ኒውዝላንዳውያን "ጦር መሣሪያ አንፈልግም" እያሉ ነው

የጦር መሣሪያ Image copyright Getty Images

ከኒውዝላንድ ክራይስርቸርች ጥቃት በኋላ መሣሪያ መታገዱን ተከትሎ፤ ኒውዝላንዳውያን ከፊል አውቶማቲክ መሣሪያቸውን ማስረከብ ጀምረዋል።

መሣሪያ የታጠቀ ግለሰብ መስጅድ ውስጥ በሰነዘረው ጥቃት 51 ሰዎች መግደሉ ይታወሳል።

ኒውዝላንዳውያን መሣሪያቸውን እያስረከቡ ያሉት ክራይስትቸርች መስጅድ ውስጥ ሲሆን፤ በቀጣይ በመላው አገሪቱ 250 የመሣሪያ መሰብሰቢያ ይኖራል።

ከክራይስትቸርች የመስጊድ ጥቃት በተአምር የተረፈው ኢትዮጵያዊ

እስካሁን 224 መሣሪያ ላስረከቡ 169 የመሣሪያ ባለቤቶች 230,000 ዩሮ ካሳ ተከፍሏል። መሣሪያዎቹ እንዲወድሙም ተደርጓል።

የፖሊስ ኮማንደር ማይክ ጆንሰን እንደተናገሩት፤ ዜጎች በጎ ምላሽ እየሰጡ ይገኛሉ። 900 የመሣሪያ ባለቤቶች 1,415 ሽጉጥ ለመመለስ መመዝገባቸውንም አክለዋል።

የኒውዚላንድ ጠቅላይ ሚኒስትር አድናቆት እየጎረፈላቸው ነው

አንድ የመሣሪያ ባለቤት ለአደን ይጠቀሙበት የነበረውን ሽጉጥ አስረክበው 6,900 ዩሮ ካሳ ተሰጥቷቸዋል። በሂደቱ ደስተኛ እንደሁኑም ተናግረዋል።

በእርግጥ መሣሪያ የመሰብሰቡ ነገር ሁሉንም የህብረተሰቡ ክፍል አላስደሰተም።

ቪንሰንት ሳንደርስ የተባሉ ግለሰብ መቶ ዓመት እጃቸው ላይ የቆየና የአያታቸው ንብረት የነበረ መሣሪያ አላቸው። መንግሥት መሣሪያ ለመሰብሰብ ቅድመ ማስጠንቀቂያ የሰጠው ለሁለት ቀናት ብቻ እንደሆነና ሂደቱ እንደተጣደፈ ይናገራሉ።

የኒውዝላንድ መንግሥት ለመሣሪያ መላሾች በአጠቃላይ 110 ሚሊየን ዩሮ ካሳ መድቧል።

ወታደራዊ ከፊል አውቶማቲክ መሣሪያዎች እንዲሁም መሣሪያ ለመገጣጠም የሚውሉ ቁሳቁሶች የታገዱት ሚያዝያ ላይ ነበር። በወቅቱ የአገሪቱ ጠቅላይ ሚንስትር ጃሲንዳ አርደን በሕዝብ እንደራሴዎች ፊት በስሜት ተሞልተው "እርምጃው መወሰድ ያለበት ትክክለኛ ጊዜ አሁን ነው" ማለታቸው ይታወሳል።

ተያያዥ ርዕሶች