እስራኤል በቁፋሮ መስጂድ አገኘች

በእስራኤል በረሀ ጥንታዊ መስጂድ ተገኘ። Image copyright Getty Images
አጭር የምስል መግለጫ መስጂዱ የተገኘው በእስራኤሏ ኔጌቭ በረሃ በምትገነው ራሀት ቤዱዌን ከተማ ነው

በእስራኤል ኔጌቭ በረሀ አርኪኦሎጂስቶች 1200 ዓመት ዕድሜ ያለው መስጂድ በቁፋሮ ማግኘታቸው ተነገረ። መስጂዱ ዓለም ላይ ጥንታዊ ከሚባሉት መካከል እንደሚመደብ ተገልጿል።

ወደ ሰባተኛውና ስምንተኛው ክፍለ ዘመን ዕድሜያቸውን የሚቆጥሩ ቅሪቶች የተገኙት በራሀት ቤድዌን ከተማ ነው።

ከላሊባላ ጥገና ጀርባ ያለው ማን ነው ?

የእስራኤል ቅርስ ጥበቃ እንዳለው፤ መስጂዱ ሊገኝ የቻለው በአካባቢው ለግንባታ ተብሎ ቁፋሮ በሚካሄድበት ወቅት ነው።

Image copyright Israel's Antiquities Authority
አጭር የምስል መግለጫ መስጂዱ የተገኘው በአካባቢው ግንባታ ለማካሄድ ቁፋሮ በሚደረግበት ወቅት ነው
Image copyright Getty Images
አጭር የምስል መግለጫ ሙስሊሞች አዲስ በተገነው ጥንታዊ መስጂድ ውስጥ ሲሰግዱ

"በአካባቢው በዚህ ክፍለ ዘመን የነበረ እና በመካ እና እየሩሳሌም ከተገኙት መስጂዶች ጋር በእድሜ የሚፎካከር ቅርስ ነው" ሲል የእስራኤሉ የቅርስ ጥበቃ መሥሪያ ቤት ተናግሯል።

ቁፋሮውን የመሩት ባለሙያዎች በበኩላቸው መስጂዱ "በዓለማችን የትኛውም ጥግ ከተገኙት ሁሉ ለየት ያለው ነው" ብለዋል።

የመስጂዱ ምዕመናኖችም የአካባቢው ገበሬዎች ሊሆኑ እንደሚችሉ ያላቸውን ግምት ተናግረዋል።

Image copyright Getty Images
አጭር የምስል መግለጫ የእስራኤል የቅርስ ጥበቃ ባለስልጣን ባልደረባ ስለ ግኝቱ ዝርዝር ማብራሪያ ሲሰጡ

መስጂዱ ጣሪያ የሌለው ሲሆን፤ በአራት መአዘን ቅርፅ የታነፀ ነው። ፊቱን ወደ ሙስሊሞች ቅድስቷ ከተማ መካ ያዞረ መስገጃ አለው።

"ይህ የመስጂዱ አቀማመጥ ከበርካታ መቶ ዓመታት በፊት ሙስሊሞች በዚህ መስጂድ ውስጥ ይሰግዱ እንደነበር ምስክር ነው" ብለዋል የቅርስ ጥበቃ መሥሪያ ቤቱ ባልደረባ።

Image copyright Getty Images
አጭር የምስል መግለጫ የእስራኤል የቅርስ ጥበቃ መሥሪያ ቤት ባልደረባ በሥራ ላይ

የእስልምና ታሪክን እንዳጠኑት ባለሙያዎች ከሆነ ይህ መስጂድ እስልምና ወደ አሁኗ እስራኤል በመጣበት የመጀመሪያዎቹ ዓመታት የተገነባ ቀደምት መስጂድ ነው ተብሎ ይታመናል።

አክለውም በዚያ ዘመን የነበረውን ሁኔታ የበለጠ ለማወቅ "የዚህ መስጂድ በአካባቢው መገኘት የሚያበረክተው አስተዋፅኦ ከፍ ያለ ነው" ይላሉ።

አደጋ የተጋረጠበት የአፄ ፋሲለደስ ቤተ መንግሥት

የሠላም ተጓዧ ሉሲ (ድንቅነሽ) ምን ደረሰች?