በባንግላዲሽ በሐሰተኛ ወሬ ሳቢያ ስምንት ሰው ተገደለ

የባንግላዲሽ ፖሊስ አዛዥ ጃቬድ ፓትዋሪ Image copyright AFP

በባንግላዲሽ "ሕፃናት ሊሰርቁ ነው" በሚል በተነዛ ሐሰተኛ ወሬ ሳቢያ ስምንት ሰዎች በደቦ ጥቃት መሞታቸውን ፖሊስ አስታወቀ።

ሟቾቹ በባንግላዲሽ ዋና ከተማ ደቡባዊ አቅጣጫ በዳካ ድልድይ ለመገንባት ሕፃን በመስዋዕትነት ሊቀርብ ያስፈልጋል ተብሎ በሰፊው መወራቱን ተከትሎ ጥቃቱ እንደተፈፀመባቸው ለማወቅ ተችሏል።

ይህ 3 ቢሊየን ዶላር የተመደበለት የድልድይ ግንባታ ፕሮጀክት የሕፃናት ደም ግብር ሊቀርብለት ይገባል የሚል አሉባልታ ሲወራ ነበር።

ከኢንጅነር ስመኘው ሞት በኋላ ህዳሴ ግድብ ምን ላይ ደረሰ?

"አዲስ አበባ የምንወዛገብባት ሳትሆን በጋራ የምንኖርባት ከተማ ናት" ም/ከንቲባ ታከለ ኡማ

ከዚህ በኋላ ነው ሕጻናት ሰርቀው ለድልድዩ ግንባታ መስዋዕት ሊያቀርቡ ነው የተባሉ ስምንት ሰዎች ላይ በደቦ ጥቃት የተፈፀመባቸው።

የፖሊስ አዛዥ የሆኑት ጃቬድ ፓትዋሪ፣ ዳካ ውስጥ ለጋዜጠኞች እንደተናገሩት በአሰቃቂ ሁኔታ ከተገደሉት መካከል አንዳቸውም በሕፃናት ስርቆት ውስጥ አልተሳተፉም።

ከተገደሉት መካከል የሁለት ልጆች እናት የሆነችው ታስሊማ ቤገም የምትገኝበት ሲሆን የ11 ዓመትና የአራት ዓመት ልጆች እንዳሏት ለማወቅ ተችሏል።

እንደ ፈረንሳዩ የዜና ወኪል ከሆነ ከዚህች እናት ግድያ ጋር በተያያዘ ስምንት ሰዎች በቀጥታ ተሳታፊነት ተጠርጥረው፣ አምስት ሰዎች ደግሞ ሐሰተኛ ወሬ በማናፈስ በቁጥጥር ስር ውለዋል።

ሟቾቹ እነማን ናቸው?

Image copyright Police handout

ቅዳሜ ዕለት የ42 ዓመቷና የሁለት ልጆች እናት የሆነችውን ቤገምን ከመኖሪያ አቅራቢያዋ በሚገኝ አንድ ትምህርት ቤት በራፍ ላይ 'የልጅ ሌባ' በሚል ቀጥቅጠው ገድለዋታል።

ወደ ትምህርት ቤቱ የሄደችው ለልጆቿ ምዝገባ ለመጠየቅ ሲሆን፤ የጥቃቱ አድራሾቹ ግን 'ልጅ ልትሰርቅ ነው' በሚል እንዳጠቋት የአካባቢው ነዋሪዎች ለአንድ ድረ ገፅ ተናግረዋል።

በደቡብ ወሎ እውን የህፃናት ስርቆት አለ?

እንደወጡ የቀሩት ተመራማሪዎች

ይህች እናት ስትገደል የተመለከተ መምህር ለድረ ገፁ ሲያስረዳ "ከሰዉ ብዛት አንፃር ምንም ማድረግ አንችልም ነበር " ብሏል።

ሌሎች እድሜያቸው በ30ዎቹ ውስጥ የተገመተ ወንድና ሴትም ባለፈው ሐሙስና ቅዳሜ በተለያየ አካባቢ በተመሳሳይ ልጅ ሊሰርቁ ነው በሚል በደረሰባቸው ድብደባ ምክንያት እንደሞቱ ተነግሯል።

ወሬው በምን ጀመረ?

የአገር ውስጥ መገናኛ ብዙሀን እንደዘገቡት፤ ወሬው መናፈስ የጀመረው በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ሲሆን፤ ከሁለት ሳምንት በፊት ጀምሮ በፌስቡክ እና በዩቲዩብ ላይ በሚለጠፉ ቪዲዮዎች አማካኝነት መሰራጨቱን ያስረዳሉ።

በዚህ የሐሰት ወሬ ላይ አንድ ሰው በባንግላዲሽ ሰሜናዊ ግዛት ኔትኦካና ውስጥ ህፃን ልጅ ቀልቶ አንገቱን ይዞ መታየቱን ይጠቅሳል።

በፌስ ቡክ ላይ በተሰራጨው ወሬ ሕፃናትን እያገቱ አንገታቸውን የሚቀሉና ለሚገነባው ፓዳማ ድልድይ መስዋዕትነት የሚያቀርቡ ሰዎች በተለያዩ ቦታዎች ተሰማርተዋል ይላል።

Image copyright Wikipedia Commons

ቢቢሲ ይህንን ወሬ የሚያሰራጩ የተለያዩ የፌስቡክ ጽሁፎችና ቪዲዮዎችን ተመልክቷል።

እሮብ ዕለት የመንግሥት አካላት በሰጡት መግለጫ ላይ እንደገለፁት ይህ ሐሰተኛ ወሬ እየተሰራጨ ያለው ሆን ተብሎ በአገሪቱ ውስጥ አለመረጋጋት ለመፍጠር ነው ብለው ነበር።

በኢትዮጵያ የመንጋ ፍትህ የሰው ህይወት እየቀጠፈ ነው

አምስት ሰዎች ደቡብ ወሎ ውስጥ በደቦ ጥቃት ተገደሉ

ፖሊስ ምን እያደረገ ነው?

እንደ መንግሥት ኃላፊዎች መግለጫ ከሆነ ይህንን ሐሰተኛ ወሬ የሚያሰራጩ 25 የዩቲዩብ፣ 60 የፌስቡክ፣ 10 ድረ ገፆች ተዘግተዋል። ከዚህ በተጨማሪም ይህንን ሐሰተኛ አሉባልታ ለመቀልበስ መንግሥት በመገናኛ ብዙኀን የግንዛቤ ማስጨበጫ ፕሮግራሞች እያካሄደና ማህበረሰቡ ምንም አይነት ጥቃት እንዳይፈፅም እያስጠነቀቀ ይገኛል።

በገጠሪቱ የአገሪቱ ክፍል ደግሞ መንግሥት የድምፅ ማጉያ ይዞ የወሬውን ሐሰተኝነት ለማስረዳት እየተንቀሳቀሰ ነው።

የአገሪቱ መገናኛ ብዙኀን በ2010 በድልድይ ግንባታ ምክንያት ተመሳሳይ የደቦ ጥቃትመመፈፀሙን ዘግበዋል።

በቅርቡም ኢትዮጵያ ውስጥ ደቡብ ወሎ አካባቢ ሕፃናት ይሰርቃሉ በሚል አምስት ሰዎች ላይ በተፈፀመ የደቦ ጥቃት መሞታቸውን መዘገባችን ይታወሳል።

በዚህ ዘገባ ላይ ተጨማሪ መረጃ