተሸጦ አልቋል። ስለዚህ አገር ውስጥ በድጋሚ ሊታተም ነው።

ሌላ እየ ወይም እየተረጎም ያለኸውጽሐፍ አለ?

ደበበ እሸቱ፡ በቅርብ ጊዜ ለህትመት የሚበቃ ተርጉሜ የጨረስኩት መጽሐፍ አለ። መጽሐፉ ወደ ኢትዮጵያ ስለመጡት የመጀመሪያው የካቶሊክ ጳጳስ አቡነ ዣርሶ ነው። ስለእርሳቸው ብዙ አይነገርም። ጃንሆይን ፈረንሳይኛ ያስተማሩት አቡነ ዣርሶ ናቸው ይባላል። ነገር ግን አይደሉም። አቡነ ዣርሶ መርጠው ያሳደጓቸው አቶ አለማየሁ የሚባሉ ሰው ናቸው። ጃንሆይ በስደት በሄዱበት ጊዜ ሊግ ኦፍ ኔሽን ውስጥ ገብተው እንዲናገሩ ያደፋፈሯቸው፣ ያስገደዷቸው፤ እንደውም ከፈረንሳይና ከሌሎችም አገሮች አብረዋቸው የሚሄዱ ሰዎች እንደሚኖሩና ይህንን ካላደረጉ ግን የጣሊያን መንግሥት ያለምንም ተቃውሞ ኢትዮጵያን ቅኝ ስለሚገዛ ሄደው ንግግር ያድርጉ ያሉ ትልቅ ሰው ናቸው።

በብርሃን ታስሰው የማይገኙት ሴት ኮሜዲያን

ንግሥቲቱ ባያቆሟቸው ኖሮ የኢትዮጵያ ሕዝብ በመላ ካቶሊክ ይሆን ነበር፤ ካለህበት ቦታ እንዳንትንቀሳቀስ በማለት የገደቧቸው።

ታሪካቸውን በፈረንሳይኛ ነው የጻፉት። እኔ ወደ እንግሊዘኛ ተመልሶ የታተመውን መጽሐፍ ከአንድ ወዳጄ ጋር አግኝቼ ነው አንብቤ የተረጎምኩት።

መቼ ነው ገበያ ላይ የሚውለው?

ደበበ እሸቱ፡ ገና ወደ ማተሚያ ቤት አልሄደም፤ ምናልባት ከሁለት ወር በኋላ ታትሞ ገበያ ላይ ይውል ይሆናል።

ከእስራኤላውያን ጋር 'ቀያይ ቀምበጦች' የሚል አንድ ፊልም እየራህ እንደነበር ሰምቻለሁ። ኢትዮጵያ ውስጥ ታየ?

ደበበ እሸቱ፡ ኢትዮጵያ ውስጥ አልታየም። አሁንም ገና ፌስቲቫሎች ላይ እየቀረበ ነው። ከሁለት ዓመት በፊት ካናዳ፣ ቫንክሁቨር ላይ ዓለም አቀፍ የፊልምና የቴሌቪዥን ፌስቲቫል ላይ ታይቶ በምርጥ መሪ ተዋናይ ዘርፍ ተሸላሚ ሆኛለሁ።

በመሪ ተዋናይነት ብቻ ነው የተሳተፍከው?

ደበበ እሸቱ፡ በትርጉምም ተሳትፌያለሁ። ስክሪፕቱን (ፅሁፉን) ከእንግሊዝኛ በመመለስና ዳይሬክተሩን በማገዝም ተሳትፌያለሁ።

ከምናውቃቸው ሰዎች ማን ማን ተሳትፎበታል?

ደበበ እሸቱ፡ (ሳቅ) ከምታውቃቸው መካከል እኔ ብቻ ነኝ የተሳተፍኩበት።

ፈረንጆቹን አታውቃቸውም እያልከኝ ነው?

ደበበ እሸቱ፡(ሳቅ) አይደለም፤ ቤተ እስራኤሎቹን አታውቃቸውም ለማለት ነው። ደራሲውና ጸሐፊው ቤተ እስራኤላዊ ነው። ፊልም ሥራ ተምሯል። ሁለት ዘጋቢ ፊልሞች ሰርቷል። አንደኛው ተሸልሟል። ፕሮፌሽናል ኤዲተር ነው። የአይ ቲ ኤክስፐርት (ባለሙያ) ነው። በዳይሬክቲንግና በአክቲንግ (በተዋናይነት) ሁለት ዲግሪ አለው። አሁን ኢትዮጵያዊ ነኝ ነው የሚለው። ከእኔ ጋር ከተገናኘ በኋላ ሁለት ጊዜ ወደ ኢትዮጵያ መጥቷል።

Image copyright Getty Images
አጭር የምስል መግለጫ ደበበ እሸቱ እ.አ.አ. በ1973 'ሻፍት ኢን አፍሪካ' የተሰኘው ፊልም ላይ ከኔዳ አርነሪክ ጋር ሲተውን

ድምፅ ፈታዮቹ መረዋዎች

ማን ይባላል ስሙ?

ደበበ እሸቱ፡ባዚ ጌቴ ይባላል። በሕፃንነቱ ነው ወደ እስራኤል የሄደው። ከራሱ ሕይወት በመነሳት ነው ፊልሙን የፃፈው። በፊልሙ የሚያሳው የባህል ልዩነት በቤተሰብ ውስጥ የሚያመጣውን መለያየት ነው። ፊልሙ ለመጀመሪያ ጊዜ ቴልአቪቭ ውስጥ በዘጠኝ ሲኒማ ቤቶችና በዘጠኝ ቴሌቪዥኖች አንዴ ነው ለእይታ የበቃው።

የመክፈቻ ፕሮግራሙ መዝጊያ ላይ ቡና ሻይ እያልን ከእንግዶች ጋር ስንወያይ አንዲት ሁለተኛ ዲግሪዋን አጠናቅቃ ሦስተኛ ዲግሪዋን እየሠራች ያለች ቤተ እስራኤላዊት ወጣት መጥታ ከሚገባኝ በላይ አጥብቃ አመሰገነችኝ።

እኔም 'ምነው እንዲህ ምስጋናውን አጠነከርሽው?' ብዬ ስጠይቃት 'ፊልሙ ላይ ከአባቷ ጋር የተጣላችውን ልጅ ስመለከት የኔ ታሪክ መስሎኝ ነው' ብላ ነገረችኝ። 'ከአባቴ ጋር ሳንነጋገር ብዙ ዓመት ሆኖናል' አለች። 'አባትሽ ዛሬ አልመጡም?'ስላት፤ 'መጥተዋል' ብላ በርቀት ጠቆመችኝ።

ባሕልና ተፈጥሮን ያጣመረው ዞማ ቤተ መዘክር

ሄጄ አባትየውን 'ፊልሙን እንዴት አዩት?' ስላቸው 'ልጄንና እኔን አየሁበት፤ እግዚአብሔር ይስጥህ አስለቀስከኝ' አሉኝ።

'ታዲያ ለምን ልጅዎትን አያናግሯትም?' ብላቸው 'ከሷ ጋርማ በቃ ተለያየን' አሉኝ። 'አሁን ብትመጣስ?' ስላቸው 'ልጄ ነች አቅፌ እስማታለሁ' አሉ ከዚያ አገናኘኋቸውና ተላቀሱ። እና ሌሎች ሰዎችም እንዲህ እንዲያደርጉ ያስቻለ ፊልም ነው። ባዚ ጌቴ ይህንን እድል ስለሰጠኝ በጣም አመሰግነዋለሁ።

ከፊል በፊት ትተዋወቁ ነበር?

ደበበ እሸቱ፡ አንተዋወቅም። ሲፈልገኝና የተለያዩ ሰዎችን ሲጠይቅ (ሳቅ) ቃሊቲ ነበርኩ። ትምህርት ቤት ነበርኩ። ስለዚህ አላገኘኝም። ከቃሊቲ ከወጣሁ በኋላም ሰዎች አታገኘውም ብለውት ተስፋ አስቆርጠውት እንደነበር አጫውቶኛል። በኋላ ግን ቺካጎ የሚኖር አንድ ኢትዮጵያዊ ልጄን ፌስቡክ ላይ አግኝቷት 'የደበበ እሸቱ ልጅ ነሽ?' ብሎ ይጠይቃታል። እርሷም ሌላ ነገር ስለመሰላት 'ምን አገባህ?' ብላ ትመልስለታለች።

በኋላ ላይ 'አባትሽን እስራኤላውያን ለሥራ እየፈለጉት ነው' ብሎ ዝርዝሩን ሲያጫውታት 'ልጠይቀውና እሺ ካለኝ ስልኩን እሰጣችኋለሁ' ብላቸው አናገረችኝ። ከዚያ በኋላ ነው የደወሉልኝ። በንግግራችን መካከል እሺም እምቢም ከማለቴ በፊት ጽሁፉን ማየት አለብኝ አልኩ። ሲኖፕሲሱን (የፅሁፉን ጭብጥ) ላኩልኝ። እኔ በሲኖፕስስ አላምንም። ምክንያቱም በመካከል በርካታ ነገር ሊካተትበት ይችላል። ስለዚህ ሙሉ ጽሑፉን ላኩልኝ አልኳቸው፤ ላኩልኝ።

የፈረሰው የደጃዝማች ዐምዴ አበራ ቤት ጠባቂ ምን ይላል?

ከዚያ ትንሽ ፊልም ተቀርፀህ ላክልን አሉኝ። ላኩላቸው። ከዚያ በኋላ ግን ጠፉ። እኔም ትተውታል ብዬ ተቀምጬ ባለሁበት ካናዳ ልጄን ለመጠየቅ ከባለቤቴ ጋር በሄድኩበት ደወሉልኝ። ከዛም 'ኮንትራት ለመፈራረም ለንደን ና እኛም ለንደን እንመጣለን' አሉ። አልመጣም አልኩ። ኮንትራቱን ከተፈራረምኩ ወይ ኢትዮጵያ አልያም እስራኤል ነው መሆን ያለበት ብያቸው በዚያ ተስማምተን እስራኤል ሄጄ ተፈራረምን። ለመጀመሪያ ጊዜ የተገናኘነው እዚያ ነው።

ከኢትዮጵያ በብዛት በዓለም አቀፍ ደረጃ በሚሩ ፊልሞች ላይ ስትሳተፍ የማውቀው አንተን ነው። ከአንተ ውጪ በዓለም አቀፍ ፊልሞች ላይ የሚሳተፉ ሌሎች ኢትዮጵያውያን አሉ?

ደበበ እሸቱ፡ዘውዴ አርዓያ የምትባል ጣሊያን አገር ከፍተኛ እድል አግኝታ ፊልም የምትሠራ ኤርትራዊት አውቃለሁ።

ከኤርትራዊቷ ውጪ እዚህ ገር ያለኸው አንተ ነህ? (ሳቅ)

ደበበ እሸቱ፡ (ሳቅ) አይደለሁም። ሌሎችም ሊኖሩ ይችላሉ።

ቅድምስለቃሊቲ ስታነሳ 'ትምህርት ቤት ነበርኩ' አልክ። በርግጥ የቃሊቲ ቆይታህን እንደ ትምህርት ቤት ነው የምታየው?

ደበበ እሸቱ፡አዎ እንደ ትምህርት ቤት ነው የወሰድኩት።

ምን ተማርክበት?

ደበበ እሸቱ፡ ትዕግስትን ተምሬበታለሁ። ሲጋራ ከብዙ ዓመታት በኋላ ማቆም የቻልኩት ቃሊቲ ነው። ሰዎች እስር ቤት ሲጋራ ይለመዳል እንጂ ሲጋራ አይተውም ሲሉ ሞገቱኝ። እኔ ግን ማቆም እችላለሁ ብዬ አቆምኩኝ። አንድ ሰው በሚታሰርበት ጊዜ ሰው መሆኑ እንደሚጠፋ ተምሬበታለሁ። እስር ላይ ያለ ሰው የራሱ ሰው አይደለም። ሰዎች ናቸው እንዲቀመጥ እንዲነሳ፣ እንዲበላ፣ እንዲጠጣ፣ እንዲሄድ፣ እንዲቆምና እንዲያዘግም የሚነግሩት። የሚቆጣጠሩትም ከበላይ ያሉት ሰዎች ናቸው። እኛን ያጋጠሙን ደግሞ ክፉዎች ናቸው። ሊጎዱን ይሞክሩ ነበር። ግን ሳይደግስ አይጣላም ሆኖ ፖሊሶቹን በፍቅር አሸንፈናቸው ነበር።

ወመዘክር፡ ከንጉሡ ዘመን እስከዛሬ

በወቅቱ የነበሩት ኃላፊዎች ፖሊሶቹን በየወሩ ይቀይሯቸው ነበር። እኛ ጋር በተመደቡ ማግስት ደግሞ ከእኛ ጋር ወዳጅ ይሆናሉ። እኛ እንነግራቸው የነበረው እነሱ እንዳላሰሩን፣ እነሱ የኛ ጠባቂዎች ብቻ መሆናቸውንና የሚጠብቁንም ለኛ ደህንነት እንደሆነ ነበር። ስለዚህም በጠላትነት ከመፈራረጅ ይልቅ በኢትዮጵያዊነት ለመግባባት እንሞክር ነበር። ስለዚህ እኔ ትምህርት ቤት ነው ብዬ ነው የማየው።

በርካቶች አሁንም ድረስ አንተ ያለህበትን ተውኔት ለማየት ይጓጓሉልክ እንንተ ሰፍ የምንልለት ወጣት ተዋናይ ማየት ያልቻልነውለምንድን ነው?

ደበበ እሸቱ፡ መጀመሪያ እኔን አያችሁና ወደዳችኋ (ሳቅ) [ሌሎችም ተዋንያን] ግን አሉ።

ኖሩ አናያቸውም ነበር?

ደበበ እሸቱ፡ አሉ፤ በቴአትሩም በፊልሙም ላይ አሉ።

ከነሙሉዓለም ታደሰ እና ዓለማየሁ ታደሰ ወዲያ በቴአትሩ ላይ ስማቸው የሚነሳ ተዋናዮችአሉ?

ደበበ እሸቱ፡እነሱም እኮ የኔ እድሜ አይደሉም።

ነገር ግን ተተኪወጣትየምንላቸውም አይደሉም

ደበበ እሸቱ፡ በእርግጥ ወጣት አይደሉም። ችግሩን ግን ለይቶ ማወቅ ያስፈልጋል። እነዚህ ልጆች የሚያገኙት የወር ደመወዝ አነስተኛ በመሆኑ ከቴአትር ይልቅ ወደ ፊልም ያደላሉ። ክፍያው ቢስተካከልና ለመኖር የሚያስችላቸው ገቢ ቢያገኙ መድረክ ላይ ይቆዩ ነበር። በርካታ ባለሙያ መድረክ ላይ መታየት፣ መሥራት ይፈልጋል።

አሁን በቅርብ የተከፈተው 'መንታ መንገድ' አለ። ማንያዘዋል የተረጎመው 'እምዬ ብረቷ' ቴአትርም አለ። እዚያም ላይ ብዙ ልጆች አሉ። ግን ብዙ ፈተና አለው። ደሞዛቸው ቢስተካከልላቸውና ለመኖር የሚችሉበት ገቢ ቢያገኙ በርካታ ወጣት ተዋንያንን መድረኩ ላይ እናያለን። ደግሞ ወጣቶቹ ሀሳብ አላቸው። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባዘጋጁት 'ገበታ ለሸገር' የእራት ግብዣ ላይ እነሰለሞን ዓለሙ በሕንድ ተይዞ የነበረውን በመላ አገሪቱ ዛፍ የመትከል ክብረ ወሰን ሐምሌ 21 መስበር የሚያስችል ዘመቻ ለማካሄድ አስበዋል።

በታሪካዊው ቤተ መንግሥት ውስጥ ምን አለ?

ስንት ችግኝ ነው ለመትከል ያሰባችሁት?

ደበበ እሸቱ፡ሕንድ 100 ሚሊየን ዛፍ በመትከል ክብረ ወሰኑን ይዛለች። እኛ በመላ አገሪቱ ሁለት መቶ ሚሊየን ችግኝ ለመትከል ነው ያሰብነው።

በቅርብ ጊዜ ውስጥ በትወና ወይምበዝግጅት መድረክ ላይ እናይሀለን?

ደበበ እሸቱ፡በቴሌቪዥን አላየኸኝም?

አዎ፤ 'ደርሶ መልስ' ላይ

ደበበ እሸቱ፡አንድ ሰውም ቴአትር ትሠራልኛለህ ብሎኝ ጽሁፉን ለማየት እየጠበኩ ነው። ከወደድኩት እሠራዋለሁ። ካልወደድኩት አልሠራውም።

ስሙን የምናውቀው ደራሲ ነው?

ደበበ እሸቱ፡ እኔም አላውቀውም። (ሳቅ) አንድ ጥሩ ድርሰት አለኝ ብሎኛል፤ በኩራት። እኔም የምኮራበት ደራሲ ነው። ድርሰቱን ያምጣውና እንተያያለን።

ከአሁን በኋላ ከዚህ ሰው ጋር ሰርቼ በቃኝ የምትለው ሰው አለ?

ደበበ እሸቱ፡እኔ ቴአትር አይበቃኝም። መዐዛ ወርቁ እግዜር ይስጣት 'ደርሶ መልስ' ላይ ከማከብረው ዓለማየሁ ታደሰ ጋር እንድገናኝ አድርጋኛለች። ገና ከእስር ቤት እንደወጣሁ 'ጋሽ ደበበ አብረን እንሥራ ብሎኝ' ከሰለሞን ቦጋለ ጋርም ሠርተናል። ከሌሎቹም ጋር ብሠራ ደስ ይለኛል። እና ከእንግዲህ በኋላ ከእከሌ ጋር ብሠራ የምለው ሰው የለም።

ደበበ በጣምወደ መንግሥት እየተጠጋ ነው ብለው የሚተቹህ ሰዎች ገጥመውኛል።

ደበበ እሸቱ፡ደግ አደረኩ!

ለምን?

ደበበ እሸቱ፡ ነፃነቴን የሰጠኝ [ጠቅላይ ሚንስትር] ዐቢይ ነው። ሌላ ማን ሰጠኝ? ዶ/ር ዐቢይ ነው በነፃነት የመናገር መብቴን የመለሰልኝ። ዶ/ር ዐቢይ ነው ቤተ መንግሥት ያስገባኝ። ዶ/ር ዐቢይ ነው ፕሮግራም ምራልኝ ያለኝ። ከመሸማቀቅና ማን አየኝ ከሚል መሳቀቅና መገላመጥ ያወጣኝ ዶ/ር ዐቢይ ነው። ስለዚህ ያደላሁት ወደ መንግሥት ሳይሆን ወደ ዶ/ር ዐቢይ ነው። ለእሱ ደግሞ መልሴ ደግ አደረኩ ነው።

በርግጥ ጠቅላይ ሚኒስትሩን በዚህ መልክ የምትደግፋቸው ከሆነ ስህተት ሲሰሩ ብትመለከት ለመናገር ድፍረቱ ይኖርሀል?

ደበበ እሸቱ፡ መንገድ ፈልጌ እነግረዋለሁ። ለጠቅላይ ሚኒስትሩ እነግረዋለሁ እንጂ ከጀርባ አላማውም። ምክንያቱም በአንድ ቀን ሁሉንም ነገር መሥራት እንደማይችልና አንድ ሰው መሆኑን አውቃለሁ። በፊት ካሉት ሰዎች እሱ እያበላሸ ቢቀጥል ይሻለኛል። ሌላው ቢቀር ትንሽ የዲሞክራሲ ጭላንጭል አሳይቶኛል። እነዚያ 'ደበበ ከመንግሥት ጋር ገጥሟል' የሚሉ ከዚያኛው መንግሥት ጋር ገጥመው ይሆናል ስለዚህ ይናደዳሉ። የዶ/ር ዐቢይ ደጋፊ ሲያዩ አይናቸው ደም ይለብሳል።

ተያያዥ ርዕሶች

በዚህ ዘገባ ላይ ተጨማሪ መረጃ