ትራምፕ ጦርነት ከተጀመረ ኢራን ከምድረ ገጽ ትጠፋለች ሲሉ አስጠነቀቁ

የኢራን ቴሌቪዥን ተመትቶ ወደቀው ነው ያለውን ሰው አልባ አውሮፕላን አሳይቷል Image copyright IRIBNEWS
አጭር የምስል መግለጫ የኢራን ቴሌቪዥን ተመትቶ ወደቀው ነው ያለውን ሰው አልባ አውሮፕላን አሳይቷል

ፕሬዝዳንት ትራምፕ ከኢራን ጋር ጦርነት እንደማይፈልጉ ነገር ግን በሁለቱ ሃገራት መካከል ግጭት ከተጀመረ "ውድመት " እንደሚከሰት ተናገሩ።

አርብ ዕለት ለኤንቢሲ ቴሌቪዥን በሰጡት ቃለ ምልልስ አሜሪካ ከኢራን ጋር ለመነጋገር በሯ ክፍት መሆኑን አስታውቀዋል። ነገር ግን ኢራን የኒውክለር ጦር መሣሪያ እንዲኖራት እንደማይፈልጉ አልሸሸጉም።

በዚህ ሳምንት ኢራን የአሜሪካን ሰው አልባ አውሮፕላን መትታ መጣሏን ተከትሎ አሜሪካ የአፀፋ እርምጃ ልትወስድ ወስና በመጨረሻ ሰዓት ውሳኔያቸውን መቀልበሳቸውንም ተናግረዋል።

150 ኢራናያውያን ሕይወታቸውን ያጣሉ በሚል ውሳኔያቸውን እንዳጠፉት ጨምረው ተናግረዋል።

"ቃሊቲ ማረሚያ ቤት ትምህርት ቤት ሆኖኛል" ደበበ እሸቱ

ኮሎኔል መንግሥቱን ትግል ለመግጠም ቤተ መንግሥት የሄደው ደራሲ

"አልወደድኩትም፤ የአፀፋ እርምጃው ተመጣጣኝ ነው ብዬ አላሰብኩም" ብለዋል።

ኢራን ማክሰኞ ዕለት የአየር ክልሏን ጥሶ የገባውን የአሜሪካ ሰው አልባ አውሮፕላን መትታ መጣሏን ተናግራለች።

አሜሪካ ግን አውሮፕላኑ ዓለም አቀፉ የአየር ክልል ውስጥ ነበር ስትል ተከራክራለች።

በሁለቱ ሃገራት መካከል ውጥረቱ እየተጋጋለና እየተካረረ ሲሆን አሜሪካ በቅርቡ ሁለት ነዳጅ ጫኝ መርከቦች ላይ የደረሰውን አደጋ ኢራን ፈፅማዋለች ስትል መክሰሷ ይታወሳል

ኢራን ደግሞ በምላሹ አቋርጣው የነበረውን የኒውክሌር ማብላላት እንደምትቀጥልበትና ከተቀመጠላት መጠንም ከፍ እንደምታደርግ ገልፃለች።

ባለፈው ዓመት አሜሪካ እንዲሁም ሌሎች የአውሮፓ ሃገራት በ2015 ከኢራን ጋር የተፈራረሙትን ስምምነት አሜሪካ አልፈልግም ብላ መውጣቷ ይታወሳል።

አሜሪካ፤ የተባበሩት መንግሥታት የፀጥታው ምክር ቤት ሰኞ ዕለት ተገናኝቶ በኢራን ጉዳይ ላይ እንዲመክር ጥሪ አቅርባለች።

በዚህ ዘገባ ላይ ተጨማሪ መረጃ