ደቡብ አፍሪካዊቷ የፓርላማ አባል የዘረኝነት ጥቃት ደረሰባት

ፑምዚሌ ቫን ዳሜ Image copyright Foto24

ደቡብ አፍሪካዊቷ የተቃዋሚ ፓርቲው የዲሞክራቲክ አሊያንስ ቃል አቀባይና የፖርላማ አባሏ ፑምዚሌ ቫን ዳሜ በኃገሪቱ ውስጥ አሉ ከሚባሉት የቱሪስት መናኸሪያ አንዱ በሆነው 'ቪኤ ዋተር ፍሮንት' በተሰኘው ስፍራ የዘረኝነት ጥቃት እንደደረሰባት ገልፃለች።

ፑምዚሌ ቫን ዳሜ በኬፕታውን ከተማ 'ቪኤ ዋተር ፍሮንት' የተባለውን ቦታ እየጎበኘችበት በነበረችበት ወቅት አንዲት ነጭ ሴት እንደሰደበቻት በትዊተር ገጿ አስፍራለች።

ደቡብ አፍሪካ ሚኒስትሯ በሩዋንዳ ጋዜጣ ሴተኛ አዳሪ ተብላ መሰደቧን ተቃወመች

በደቡብ አፍሪካ በየቀኑ 57 ሰዎች ይገደላሉ

በደቡብ አፍሪካ ዝቅተኛው የሠራተኛ ክፍያ 7ሺ ብር ሊሆን ነው

ስድቡ ምን እንደሆነ ግልፅ ያልተደረገ ሲሆን ነጯ ሴት ይቅርታ ጠይቂ ብትባልም በእምቢተኝነቷ እንደፀናች የፓርላማ አባሏ ገልፃለች።

"ከስፍራው በወጣሁበትም ወቅት ውጭ ላይ ሴትዮዋ ከቤተሰቦቿ ጋር ተሰባስባ በሚያስፈራራ መልኩ እያየችኝ ነበር፤ እናም ለምንድን ነው እንዲህ የምታይኝ ብየ ስጠይቃትም፤ ጥቁር ስለሆንሽ ነው የሚል መልስ ሰጥታኛለች" ብላለች።

ኤኤንሲ የአትሌቲክስ ፌዴሬሽኑን ውሳኔ 'ዘረኛ' ነው አለ

የፓርላማ አባሉ ሴት ባልደረባቸውን በመምታታቸው ተያዙ

ሴትዮዋ ብቻ ሳትሆን ልጇም እንደሰደባትና ጥቁር ስለሆነችም መሳደብ እንደሚችል የነገራት ሲሆን እየቀረፀችበት የነበረውንም ስልኳን መሬት ላይ በመወርወሩ ራሷንም ለመከላከል በቦክስ እንደመታችው ተናግራለች።

በቦታው የነበረው የጥበቃ አካል እንዳልደረሰላትም መግለጿን ተከትሎ የቦታው አስተዳደር በተገቢው መልኩ ምላሽ ባለመስጠታቸው ይቅርታ ጠይቀው ምርመራ እንደሚጀመር ገልፀዋል።

በዚህ ዘገባ ላይ ተጨማሪ መረጃ