ደቡብ ኮሪያና ጃፓን ለሩሲያና ቻይና ምላሽ የጦር ጀት ላኩ

የሩሲያ A-50 የቅድመ ትንቃቄ የጦር አውሮፕላን Image copyright Getty Images

ሩሲያ ከቻይና ጋር በጥምረት የአየር ላይ ቁጥጥር ልምምድ ማድረጓን ስታስታውቅ፤ ደቡብ ኮሪያና ጃፓን ደግሞ በምላሹ የጦር ጀቶቻቸውን ልከዋል።

የሩሲያ መከላከያ ሚኒስትር አራት ቦምብ ጣይ አውሮፕላኖች ከተዋጊ ጄት ጋር በመሆን በጃፓንና በምሥራቅ ቻይና ባህር ላይ በእቅድ ተይዞ የነበረ የቅኝት ልምምድ ማድረጋቸውን አስታውቀዋል።

ደቡብ ኮሪያ በበኩሏ የሩሲያ አውሮፕላን የአየር ክልሏን ጥሶ በመግባቱ የማስጠንቀቂያ ተኩስ መተኮሷን ተናግራለች። በክስተቱ ላይ ጃፓን ደቡብ ኮሪያና ሩሲያ ላይ ተቃውሞዋን አሰምታለች።

ኢራን የ 'ሲአይኤ ሰላይ' ያለቻቸውን በሞት እቀጣለሁ አለች

"አዲስ አበባ የምንወዛገብባት ሳትሆን በጋራ የምንኖርባት ከተማ ናት" ም/ከንቲባ ታከለ ኡማ

ፍጥጫው የተነሳው ደቡብ ኮሪያ በምትቆጣጠረውና ጃፓን የይገባኛል ጥያቄ በምታነሳበት ዶክዶ/ታኬሺማ ደሴት ላይ ነው።

ደቡብ ኮሪያ ማክሰኞ እለት የቻይና እና ሩሲያ አውሮፕላኖች በምቆጣጠረው የአየር ክልል ገብተዋል ብላ ስትከስ፤ ኤ-50 የተሰኘ የሩሲያ አውሮፕላን በደሴቲቱ አቅራቢያ ሁለት ጊዜ የአየር ክልል መጣሱን በማስረጃ ታቀርባለች።

ሩሲያ በበኩሏ የቀረበባትን ውንጀላ ውድቅ አድርጋለች።

ከቅርብ አመታት ወዲህ የሩሲያና ቻይና ቦምብ ጣይ እና የቅኝት አውሮፕላኖች አልፎ አልፎ ደቡብ ኮሪያ የአየር ክልሌ የምትለውን ሥፍራ ጥሰው ይገባሉ።

Image copyright Getty Images

ሩስያ ምን አለች?

የሩሲያ መከላከያ ሚኒስትር ሁለት ሚሳኤል ተሸካሚ ቲዩ-95ኤምኤስ አውሮፕላኖች እንዲሁም ሁለት ሆንግ-6ኬ የቻይና ቦምብ ጣይ አውሮፕላኖችን ነፃ በሆነ የውሃ ቀጠና ላይ ለሚደረግ የቅኝት ልምምድ መቀናጀታቸውን ገልጿል።

በኤ-50 እና ኮንግጂንግ-2000 ተዋጊ ጀቶች የታገዘ ቅኝትና የቅድመ ማስጠንቀቂያ የሚሰጥ አውሮፕላን መታጀባቸውንም አክለው ገልፀዋል።

ነገር ግን የቅኝት ልምምዱን በሚያደርጉበት ወቅት 11 ጊዜ "ባዕዳን ተዋጊ" ባሏቸው አካላት ክትትል ተደረገብን በማለት ከስሰዋል።

ለዚህም የደቡብ ኮሪያ አብራሪዎች የይገባኛል እሰጥ አገባ ባለበት አካባቢ ላይ በወሰዱት እርምጃ "የአየር ክልሉን ቡድኑ በሚያቋርጡበት ሰዓት የበረራ ደህንነት አደጋ በመፍጠር" ሲሉ አደገኛ ሙከራ መደረጉን ጠቅሰው ከስሰዋል።

አክለውም የደቡብ ኮሪያ ጀቶችም የማስጠንቀቂያ ተኩስ መተኮሳቸውን ተናግረዋል።

ቅኝቱ የይገባኛል ጥያቄ ከሚነሳባት ደሴት 25 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የተደረገ መሆኑን በመጥቀስ የደቡብ ኮሪያ ፓይለቶችን "የአየር ላይ በጥባጮች" ሲሉ ቅሬታቸውን አቅርበዋል።

ሩሲያም ለደቡብ ኮሪያ መከላከያ አብራሪዎቻቸው ስለ ፈፀሙት አደገኛና ሕገ ወጥ ድርጊት ቅሬታ ማቅረባቸውን ተናግረዋል።

አሜሪካ ስደተኞችን ፍርድ ቤት ሳታቀርብ ወደመጡበት አገር መመለስ ልትጀምር ነው

በመድፈር የተወነጀለው ሮናልዶ አይከሰስም ተባለ

ደቡብ ኮሪያ ምን አለች?

ደቡብ ኮሪያ በበኩሏ ማክሰኞ እለት አምስት የጦር ጀቶች የአየር ክልሏን ጥሰው መግባታቸውን አስታውቃለች። ስለዚህ ሁለት የደቡብ ኮሪያ ጀቶች ጥሰው የገቡትን ጀቶች ተግባር ለማስቆም ተሰማርተዋል።

በመጀመሪያው የአየር ጥሰት 10 የማስጠንቀቂያ ተኩስና 80 ጥይት ተኩሰዋል።

የሩሲያ ኤ-50 አውሮፕላን ወዲያውኑ የአየር ክልሉን ለቆ ቢወጣም ተመልሶ በመግባቱ በተደጋጋሚ የማስጠንቀቂያ ተኩስ ተተኩሶበታል።

የደቡብ ኮሪያ መከላከያ ብሔራዊ ደህንንት ቢሮ ኃላፊ፣ ቹንግ ኢዩ ያንግ ለሩሲያ ክስ ጠንካራ ተቃውሟቸውን ያሰሙ ሲሆን፣ የሩሲያ የደህንነት ምክር ቤቱ ተገቢውን እርምጃ እንዲወስድ ጠይቀዋል።

"ይህ ጉዳይ ከተደገመ ጉዳዩን እንደ ቀላል አንመለከተውም፤ ከተደገመ ከዚህ ጠንከር ያለ እርምጃ እንወስዳለን" ሲሉም አስጠንቅቀዋል።

ደቡብ ኮሪያ ቅሬታዋን ለቻይና ያቀረበች ሲሆን፤ ቻይና በበኩሏ በደሴቲቱ ዙሪያ ደቡብ ኮሪያ የአየር ክልሌ የምትለው ድንበሯ ሳይሆን ሁሉም አገራት እንዳሻቸው የሚንቀሳቀሱበት ክልል መሆኑን በመጥቀስ ተሟግታለች።

ተያያዥ ርዕሶች