የአሜሪካ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ለትራምፕ የድንበር ግምብ ግንባታ ይሁንታ ሰጠ

የድንበር አጥር Image copyright EPA

የአሜሪካ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በደቡባዊ ድንበር ግምብ ለመገንባት የሚያስችላቸውንና ከፔንታጎን ያገኙትን 2.5 ቢሊየን ዶላር እንዲጠቀሙ ይሁንታ ሰጠ።

ካሊፎርኒያ ውስጥ የተሰየመውና በፌደራል ዳኛ የተመራው ችሎት ፕሬዝዳንቱ እንዳይጠቀሙበት ታግዶ የነበረውን ገንዘብ በአብላጫ ድምፅ በመሻር ይሁንታውን ሰትቷቸዋል።

ግንቡ ሜክሲኮንና አሜሪካን የሚለይ ሲሆን፤ የፕሬዝዳንት ትራምፕ የ2016 የምርጫ ቅስቀሳ ዋነኛ አካል ነበር።

አሜሪካና ሜክሲኮን የሚለየው ግንብ መገንባት ተጀመረ

"ትራምፕን ከቁብ አትቁጠሩት" አራቱ የኮንግረስ አባላት

በአሜሪካ ድንበር ላይ ተይዞ የነበረው ስደተኛ ህፃን ሞተ

ዲሞክራቶች ይህንን ውሳኔ አምርረው ተቃውመውታል።

በፍርድ ቤቱ ውሳኔ መሰረት ፕሬዝዳንት ትራምፕ ገንዘቡን በካሊፎርኒያ፣ አሪዞና እና ኒው ሜክሲኮ ድንበር ግንቡን ለመገንባት ይጠቀሙበታል። ፕሬዝዳንት ትራምፕ በትዊተር ገፃቸው ላይ ብቅ ብለው "ታላቅ ድል" ብለዋል።

በካሊፎርኒያ የዋለው ችሎት ኮንግረስ ፈንዱን ግንቡን ለመገንባት እንዲውል አልፈቀደም ሲል ተከራክሯል።

አርብ እለት አሜሪካና ጓቲማላ ስምምነት የተፈራረሙ ሲሆን፤ በጓቲማላ በኩል ከሆንዱራስ እና ኤልሳልቫዶር የሚመጡ ስደተኞች በቀጥታ ወደ አሜሪካ እንዲገቡ ከሚደረግ ይልቅ በቅድሚያ ጓቲማላ ጥገኝነት እንዲጠይቁ የሚያስገድድ ነው።

አፈ ጉባኤዋ ናንሲ ፒሎሲ "የከፍተኛው ፍርድ ቤት ውሳኔ ትራምፕ የወታደሩን ፈንድ እንዲሰርቁ የሚያደርግና እርባና በሌለው ተግባር ላይ እንዲያውሉት የሚፈቅድ ነው"ብለዋል።

እንደ አሜሪካ ባለሥልጣናት ከሆነ በሰኔ ወር ብቻ በድንበር የሚያቋርጡ ስደተኞች ቁጥር በ28 በመቶ ቀንሷል።

የትራምፕ አስተዳደር መቀነሱ የታየው የስደተኞችን ቁጥር ለመቀነስ ከሜክሲኮ ጋር የተወሰደው ፖሊሊን ተከትሎ ነው ሲሉ ይናገራሉ።

ተያያዥ ርዕሶች

በዚህ ዘገባ ላይ ተጨማሪ መረጃ