በሲዳማ ክልልነት ጉዳይ ህዝበ ውሳኔ እንዲካሄድ የምርጫ ቦርድ ወሰነ

ወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳ

በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልላዊ መንግሥት ምክር ቤት የሲዳማ ዞንን የክልልነት ጥያቄን ለመወሰን በአምስት ወራት ውስጥ ህዝበ ውሳኔ እንዲካሄድ የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ መወሰኑን የሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።

ህዝበ ውሳኔውንም ለማካሄድ ዝግጅት መጀመሩንም ምርጫ ቦርድ አስታውቋል።

ምርጫ ቦርድ በቀጣይ ለሚካሄደው ምርጫ 3.7 ቢሊዮን ብር ጠየቀ

የምርጫ ቦርድ መግለጫ እንደሚያስቀምጠው፡

ከቦርዱ የሚጠበቁ ተግባራት፦

•የህዝበ ውሳኔ አካሄድ የሚመራበት የስነስርአት መመሪያ ማዘጋጀት

• የህዝበ ውሳኔ አጠቃላይ ጊዜ ሰሌዳና በጀት ማዘጋጀት

• በህዝበ ውሳኔ ዝግጅትና ድምፅ መስጠት ሂደት ስለሚኖረው የፀጥታ አጠባበቅ ሁኔታ ግብረ ሃይል ማደራጀትና ዕቅድ ማፅደቅ

• ገለልተኛ የምርጫ አስፈፃሚዎች መመልመል፣ ማሰልጠንና ማሰማራት

• ከባለድርሻ አካላት ጋር የጋራ መድረክ ማዘጋጀት፣ የድርጊት መርሃ ግብር ማውጣት

• በህዝበ ውሳኔ አፈፃፄም ሂደቱ ላይ የጋራ ምክክር መርሃ ግብሮችን አውጥቶ መተግበር

• የሰነድና ቁሳቁስ ዝግጅትና ህትመት ስራዎች ማከናወን

• ድምፅ መስጫ ወረቀቶችና ፖስተሮች ማዘጋጀት፣ ማሳተም፣ ማሰራጨት

• ህዝበ ውሳኔ ድምጽ ማሰጠት

• ቆጠራና ውጤት ማሳወቅ

ከሌሎች ባለድርሻ አካላት የሚጠበቁ ተግባራት፦

ለሲዳማ ክልልነት 'ይሁንታ ተሰጠ' በሚል በርካቶች ደስታቸውን እየገለጹ ነው

ሲሆኑ በሌላ በኩል ሂደቱ የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላትም የሚጠበቅባቸውን ዝግጅት ማድረግ ይኖርባቸዋል፡፡በዚህም መሰረት፦

1. የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልል ምክር ቤት ከክልሉ መንግስትና ከዞኑ መስተዳደር ጋር በመመካከር በአሁኑ ወቅት የክልሉም የዞኑም አስተዳደር ዋና ከተማ ሆና የምታገለግለው የሀዋሳ ከተማ የህዝበ ውሳኔው ውጤት የሲዳማን ክልል መሆን የሚያረጋግጥ ቢሆን በከተማዋ ላይ ሁለቱ አካላት የሚኖራቸውን መብትና ከዚህ ጋር በተያያዘ የሚነሱ የሃብት ክፍፍል ጥያቄዎችን የሚያስተናግዱበትን አሰራር አዘጋጅተው ለቦርዱ እንዲያሳውቁ

2. በአዋጅ 532/1999 አንቀጽ 107 በተጠቀሰው የትብብር ድንጋጌ መሰረት የህዝበ ውሳኔው ጸጥታና ደህንነትን ( electoral security) ማስጠበቅን አስመልክቶ የፌደራል ፓሊስ፣ የክልሉ ፓሊስና የዞኑ ፓሊስ በትብብር የሚሰሩበትን ዝርዝር እቅድ እንዲያወጡና ከቦርድ ጋር ተባብረው እንዲሰሩ

ጃኮብ ዙማ የሞት ማስፈራሪያ እንደደረሳቸው አስታወቁ

3. የደቡብ ክልል ምክር ቤት በሲዳማ ዞን የሚኖሩ የተለያዩ የሌሎች ብሄር ብሔረሰብ አባላት ከህዝበ ውሳኔው በኋላ የሚኖራቸውን ህጋዊ የመብቶች ጥበቃ አስመልክቶ ግልጽ አስተዳደራዊና ህጋዊ ማእቀፍ እንዲያዘጋጅና ለቦርዱ እንዲያሳውቅ ምርጫ ቦርድ የወሰነ ሲሆን ከዚህም በተጨማሪ የሚመለከታቸው አካላት ከላይ የተጠቀሱት ጉዳዮች ላይ ያላቸውን ምላሽ እስከ ሐምሌ 19 ቀን 2011 ዓ.ም በጽሁፍ እንዲያሳውቁ ወስኗል፡፡

በዚህ አጋጣሚ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በህገ መንግስቱና በምርጫ አዋጁ የተሰጠውን ሃላፊነት አለም አቀፍ የምርጫ መሰረታዊ መርሆዎች ጋር በማጣመር ሃላፊነቱን ለመወጣት ከፍተኛ ጥረት እያደረገ እንደሚገኝ ለመግለጽ ይወዳል፡፡

ተያያዥ ርዕሶች