ሳፋሪኮም የተጠቃሚዎችን መረጃ በማውጣት ተከሰሰ

ሳፋሪኮም Image copyright AFP

የኬንያው ግዙፍ ቴሌኮም ኩባንያ ሳፋሪኮም ሆን ብሎ የግል መረጃን የመጠበቅ መብት በመተላለፍ የ 11.5 ሚሊዮን ተጠቃሚዎችን መረጃ በማውጣት ተከሰሰ።

ኩባንያው የስፖርት ውርርድ መረጃዬን እንዲሁም የግለ ታሪኬን አደባባይ አስጥቶብኛል ያለ አንድ ተጠቃሚ ነው ሳፋሪኮምን ለመክሰስ የመጀመሪያውን እርምጃ የወሰደው።

ግለሰቡ የበርካታ ተጠቃሚዎችን ፊርማ በማሰባሰብ በኬንያ መዲና ናይሮቢ ወደ ከፍተኛው ፍርድ ቤት አምርቷል። ኩባንያው የግል መረጃዬን ሆን ብሎ አውጥቶብኛል ሲልም የአስር ሚሊዮን ዶላር ካሳ ጠይቋል።

ኢትዮጵያ እና ኤርትራ - ከሰኔ እስከ ሰኔ

የሰኔ 16ቱ ጥቃትና ብዙም ያልተነገረላቸው ክስተቶች

"እንዴት ለሴት ልጅ የወንዶች ክለብ ይሰጣል?' ተብሎ ነበር" መሠረት ማኒ

ሳፋሪኮም አባከነ የተባለው መረጃ ሙሉ ስም፣ የሞባይል ቁጥር፣ ፆታ፣ እድሜ፣ የመታወቂያ ቁጥር፣ የፓስፖርት ቁጥር እንዲሁም ምን ያህል ጊዜ የስፖርት ቁማር ላይ እንዳሳለፉ የሚያሳይ እንደሆነ ተገልጿል።

እስካሁን ሳፋሪኮም ስለ ጉዳዩ ያለው ነገር የለም።