በአውስትራሊያ አደንዛዥ ዕፅ የጫነ መኪና የፖሊስ መኪና ገጭቶ በቁጥጥር ሥር ዋለ

በግጭቱ የተጎዱ መኪኖች Image copyright NSW POLICE

በአውስትራሊያ ሲድኒ በፖሊስ ጣቢያ ቆሞ የነበረ የፖሊስ መኪናን ገጭቶ ለማምለጥ የሞከረ መኪና በቁጥጥር ሥር ሲውል 200 ሚሊየን ዶላር የተገመተ አደንዛዥ ዕፅ ይዞ ተገኝቷል።

አሽከርካሪው 28 ዓመቱ ሲሆን የፖሊስ መኪና ገጭቶ በፍጥነት ለማምለጥ ሞክሯል። ፖሊስ ከአንድ ሰዓት በኋላ በከተማዋ ሰሜናዊ ክፍል ኢስትውድ በተባለ ስፍራ በቁጥጥር ሥር አውሎታል።

"አዲስ አበባ የምንወዛገብባት ሳትሆን በጋራ የምንኖርባት ከተማ ናት" ም/ከንቲባ ታከለ ኡማ

አሜሪካ ስደተኞችን ፍርድ ቤት ሳታቀርብ ወደመጡበት አገር መመለስ ልትጀምር ነው

በመድፈር የተወነጀለው ሮናልዶ አይከሰስም ተባለ

መኪናው ሲበረበርም 273 ኪሎ ግራም ሜት የተሰኘ አደንዛዥ ዕፅ ተገኝቶበታል።

ባለሥልጣናት በግጭቱ ማንም ሰው አለመጎዳቱን የተናገሩ ሲሆን፤ የፖሊስ መኪናው ግን "ከፍተኛ ጉዳት ደርሶበታል" ብለዋል።

በአውስትራሊያ ሜት የተሰኘው አደንዛዥ ዕፅ በበርካታ ተጠቃሚዎች ዘንድ የተለመደ ነው። ይህ አደንዛዥ ዕፅ ዋጋው እጅግ ውድ ሲሆን፤ በአገሪቱ በዚህ ንግድ ላይ የተሰማሩ ሰዎች ለሚፈፅሙት የተደራጀ ወንጀል ምክንያትም ነው ተብሏል።

በቁጥጥር ሥር የዋለው ግለሰብ ስሙ ያልተጠቀሰ ሲሆን፤ ፍርድ ቤት ቀርቦ ዕፅ በማቅረብ እና በግዴለሽነት በማሽከርከር እንደሚከሰስ ተነግሯል።