ዘቢባ ዮኑስ (ዶ/ር )፡- ከበለስ ኤሌክትሪክ ለማመንጨት የምትመራመረዋ ሳይንቲስት

ዶክተር ዘቢባ የኑስ ኑሩ Image copyright ZEBIBI/FB

ዘቢባ የኑስ (ዶ/ር) በአዲግራት ዩኒቨርስቲ መምህርት ስትሆን ከበለስ ኃይል አመንጭቶ የኤሌክትሪክ አቅርቦት ባልደረሰባቸው አካባቢዎች የኃይል አማራጭ መፍጠር ላይ ምርምር እየሠራች ትገኛለች።

በቅርቡም ፍሌየር ዓለም አቀፍ ጥናት ፈንድ ከአፍሪካ የሳይንስ አካዳሚ ጋር በመተባበር የመሪነት አቅም ያላቸው አፍሪካውያን ተመራማሪዎችን ለማገዝ ባዘጋጀው ውድድር ላይ አሸንፋ ተሸልማለች።

ፍሌየር በሮያል ሶሳይቲ የሚደረግ ፈንድ ነው።

"ይህ ፈጠራ ወደፊት ብዙ ነገሮችን እንደሚቀይር ከአሁኑ መናገር እችላለሁ።''

በውድድሩ ላይ በታዳሽ ኃይል፣ የምግብ ዋስትና፣ ውሀ እና ጤና ላይ ያተኮሩ የምርምር ሥራዎች የያዙ 700 ተመራማሪዎች ለውድድር አመልክተው እንደነበር ዘቢባ የኑስ (ዶ/ር) ትናገራለች።

ዘቢባ (ዶ/ር) በዚህ ውድድር ያሸነፈች ቀዳሚዋ ኢትዮጵያዊት ሳይንቲስት ስትሆን 300 ሺ ፓውንድ ወይም 12 ሚሊዮን ብር ተሸልማለች።

ብዙዎች በማይደፍሩት ፊዚክስ መከሰት

በፊዚክስ እና ሂሳብ የላቀ ችሎታ እንደነበራት ትናገራለች። የዘቢባ የኑስ (ዶ/ር) አባትና እናት አስተማሪዎች ስለሆኑ 'የአስተማሪ ልጅ አይሰንፍም' እየተባለች ለትምህርቷ ትኩረት እየሰጠችና ከእኩዮቿ ጋር እየተፎካከረች ማደጓን ትናገራለች።

የሁለተኛ ደረጃ መልቀቂያ ፈተና ስትወስድ ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚያስገባት ጥሩ ውጤት አምጥታ ጅማ ዩኒቨርሲቲ ተመደበች። ሆኖም የተመደበችበት ትምህርት ክፍል የምትፈልገው አልነበረምና አዘነች።

የሃምዛ ሃሚድ ገመድ አልባ የኤሌክትሪክ ማስተላለፊያ

ሀዘኗ ትምህርቷን ለማቋረጥ እስከመወሰን የደረሰ ነበር። ዘቢባ (ዶ/ር) "ፊዚክስ ማጥናት አልፈለግኩም" ትላለች።

ለምን?

"ሕብረተሰቡም ቤተሰባችንም ሲያሳድገን በተለያዩ የትምህርት ክፍሎች ውስጥ ገብተን እንድንማር ሳይሆን ሀኪም፣ ፓይለት. . . እንድንሆን ነበር የሚነግረን? እና እኔም ሀኪም መሆን አለብኝ ብዬ ነበር የደመደምኩት።"

ፊዚክስና ሂሳብ እንደ ውሀ ፉት የምትለው የትምህርት ዓይነት መሆኑን የምትናገረው ዘቢባ (ዶ/ር) በፊዚክስ የመቀጠሉን ነገር ግን ልቧ አልፈቀደውም።

ያኔ አባቷ "አቅሙ ስላለሽ ጥሩ ውጤት ማምጣት ትችያለሽ" በሚል መከሯት፤ ባይዋጥላትም አይንዋን ጨፍና መቀጠልን መረጠች።

የታኘከ ማስቲካ ዳግም ነብስ ሲዘራ

ነገር ግን ልቧ ያለው ሕክምና ማጥናት ላይ ስለነበር ለትምህርቷ እምብዛም ትኩረት አልሰጠችም።

ትምህርቷን አጠናቅቃ ሥራ በምትፈልግበት ወቅት ዩኒቨርሲቲ ውስጥ ያገኘችው ውጤት ዝቅተኛ ስለነበረ፤ ሥራ ካገኘች በኋላ የሚመጡ የትምህርት እድሎች ላይ እንቅፋት ሆነባት።

"በዛ ሰዓት እጅግ ቆጨኝ። አቅም እያለኝ ለምን በቸልተኝነት እንዲህ አደረግኩኝ አልኩ። በእርግጥ በመቀሌ የመምህራን ኮሌጅ ሥራ ጀምሬያለሁ፤ ግን ሁልግዜ የትምህርት እድል፣ የሥራ እድገት ወይም ሌላ ሲኖር ነጥብ ላይ ትኩረት ያደረገ ስለነበር ቆጨኝ። በዚህ ራሴን እወቅስ ነበረ" ትላለች።

መምህራን ኮሌጅ ውስጥ ሁለት ዓመት ካስተማረች በኋላ፣ ሁለተኛ ዲግሪዋን ለመማር ወደ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አቀናች።

አሁን ደግሞ ምርጫዋ ወደ ሥርዓተ ጾታ አደላ። ሆኖም 'የፊዚክስ መምህርት ብለን ስለቀጠርንሽ በፊዚክስ ነው የምትቀጥይው' ስለተባለች በዛው ገፋችበትና ሁለት ዓመት ሙሉ ሲቆጫት የነበረውን አካካሰች።

Image copyright Zebiba

አዲስ አበባ፡ የፈጠራ ማዕከል ለመሆን እየጣረች ያለች ከተማ

"በጊዜው እልህ ስለነበረኝ የምችለውን ሠርቼ ጥሩ ውጤት ይዤ ተመረቅኩ። የመመረቂያ ጽሁፌን ሥሰራ ከሌላው ጊዜ በይበልጥ ደስ እያለኝ ስለሠራሁ፣ ደስ የሚል ስሜት ይዤ ነጻ የትምህርት እድሎች በጎን መፈለግ ጀመርኩኝ።"

ጥረትዋ አላሳፈራትም፤ በደቡብ አፍሪካ 3ኛ ዲግሪዋን የምትከታተልበት ነጻ የትምህርት እድል አገኘችና ወደዚያው አቀናች።

"ልጄን ላጠባ ስመላለስ ነበር"

ፍሌየር ወደ መሬት ወርደው የህብረተሰቡን ችግር የሚፈቱ የምርምር ሀሳብ ያለቸው ምሁራንና ተመራማሪዎችን አወዳድሮ የገንዘብ ሽልማት ሲሰጥ የመጀመሪያው ነው።

ዶ/ር ዚቢባ የዚህ ውድድር እጩና አሸናፊ ያደርገኛል የምትለው ይሄ ነው የሚባል መረጃ ፈጽሞ አልነበራትም። አንድ እምነት ያሳደረባት ወዳጅዋ ግን ለውድድሩ ጋበዛት።

"በወሊድ ምክንያት እረፍት ላይ ነበርኩኝ። በተለያዩ አገራት ከሚገኙ ሰዎች ጋር ስለምሠራ አንዱ 'ይሄንን እድል ልታገኚው ስለምትችይ ተሳተፊ' የሚል መልእክት [ኢሜይል] ላከልኝ።"

ግን ደግሞ አጭር ጊዜ የሚጠይቅና በቀላሉ የሚያልቅ ዝርዝር አይደለም የጠበቃት።

በወቅቱ ወልዳ አራስ ቤት ነበረች።

"ዓላማችን ችግሮችን ፈተን ገንዘብ ማግኘት ነው " የጠብታ አምቡላንስ ባለቤት

መብራትና ኢንተርኔት ደግሞ በተደጋጋሚ የሚቆራረጥበት ጊዜ ነበር። ፎርሙ ደግሞ ኢንተርኔት ካለበት ቦታ ውጪ የሚሞላ አይደለም።

"አማራጭ ስላልነበረኝ ልጄን እናቴ ጋር ትቼ እየሄድኩ ከዛም ለማጥባት ከዩኒቨርስቲ ቤት እየተመላለስኩ ፎርሙን ሞላሁ። ግን በስጋት ውስጥ ሆኜ ስለሞላሁት ብዙም ተስፋ አላደረግኩም።"

ድካሟን የሚክስና ስጋትዋን በደስታ የሚተካ ብስራት ከወደ ኬንያ ሰማች። ያስገባችው ወረቀት ተመረጠ፤ አሸነፈች።

ፍሌየር ተመራማሪዎቹ በሚያገኙት የሽልማት ገንዘብ የራሳቸውን ቤተ ሙከራ ከፍተው የተሻለ እንዲሠሩና ልምድ ካላቸው ሰዎች እየተገናኙ በትብብር እንዲሠሩ ይፈልጋል።

ለዚህ ከመረጣቸው አንዷ የሆነችው ዶ/ር ዚቢባንም የ12 ሚሊዮን ብር ተሸላሚ አደረጋት።

"ፊዚክስና ሴት"

'ሴት ስለሆነች እንዲህ ያለ ነገር ይከብዳታል' ከሚል አግላይና ጨቋኝ አገላለጽ እስከ 'የመጀመሪያዋ ሴት ተሸላሚ ወይም 'ሴት ሳይንቲስት' የሚሉ ጾታን መሰረት ያደረጉ ተቀጽላዎችን ዶ/ር ዘቢባ ትተቻቸዋለች።

በዓለምም ሆነ በአገራችን ሴቶች ይከብዳቸዋል የሚባለው የጉልበት ሥራ ብቻ አይደለም የምትለው ዘቢባ (ዶ/ር)፤ በትልልቅ ተቋማት ሳይቀር ትምህርት ክፍሎች ተለይተው ለሴቶች አይሆኑም ስለሚባሉ በፊዚክስና ሂሳብ ጎልተው የሚወጡ ሴቶች ቁጥር ጥቂት ነው ትላለች።

"ሥራ በጾታ፣ ጾታ ደግሞ በሥራ አይገልጹም" የምትለው ዶ/ር ዘቢባ፤ "በፊዚክስ ስቀጥል ብዙ ጓደኞቼና የማያውቁኝ ሰዎች 'ትችለዋለች ግን?' 'ከባድ'ኮ ነው'፤ ሲሉ ነበር። ይህ ልክ አይደለም" ትላለች።

ሴቶች በብዛት ወደ ፊዚክስ ወይም ሂሳብ እንዳይገቡ የሚያደርግ ማህበረሰባዊ ጫና አለ ብላ የምታምነው ዘቢባ (ዶ/ር)፤ ሁለቱም 'ከባድ ስለሆኑ ወንዶች ናቸው የሚችሉት' የሚለው ኋላ ቀር አመለካከት የሚፈጥረው ስሜት ሴት ልጅ በነጻነት እችለዋለሁ ብላ እንዳትገባ ጫና እንደሚፈጥርባት ትናገራለች።

ዶ/ር ዘቢባ "ሴቶች በተፈጥሯችን ብዙ ነገር አንድ ላይ ማስኬድ እንችላለን" በማለት "ቢከብደኝም እንኳ የሚያግዘኝ ባለቤት አለኝ። ባለቤቴ በሞራል፣ በሀሳብና በሌሎችም ስለሚያግዘኝ አመሰግነዋለሁ። ከምንም ነገር በላይ ግን ግዜን በአግባቡ መጠቀም ወሳኝ ነው" ትላለች።

ይሁን እንጂ ዶ/ር ዘቢባ አልወደድኩትም ብላ ለመተው አቆብቁባ በነበረው ትምህርት ዘርፍ ዘልቃ፤ ላለፉት ዓመታት በታዳሽ ኃይል በተለይ ደግሞ የጸሃይ ብርሃን ላይ ትኩረት ያደረጉ የምርምር ጽሑፎች በዓለም አቀፍ ጆርናሎች ላይ አሳትማለች።

በዚህ ዘገባ ላይ ተጨማሪ መረጃ