ምግብ ወሲብን የተሻለ ያደርጋል?

ቃርያ Image copyright Getty Images

ወሲብና ምግብን ምን ያገናኛቸዋል? ብለው ይጠይቁ ይሆናል። ተመራማሪዎች እንደሚሉት አመጋገባችን እና የወሲብ ሕይወታችን ቀጥተኛ ትስስር አላቸው።

ደስታ የሚፈጥር ንጥረ ነገር ያላቸው ምግቦች ጤናማ የወሲብ ሕይወት እንዲኖረን ያደርጋሉ። ከነዚህ ምግቦች ጥቂቱን እናስተዋውቃችሁ።

1. ቃርያ፣ ሚጥሚጣ. . .

ካፕሳይሲን የሚባለው ንጥረ ነገር ቃርያ፣ ሚጥሚጣ በመሰሉ የሚያቃጥሉ ምግቦች ውስጥ ይገኛል። ሰዎች ደስታ ሲሰማቸው የሚመነጨው ኢንዶርፊን ሆርሞን እንዲዘዋወር ቃርያና ሚጥሚጣ ያግዛሉ።

በተጨማሪም የደም ዝውውርን ያፋጥናል። የሰውነት የሙቀት መጠንና የልብ ምት ፍጥነት እንዲጨምርም ይረዳል። እነዚህ በወሲብ ወቅት ሰውነታችን ላይ የሚስተዋሉ ለውጦች ናቸው።

ለወሲብ ትክክለኛው ዕድሜ የቱ ነው?

2. ቸኮሌት

Image copyright Getty Images

ቸኮሌት ፊኒሌትያላሚን የሚባል ንጥረ ነገር አለው። ቸኮሌት መብላትና በፍቅር መክነፍ የሚያያዙትም በዚህ ንጥረ ነገር ምክንያት ነው።

ንጥረ ነገሩ የፍቅር ግንኙነት ሲጀመር ደስ የሚል ስሜት እንዲፈጠር ያደርጋል። ቸኮሌት ውስጥ ትራይፕቶፋን የተባለ አሚኖ አሲድ ይገኛል። ይህም ሰውነት ውስጥ ደስታ የሚያመነጭ ሴሮቶይን የሚባል ንጥረ ነገር እንዲዘዋወር ይረዳል።

ትራይፕቶፋን ከእንቁላል፣ ከለውዝ፣ ከሶያ ምርቶችም ሊገኝ ይችላል።

ኢንተርኔትን የሚሾፍረው የወሲብ ፊልም ይሆን?

ቸኮሌትና የወሲብ ሕይወት መካከል ግንኙነት አለ መባል የጀመረው ከ16ኛው ክፍለ ዘመን አንስቶ ነው።

3. አልኮል ወሲብን የተሻለ ያደርጋል?

Image copyright Getty Images

አልኮል የወሲብ ተነሳሽነትን ቢጨምርም፤ የግብረ ሥጋ ግንኙነት በሚደረግበት ወቅት ተጽዕኖ ሊያሳድርም ይችላል። ተመራማሪዎች እንደሚሉት፤ ከመጠን በላይ መጠጣት የወሲብ ፍላጎትን ይቀንሳል።

የአልኮል ሽታ ስለሚረብሽም የወሲብ ሕይወት ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ሊያሳድር ይችላል።

እንግሊዛውያን የወሲብ ሕይወታቸው ''ደካማ ነው'' ተባለ

4. ፍራፍሬዎችስ?

ጥናቶች እንደሚያሳዩት የብልት አለመቆም ችግር ያለባቸው ወንዶች ፍላቮኖይድ የተባለ ኬሚካል የያዙ ምግቦች እንዲመገቡ ይመከራል።

ለምሳሌ ብሉቤሪ የተባለ የእንጆሪ ዝርያ፣ ብርቱካንና ሎሚም ችግሩን ይቀርፋሉ።

የተለያዩ ፍራፍሬዎችን መመገብ የብልት አለመቆም ችግርን 14% ይቀንሳል።

የአለም የምግብ ቀን: አስገራሚ የአለማችን ምግቦች

ከአትክልት፣ ፍራፍሬዎች፣ የወይራ ዘይትና ለውዝ በተጨማሪ የሜዲትራኒያን አካባቢ ምግቦች የብልት አለመቆም ችግርን እንደሚቀርፉም ተመራማሪዎች ይናገራሉ።

ቼሪ፣ ብላክቤሪ የተባለው የእንጆሪ አይነት፣ የወይን ፍሬ እና ቀይ ጥቅል ጎመን አንቶካይኒን የያዙ ምግቦች ናቸው።

ሲጠቃለል. . .

የወሲብ ሕይወትን እንደሚያሻሽሉ የሚነገርላቸው አፍሮዲሲያክ የተባሉ ምግቦችን በሦስት ከፍሎ ማየት ይቻላል። አንደኛው የወሲብ ፍላጎት፣ ሁለተኛው ወሲብ የመፈጸም ብቃትና ሦስተኛው ከወሲብ የሚገኝ ሀሴት ናቸው።

በእርግጥ ተመራማሪዎች እነዚህን ውጤቶች መለካት አልቻሉም። እንዲያውም እስካሁን በእርግጠኛነት መናገር የቻሉት አፍሮዲሲያክ የቆዩ ፍራፍሬዎችን ሽታ ነው።

ዶ/ር ክሪችማን የተባሉ የተባሉ የሥነ ተዋልዶ ጤና ተመራማሪ እያንዳንዱ ሰው የተሻለ የወሲብ ሕይወት እንዲኖረኝ ረድቶኛል የሚለውን ምግብ እንዲያዘወትር ይመክራሉ።

አብዛኞቹ አፍሮዲሲያክ የሚባሉ ምግቦች ጤናማ ምግቦች ናቸው። ወሲብ የተሻለ እንዲሆን ይረዳሉ የሚባሉ ነገር ግን ጤናማ ያልሆኑ ምግቦችን አለመጠቀም ይመከራል።

አንዳንዴ የወሲብ ፍላጎት አናሳ ሲሆን ከጤና ችግር ጋር ሊያያዝ ስለሚችል ሀኪም ማማከር ያሻል።

ተያያዥ ርዕሶች