ኢትዮጵያና ሌሎች ድሃ የአፍሪካ ሀገራት ለመድኃኒት ከዋጋው 30 እጥፍ ይከፍላሉ

እንክብል መድሀኒቶች Image copyright Getty Images

እንደ ኢትዮጵያ፣ ናይጄሪያ፣ ጋና፣ ኬኒያ ያሉ ሀገራት አንድ መድሀኒት ከሚያወጣው ዋጋ 30 እጥፍ እንደሚከፍሉ በቅርቡ ይፋ የሆነ ጥናት አስታወቀ።

የምጣኔ ሀብታቸው ከዝቅተኛ እስከ መካከለኛ የሆኑ የአፍሪካ ሀገራት ፍትኑነታቸው ዝቅተኛ ለሆነ መድሀኒቶች ከፍተኛ ገንዘብ ይከፍላሉ ሲሉ የተናገሩት የሲዲጂ ከፍተኛ የጤና ባለሙያ ናቸው።

እንደ ዛምቢያ፣ ሴኔጋል፣እና ቱኒዚያ ያሉ ሀገራት የሕመም ማስታገሻ የሆነውን ፓራሲታሞል ለመግዛት እንኳ አሜሪካና እንግሊዝ ከሚሸጥበት 30 እጥፍ ይከፍላሉ ብለዋል።

ጥናቱን ያካሄደው ሲዲጂ የተባለ መቀመጫውን አሜሪካ ያደረገ ድርጅት ሲሆን ከዝቅተኛ እስከ መካከለኛ ገቢ ያላቸው ሀገራት 'ብራንድ' የሆኑና ተመሳስለው የተሰሩ መድሀኒቶችን ለመግዛት ከፍተኛ ገንዘብ እያወጡ ነው ሲል ተናግሯል።

ክትባት ከየት ተነስቶ የት ደረሰ

በኬንያ ከኢቦላ ጋር የሚመሳሰሉ ምልክቶች ያለባት ታማሚ ተገኘች

ጥናቱን ካደረጉት ባለሙያዎች መካከል አንዷየሆነችው አማንዳ ግላስመን እንዳለችው በርካታ ሀገራት 'ብራንድ' የሆኑ መድሀኒቶች ለመግዛት ከፍተኛ ገንዘብ እያወጡ ሲሆን ነገር ግን በተቃራኒው ጥራታቸው የተረጋገጠ 'ብራንድ' ያልሆኑ ጄኔሪክ ተብለው የሚጠሩ መድሀኒቶችን በርካሽ ዋጋ ማግኘት ይችላሉ ብላለች።

'ብራንድ' የሆኑ መድሀኒቶች ሲባል ከፍተኛ ስምና ዝና ያላቸው የመድሀኒት አምራች ድርጅቶችን ስም ያዙ ማለት ብቻ ሲሆን መድሀኒቱን በማምረት ሂደትም ሆነ መድሀኒቱ በያዘው ፈዋሽ ንጥረ ነገር ላይ ምንም አይነት ድርሻ የለውም ስትል ታክላለች።

የመድሀኒት ገበያ በድሀ ሀገራት "እየሰራ አይደለም" ያሉት ከሴንተር ፎር ዴቬሎፕመንት የመጡት ካሊፕሶ ቻልኪዶ ናቸው።

እርሳቸው እንደሚሉት "የገበያ ውድድር የለም" ይህ ደግሞ የሆነው "የአቅራቢዎች ቅብብሎሹ በተወሰኑ ድርጅቶች ስለታጠረ ነው።"

በሚሰሩበት ድርጅት የአለም አቀፍ ጤና ፖሊሲ ዳይሬክተር የሆኑት ቻልኪዶ በቅርቡ አንድ ጥናት ከባልደረቦቻቸው ጋር በመሆን ይፋ አድርገዋል።

ሞሐመድ ሙርሲ ፍርድ ቤት ውስጥ ሞቱ

በጥናቱ ላይ ገቢያቸው ዝቅተኛና መካከለኛ የሆነ ሀገራት የመድሀኒት ፍጆታቸው የተወሰኑ ላይ ብቻ የሚያተኩር ነው። ይህም ደካማ የሆነ የገበያ ወድድር፣ ቁጥጥርና ጥራት እንዲኖር አድርጓል።

የበለጸጉ ሀገራት የህዝብ ገንዘብ እንዲሁም መድሀኒት ለመሸመት ያለው ውጣ ውረድ ጠንካራ ስለሆነ ርካሽ መድሀኒቶች ገበያው ላይ ይገኛሉ ሲሉ ይናገራሉ።

ድሀ ሀገራት ግን ውድ መድሀኒቶችን ገዝተው ይጠቀማሉ ነገር ግን በአሜሪካና በእንግሊዝ ያየን እንደሆነ ርካሽና ብራንድ የሌላቸው ጄኔሪክ ተብለው የሚጠሩ የመድሀኒት ውጤቶች በገበያው ላይ 85 በመቶ ድርሻ አላቸው።

በጣም ድሃ ሀገራት ለጋሽ ሀገራት መድሀኒት ሲገዙላቸው ተጠቃሚ ይሆናሉ፤ ምክንያቱም ያለ ማዘዣ የሚሸጡ መድሀኒቶች ዋጋቸው ዝቅ እንዲል ስለሚያደርግ ነው።

ቻልኪዶ እንደሚሉት ከድሃ እስከ መካከለኛ ገቢ ያላቸው ሀገራት "ዝቅተኛ ዋጋ ለማግኘት መደራደርና ጥራቱ የተጠበቀ ምርት ለማግኘት ይቸገራሉ" እንዲሁም በርካታ ዋጋውን የሚያንሩ ጉዳዮች አሉ የሚሉት ባለሙያዋ አንዳንዴ በግብርና እንዲሁም በሙስና ምክንያት ሊሆን ይችላል ሲሉ ያስቀምጣሉ።

የቁጥጥር ደረጃው በላላ ቁጥር የመድሀኒቱም ጥራት እየወረደ እንደሆነ ይገመታል ሲሉ ባለሙያዋ ያብራራሉ።

"የቁጥጥር አለመኖር ሰዎች መድሀኒቱ እንደማይሰራ እንዲሰማቸው ያደርጋል ስለዚህ ይሰራል ብለው ላሰቡት፣ ባይሰራም እንኳ፣ ተጨማሪ ገንዘብ ይከፍላሉ።"

የወጣው ጥናት የማጠቃለያ ሀሳብ ብሎ ያቀረበው አለም አቀፉ ማህበረሰብ ከሌላው ጊዜ በተለየ ትብብር እንዲያደርግ እና የዓለም አቀፉ ጤና ድርጅት የፖሊሲ ማሻሻያ እንዲደረግ ነው። ይህም በተመረጡ ሀገራት ላይ የመድሀኒት ግዢና አስተዳደር ላይ ማሻሻያ ለማድረግ ይረዳል።

በዚህ ዘገባ ላይ ተጨማሪ መረጃ